Monday, September 30, 2013

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ይህንን የማፊያ ቡድን በማፍረስ ታሪክ ይስሩ! በግርማ ሠይፉ ማሩ

Girma-Seifu2
በግርማ ሠይፉ ማሩ
ግርማ ሠይፉ ማሩ
በ2005 ዓ.ም የምክር ቤት ዘመን መጨረሻ ላይ የደህንነት መስሪያ ቤቱን በሚኒስትር ደረጃ ለማዋቀር የሚረዳ አንድ አዋጅ ለምክር ቤት ቀርቦ ፀድቆዋል፡፡ ይህ አዋጅ ሲፀድቅ ከነቅሬታዬ ያለኝ ድጋፍ መስጠቴ ይታወቃል፣ ለዚህ አዋጅ ድጋፍ መስጠት የፈለኩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከበረሃ ይዘውት የመጡት ልዩ ልዩ አፋኝ ቡድን ስለማይኖራቸው እንዲሁም ቀደም ሲል የነበሩትን አፋኝ ቡድንች ወደ አንድ መዋቅር በማጠቃለል ተጠሪነቱ ከተለያዩ መዋቅሮችና ግለሰቦች ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ (ወደ ተገቢው ማለት ነው) ቁጥጥር በማስገባት ለዜጎች ስጋት ሳይሆን ለዜጎች እና ለሀገር ደህንነት የሚስራ ተቋም ይሆናል በሚል ተስፋ ነው፡፡ ይህ ተስፋዬም ዝም ብሎ ሳይሆን በአዋጁ አንቀፅ 3 “ይህ አዋጅ በመላው ሀገሪቱ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ በፌዴራልም ሆነ በክልል መንግስታት ደረጃ ሌላ የመረጃና ደህንነት ተቋም ማቋቋም አይቻልም” የሚል ድንጋጌ በመያዙ ነው፡፡ በመስከረም 19 እሁድ ዕለት አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ “በሰላም” ከተጠናቀቀ በኋላ እጅግ አሰገራሚ የሆነ ተግባር አጋጥሞናል፡፡ ተስፋዬንም ስለአጨለመብኝ ይህን ጉዳይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያውቁትና የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎቱ ኃላፊውን ጠርተው ማብራሪያ እንዲጠይቁ መነሻ ለመስጠት ነው፡፡

የፓርቲያችን ወጣቶች በሰልፉ ላይ ወጣቶችን፣ ሙስሊሙን፤ ክርስቲያኑን፣ ሴቶችን እንዲሁም በግፍ የታሰሩትን ዜጎች በተመሳሌነት ለማሳየት እጃቸውን እና እግራቸውን በሰንሰለት አስረው ከፊት ሆነው ሰልፍ ላይ ሲታዩ ነበር፡፡ ማንነታቸው ያልታወቀ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ከነዚህ ወጣቶች አንዱን ጎትተው ከታክሲ በማውረድ ወደ መኪና ውስጥ ለመጫና ሲሉ በአካባቢው የነበሩ የአንድነት ወጣቶች ደርሰው መውሰድ አትችሉም በሚል ግርግር ሲፈጠር በቦታው ደረስኩ፡፡ በቦታው ደርሼ ይህን የሚፈፅሙትን ሰዎች መታወቂያ እንዲያሳዩኝ ሰጠይቅ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በአካባቢው የነበሩትን ፖሊሶች (ባለ ኮከብ ማዕረግ ያለቸው ጭምር) አስጠርቼ መታወቂያ እንዲያሰዩን እንዲያደርጉ ቢሞከርም እነዚህን ጉልበተኞች መታወቂያ ሊጠይቅ የሚችል ሞራል ያለው ፖሊስ አጣን፤ ህዝብ በተሰበሰበበት ፖሊሶችን እንዴት እንደሚያደርጓቸው ማየት በእውነት በምን ሁኔታ ላይ እንዳለን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከፖሊሶቹ አንዱ ጠርቶኝ እነዚህ እኮ ከእኛ አቅም በላይ ናቸው ሲለኝ በቅርቡ በኢሳት ቴሌቪዥን ቀርቦ ምስክርነት የሰጠው የፖሊስ መኮንን ትዝ ብሎኝ የመንግስታችን ባሕሪ አሁንም ለውጥ እያሳየ ያለመሆኑ እና ፊት ለፊት ከምናያቸው ተቋሞች ጀርባ ሌላ ስልጣን እንዳለ ፍንትው ብሎ ታየኝ፡፡ የሚገርመው በዚያው ዕለት እኔን እያወቁኝ መኪናዬን በግዳጅ አሰቁመው መንጃ …read more
Via: Zehabesha

No comments:

Post a Comment