Monday, September 30, 2013

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ውሎ በኖርዌይ

የግንቦት 7 ሕዝባዊ  ኃይል ድጋፍ ማሰባሰቢያ በደማቅ ሁናቴ ተጠናቀቀ
ቅዳሜ ሴፕቴበር 28  በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት 7 ሕዝባዊ  ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ በደመቀና በተሳካ እንዲሁም የሕዝቡ ቁርጠኝነት በታየበት ሁናቴ ተከናወነ ።
በዲሞክራቲክ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ኖርዌይ አስተባባሪነት ለግንቦት 7 ሕዝባዊ  ኃይል ድጋፍ ለመስጠት የተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ በተሳካና በአማረ ሁናቴ እንዲካሄድ በማድረግ በኖርዌይ የሚገኙ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች ፣የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አባሎችና ደጋፊዎች፣በኖርዌይ የሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ከተለያዩ አገራት  ከስዊዲን፣ከኢንግላንድ፣ከሲዊዘርንድ የመጡ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ለአገራቸው ለውጥ ለማምጣት  የገቢ ማሰባሰቢያውን ገንዘብ በማዋጣት ለግንቦት 7ሕዝባዊ  ኃይል አለኝታ መሆናቸውን አሳይተዋል።

በዲሞክራቲክ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ኖርዌይ ፕርግራሙ የታቀደው ከ 3 ወር በፊት  ቢሆንም በወያኔ ደጋፊዎችና አባሎች ብዙ የተንኮል ሴራ ቢጋርጥበትም ፕሮግራሙን በተሳካ ሁናቴ እንዲደረግ ተደረጓል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ጫፍ መድረሱን የተረዱ የወያኔ ደጋፊዎችና አባላቶች በከፍተኛ ሁናቴ ፕሮግራሙ እንዳይካሄድ በኖርዌጅያን  ጋዜጦች፣በወያኔ ብሎጎች፣ በወያኔ ድረገፆችና ፌስቡክ ላይ የኖርዌጅያን መንግስትንና ሕዝብን እንዲሁም በኖርዌይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ማኅበረሰብን ለማደናገር ሴራ ሲዶልቱና ለማስተጓጎል ቢከርሙም  በጉዳዩ ላይ የኖርዌጅያን ሙዕራዎች አጥጋቢ መልስ በመስጠት አሳፍረዋቸዋል።
በዲሞክራቲክ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ኖርዌይ የፕሮግራሙ አዘጋጆች የተጠናከረ ስልት በመጠቀም የፕሮግራሙ አላማ እንዲቀጥል፣ ከግብ እንዲደርስና እንዲከናወን አድርገውታል።በኖርዌይ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የተደረገውን ሴራ በመቀልበስ ለጥሪው አጥጋቢ ምላሽ ሰተዋል።
በገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ላይ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ፣የግንቦት 7 ሕዝባዊ  ኃይል ከፍተኛ ባለስልጣን ኮማንደር አሰፋ ማሩ ፣እንዲሁም በዲሞክራቲክ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ኖርዌይ ዋና ሊ/ መንበር  አቶ ዳዊት መኮንን የተገኙ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የጀግና አቀባበል  ተደርጎላቸዋል።
የፕሮግራሙ መክፈቻ ንግግር በዲሞክራቲክ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ዋና ሊቀመንበር  አቶ ዳዊት መኮንን የተደረገ ሲሆን በመቀጠልም  የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ንግግር አድርገዋል ። አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የግንቦት 7 ሕዝባዊ  ኃይል የትግሉን ጅማሬና አሁን የደረሰበትን ሁናቴ፣ በተለያዩ የአለም አገራት በአሜሪካ ፣ በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወንዶች፣ሴቶች ግንባሩን እየተቀላቀሉ እንደሆኑና እንዲሁም መንግስት በሐይማኖት ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት እነቢ በማለት ከገዳም የመጡ መነኮሳትም ግንባሩን እንደተቀላቀሉት የሚያሳይ በፕሮጀክተር የተደገፈ ምስል አሳይተው ማብራሪያ ሰተዋል።ይኸም ደግሞ የታዳሚውን ልብ ነክቷል።በመቀጠልም የግንቦት 7 ሕዝባዊ  ኃይል ከፍተኛ ባለስልጣን ኮማንደር አሰፋ ማሩ ንግግራቸውን ያደረጉ ሲሆን እሳቸውም የወያኔን በደልና ግፍ  ለታዳሚው በማብራራት  ሕዝቡ ወደ ትግል እንዲገባ ጥሪ አስተላልፈዋል።ለግንባሩም የቀረበውን አንድ  ላፕቶፕ ኮምፒውተር ስጦታም ተቀብለዋል።
በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ጨረታዎች፣ ባህላዊ ምግቦች እንዲሁም የተለያዩ የአገር ባህል ልብሶችና ጌጦች በሽያጭ ቀርበው፣በጨረታና በስጦታ ብቻ 408 ,633.85 የኖርዌጅያን ክሮነር የተገኘ ሲሆን በስጦታው ወቅት ላይ ሰዎች የአንገት ሀብላቸውን ሳይቀር አበርክተዋል። 
  ይህ ገቢ ከምግብ ሺያጭ ፣ ከመግቢያ ትኬት፣ ከቲሸርት ሺያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶች ሺያጭ ሳይጭምር መሆኑ ወዳጆችን ሲያስፈነድቅ ጠላቶችንን አንገት አስደፍቷል ። በፕሮግራሙ በስተ መጨረሻ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁናቴ የሚያሳይ ድራማ የቀረበ ሲሆን ፕሮግራሙ ሊጠናቀቅ ሲል የግንቦት 7 ሕዝባዊ  ኃይል መዝሙር በደማቅ ሁናቴ ተዘምሯል ።
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎችን አነጋግረን በሰጡት አስተያየት በኖርዌይ ለግንቦት 7 ሕዝባዊ  ኃይል  የተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ሌሎችም አርአያ ሊሆን እንደሚችል ገልፀዋል።

 ከሰብኣዊ





No comments:

Post a Comment