
ህብር ሬዲዮ ጃዋር መሐመድ <<ኦሮሞ ፈርስት>> ለሚል ስብሰባ በቬጋስ በተገኘበት ወቅት ቃለ መጠይቅ አድርገንለታል።
ከጃዋር መሐመድ አወዛጋቢ ሆኖ የወጣው ንግግሩንና በአሁኑ ወቅት በተለያየ ቦታ <<ኦሮሞ ፈርስት>> በሚል እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ መሰረት በማድረግ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገናል።
ጃዋር <<ኦሮሞነቴ ከኢትዮጵያዊነቴ ይቀድማል>> ማለቱን ተከትሎ የመጣው አስተያየት የአገሪቱን ፖለቲካ አርባ ዓመት ወደ ሁዋላ ጎትቷል ይላል ።እንዴት? በእነዚህና በሌሎች ተያያዥ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።
<<..የሀይማኖት መቻቻል ለኔ የፖለቲካ ዘፈን ሳይሆን የቤተሰብ ጉዳይ ነው…>>
<<…ይሄ ፖለቲካ ለካ ላይ ላዩን እንጂ ውስጡ ጥሬ ነው…>>
<<…አማራ የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት አይደለም…>>
<<…የተዳፈነውን ቁስል የቀሰቀስነው እኛ አይደለንም ።…መወንጀል ያለበት ዘለፋ የከፈተብን ነው…>>
<<…ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፌዴራሊዝም የሕዝቦች የትግል ውጤት ነው…>>
<<እኔ ኦሮሞ ነኝ ማለቴ ካስቆጣው ሀይል ጋር አብሮ መስራት አይቻልም…በዛ አገር ጸረ ኦሮሞ አመለካከት አለ…>> ከጃዋር መሐመድ ንግግሮች ጥቂቶቹ (ሙሉውን ያዳምጡት) http://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-exclusive
No comments:
Post a Comment