1ኛ. አቶ የሺዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ት ሰብሳቢ
2ኛ. አቶ ስሜነ ፀሃይ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት አባል የሆኑት ለእስራት ተዳረጉ፡፡
አንድነት ፓርቲ በትላንትናው ዕለት በመንግስት አፈና የተደረገበት የተቃውሞ ሠልፍ ማካሄዱ የሚታወቅ ነው፤በተቃውሞ ሠልፍ ላይ ለመሣተፍ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ አባል እና የአንድነት ፓርቲ ም/ት ፕሬዝዳንት የሆኑቱ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ወደ ተቃውሞ ሠልፍ በማምራት ላይ እያሉ ፒያሳ በሚገኘው አፍሪካ ወርቅ ቤት አካባቢ በደንነቶች እና በፖሊሶች ወከባ የተፈፀመባቸው ሲሆን ይህን ወከባ በመከላከል እና በመቃወም አጋርነታቸው እና ወገናዊነታቸውን ያሳዩ ለእስራት ተዳረጉ፡፡
ከላይ ስማቸው የተገለፀው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በአቶ ግርማ ሰይፉ ላይ ሊፈፀም የታሰበው መንግስታዊ ደባ ለማከሸፍ የተቻላቸው ቢሆንም እነሱ ግን ለእስራት ተዳርጓል፡፡በሁን ሰዓት ጃንሜዳ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙ ሲሆን በነገው ዕለት 21/01/2006 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ሰዓት ሾላ አካባቢ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ የከተማ ነክ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ችሎት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡2ኛ. አቶ ስሜነ ፀሃይ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት አባል የሆኑት ለእስራት ተዳረጉ፡፡
አንድነት ፓርቲ በትላንትናው ዕለት በመንግስት አፈና የተደረገበት የተቃውሞ ሠልፍ ማካሄዱ የሚታወቅ ነው፤በተቃውሞ ሠልፍ ላይ ለመሣተፍ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ አባል እና የአንድነት ፓርቲ ም/ት ፕሬዝዳንት የሆኑቱ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ወደ ተቃውሞ ሠልፍ በማምራት ላይ እያሉ ፒያሳ በሚገኘው አፍሪካ ወርቅ ቤት አካባቢ በደንነቶች እና በፖሊሶች ወከባ የተፈፀመባቸው ሲሆን ይህን ወከባ በመከላከል እና በመቃወም አጋርነታቸው እና ወገናዊነታቸውን ያሳዩ ለእስራት ተዳረጉ፡፡
ይድነቃቸው ከበደ
No comments:
Post a Comment