Wednesday, September 25, 2013

የጸረ ሽብርተኝነት አዋጁን መቃወም

የጸረ ሽብርተኝነት አዋጁን መቃወም ሽብርተኝትን ከመደገፍ ጋር ያለው ልዮነት የሰማይና የምድር ያህል መሆኑን አይነተኛ ማሳያው ህገ መንግስቱና ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውና ያጸደቀቻቸው አለም አቀፍ ህጎች ናቸው፡፡አዋጁ በህገ መንግስቱና በአለም አቀፍ ህግጋት ከለላ እንደሚያገኙ የተነገረላቸውን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያለመታሰር፣ዋስትና የማግኘት፣ ጠበቃን የማናገር ፣በሰው የመጎብኘት፣ በሀይል የተሰጠ የእምነት ክህደት ቃል በፍርድ ቤት ተቀባይነት እንዳይኖረው የማድረግ፣የግል ሚስጥሮችን የስልክ ጠለፋ፣የኢሜይል አካውንት ብርበራ፣ በመኖሪያ ቤት በድብቅ ካሜራዎች የመሰለል ተግባራት በጸረ ሽብር አዋጁ እንዲጣሱ በመደረጋቸው አዋጁን እቃወማለሁ፡፡

No comments:

Post a Comment