Wednesday, September 25, 2013

የባንድራ ላይ ጥቃት (State structural terrorism against flag) በወያኔ ተፈጽሟል::

Image
ስለባንዲራ የተጨነቁ በመምሰል ማንንም ማታለል አይቻልም::
ቅድሚያ ለሰብኣዊ መብት!!! በባንድራ ላይ መንግስታዊ ጥቃት ይቁም!!!
ምንሊክ ሳልሳዊ
ይህን ሰሞን ያቺ በአመት በየወረቱ ህዝብን ለማታለል ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የሚለፉባት ቀን መታለች:: መሰረታዊ የዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸን የጠየቁ ኢትዮጵያውያንን ለመወንጀል ይኸው የባንድራ ላይ ጥቃት (State structural terrorism against flag) በወያኔ ተፈጽሟል:: ኢትዮጵያውያን ስርኣቱ የማይቀበሉ;የተቃወሙ; መሰረታዊ የዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን የጠየቁ ሁሉ ጸረ-ባንድራ ናቸው;የአብዬን ወደ እምዬ!!..ትላንትና በአለም አደባባይ ሲንቁት እና ሲያዋርዱት የነበረው ባንድራ ዛሬ የተገላቢጦሽ አድርገውት የራሳቸውን ወንጀል በሃገር ወዳዱ ህዝብ ላይ ማላከክ ጀምረዋል::

ወያኔ በረሃ በነበረበት ወቅት ባንዲራን(የኢትዮጵያን) ለተለያዩ አስቀያሚ ድርጊቶች ይጠቀምባቸው እንደነበር ደርግ በሚዲያዎቹ ነግሮናል :: በ1982 አ.ም. መጨረሻዎቹ ወደ አምቦ ተጉዠ የተገናኘኋቸው የዛሬ አንድ ከፍተኛ ሚኒስትር ባንዲራን በተመለከተ ጠይቄቸው ቃል በቃል =” ባንድራው ብሄረሰቦችን ቅኝ ለመግዛት የተወከለ ነው::…” ብለውኝ ነበር :: በተመሳሳይ በበረሃው ትግል ወቅት ጋዜጠኛ የነበረው ሴክቱሬ ጋር በተለያየ ጊዜ በተደረገው የስልክ ግንኙነት ባንድራ ትርጉም አልባ እንደነበር ይነግረን ነበር::
ዛሬ የባንድራ እና የባንድራ ባለቀኖች ሆነው በመታየት የሚመጻደቁት ትላንት ባንድራዉ ጨርቅ ነው አላማን ያዘናጋል የቅኝገዢዎች መሳሪያ ነው እንዳላሉ ዛሬ በየትኛው የሞራል አቅማቸው ባንድራን ለማክበር እንደሚንደፋደፉ ግልጽ ሊሆን አልቻለም::ይህን ሰሞን ደሞ ደርሶ ሃኪም የሚሆኑት ወያኔዎች የእኩልነት ፣ የሉአላዊነት እና የማንነት መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ አላማ ክብር እና እሴት በሚሸረሽር መልኩ የሚጠቀሙ የአንዳንድ ወጣቶችን እንቅስቃሴ ወጣቱ እንዲያወግዝ ጥሪ አቅርበዋል።…ይህ ማለት ምን እንደሆነ አልገባንም … ሊገለጽልን ይገባል ትላንት በሱማሌ በረሃዎች አልሸባብን ለመወንጀል ራሳቸው ወያኔዎች ባንዲራ ሲያቃጥሉ ነበር …እንዲሁም መሰረታዊ የዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸን የጠየቁ ኢትዮጵያውያንን ለመወንጀል ይኸው የባንድራ ላይ ጥቃት (State structural terrorism against flag) በወያኔ ተፈጽሟል::
ትላንት ቀዳደው የጨው መቋጠሪያ እና ቁምጣ ሲሰፉበት እንዳልነበር ባንድራውን ዛሬ ላይ የተቀደደ የተቦጫጨቀ … እያሉ ስም እየሰጡ መቤቴን ያለውን ኢትዮጵያዊ ለመወንጀል መሯሯጥ የትም አያደርስም::ትላንት የተቀዳደደ ባንድራ ይዞ አደባባይ ወጣ የተባለ ግለሰብ ፊልሙ በወያኔ የቴሌቭዥን ጣቢያ እጅ ይገኛል:ለምንስ ተይዞ ለፍርድ የማይቀርበው? ባንድራ የማንነት መገለጫ እንጂ የኢትዮጵያውያን መወንጀያ አይደለም::አንድን ነገር ከመስራታቸው በፊት ወያኔዎች ሁለት ጊዜ ወደፊት ራመድ ብለው ያስቡ ዘንድ እንመክራለን::ስለባንዲራ የተጨነቁ በመምሰል ማንንም ማታለል አይቻልም::

No comments:

Post a Comment