የሰላማዊ ትግል መርሆዎችን በሙላ ተጠቅሞ ትግል ለማድረግ በቁርጠኝነት የተቋቋመዉ ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ሊያደርገዉ ያሰበዉን የተቃዉሞ ሰልፍ በታሰበበት እንዳይዉል እንቅፋት በመሆን ዳግም አፋኝ መሆኑን አምባገነኑ ኢህአዲግ ባደባባይ አስመሰከረ!!!
እንደሚታወቀዉ በግንቦቱ ሰልፍ ላይ ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ ካልተሰጠ ፓርቲዉ በድጋሚ ሰልፍ እንደሚጠራ አስታዉቆ ነበር - በመሆኑም ነሐሴ 26 ይህ ሰልፍ እዲደረግ ዝግጅት ሲደረግ ከረመ - ነገር ግን አፍኖና አሸማቆ ሊገዛን የሚሻዉ ኢህአዲግ በሌለ የሃይማኖት አክርሪነት ሽፋን በጠራዉ እና እያስገደደና እያስፈራራ ባስወጣዉ ሰልፍ ሰበብ ነሐሴ 25 ሌሊት አሰነዋሪና ከአንድ ለህዝብ ቆሚያለሁ ከሚል መንግስት በማይጠበቅ መልኩ በድብደባ በማስፈራራትና በማዋከብ ይህን ብዙ የታሰበለትን የተዘጋጀንበትን ሰልፍ አከሸፈ . . .
ይህ መንግስታዊ ዉንብድና ግን ጥያቂያችንን መቼዉንም ቢሆን ከማንሳት አላስቀረዉም . . . እንዲያዉም ትግሉን አጠናክረን እንድንቀጥል ምክንያትና የመንፈስ ጥንካሬ ጨመረልን እንጂ . . . እናም በድጋሚ ኢህአዲግን በህግ የበላይነት እንዲመራና ላነሳናቸዉም ጥያቄዎች መፍትሄ እንዲበጅላቸዉ ለመስከረም 12 በመስቀል አደባባይ ዳግም ለመሰብሰብ ቀጠሮ ተያዘ . . . በነሐሴዉ ዉንብድናዉ የፖለቲካ ኪሳራ ዉስጥ ራሱን የከተተዉ ገዢዉ መደብም በተለያዩ ብልሹ አስተዳደሮች ቀኑን ለማስቀየር ያደረገዉ ጥረት በቁርጠኛዉ የሰማያዊ አመራርና አባላት ተቀባይነት ሊያገኝ ባለመቻሉና ሰላማዊ ሰልፍ ኢህአዲግ በመረጠልን ቀን እንደማናደርግ ለዚህም በምንም ተአማር ከአቋማችን ንቅንቅ እንደማንል ሲረዳ ቦታ ልምረጥላችሁ ብሎ ሌላ እሰጥአገባ ያዘ . . . ስራ አስፈፃሚዉም ህገ መንግስቱን እና አዋጁን ተከትሎ ከመስቀል አደባባይ ምንም የሚያስቀረን ህጋዊ ማእቀፍ እንደሌለ ተከራክሯል - መጀመሪያ ላይ በምክንያትነት መስቀል አደባባይ እንዳናደርግ ግንባታ ላይ ነዉ የሚል ምክንያት ቢያቀርቡም ከሁለት ሳምንት በፊት እራሱ ኢህአዲግ ያስተባበረዉ እና ያቀናበረዉ ሰልፍ የተካሄደበት እንደነበረ ያብቻም ሳይሆን ከ 4 ቀናት በኋላም ከመላዉ የከተማዉ አካባቢዎች የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች የመስቀል በአልን እንደሚያከብሩበት እየታወቀ ግንባታ ላይ ሰለሆነ አዛ አትወጡም የሚለዉ ምክንያት ፍፁም ትክክል አለመሆኑንና ፓርቲዉ እንደማይቀበለዉ አድካሚ በሆኑ የደብዳቤ ምልልሶች አሳዉቋል!!! በመጨረሻም ጭራሹኑ መስቀል አደባባይን ኢህአዲግን ለሚቃወሙ አንደተከለከለ ቃል በቃል ተናግረዉ ሰልፉን በጃንሜዳ አድርጉ የሚል ፍፁም ተቀባይነት የሌለዉ አሳፋሪ መልስ ለፓርቲዉ አመራሮች ደረሳቸዉ!!! ይህ ሀላፊነትና ፍትሀዊነት የጎደለዉ አሰራርን እንደምናወግዝ በምንም መልኩ ከመስቀል አደባባይ ዉጪ ሰልፍ እንደማናደርግ ለዚህም ሙሉ ህገ መንግስቱን መሰረት አድርገን መብታችንን በሰላማዊ መንገድ እንደምናሰማ በፅኑ አቋም ዝግጅታችንን ስናደርግ ዘሬ ላይ ደረስን . . .እንደሚታወቀዉ በግንቦቱ ሰልፍ ላይ ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ ካልተሰጠ ፓርቲዉ በድጋሚ ሰልፍ እንደሚጠራ አስታዉቆ ነበር - በመሆኑም ነሐሴ 26 ይህ ሰልፍ እዲደረግ ዝግጅት ሲደረግ ከረመ - ነገር ግን አፍኖና አሸማቆ ሊገዛን የሚሻዉ ኢህአዲግ በሌለ የሃይማኖት አክርሪነት ሽፋን በጠራዉ እና እያስገደደና እያስፈራራ ባስወጣዉ ሰልፍ ሰበብ ነሐሴ 25 ሌሊት አሰነዋሪና ከአንድ ለህዝብ ቆሚያለሁ ከሚል መንግስት በማይጠበቅ መልኩ በድብደባ በማስፈራራትና በማዋከብ ይህን ብዙ የታሰበለትን የተዘጋጀንበትን ሰልፍ አከሸፈ . . .
ሌሊቱንም ወደ 15 የሚጠጉ አመራሮችና አባላት በፓርቲዉ ፅህፈት ቤት በማደር ዝግጅቱ እስከመጨረሻዉ ሰአት ቀጠለ . . . ንጋቱ ላይም ቀስ በቀስ በርካታ ደጋፊዎችና አባላት በፓርቲዉ ፅህፈት ቤት ግቢ መሰባሰብ ጀመሩ ግቢዉም ሞቅ ሞቅ በሚያደርጉ ሀገራዊ ዜማዎች የነፃነትን አየር ይተነፈስበት ያዘ . . . ሰዓቱ ሲደርስም ሰልፉን ከፊት አስተባባሪዎች እየመሩትና መፈክሮችን እያሰሙ ተጀመረ ሆኖም ግን ከግንፍሌ ድልድይ ትንሽ ፈቅ ብሎ ወደ ዋናዉ መንገድ እንደገባ መንገዱን በመኪናና በርካታ ቁጥር ባላቸዉ የፖሊስ አባላት በመዝጋት ወደ አራት ኪሎ እንዳንሄድ እንቅፋት ሆኑ - ከፍርሀታቸዉ ብዛት በአልፋ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ዉስጥም በቁጥር እጅግ ሚልቁ የፌደራል ፖሊሶች ታይተዋል - በመንገዶችና በካፌዎች ዉስጥም እጅግ በርካታ ደህንነት ሰዎች ቀረፃና ክትትል ሲያደርጉ ታዝበናል. . . ያም ሆኖ ሰልፈኛዉ ባለበት በመቀመጥ መፈክሮችን ያሰማ ጀመር በዚህም መሀል የተመረጡ አመራሮች ፖሊስ ህግ እንዲያስከብር እንጂ ወደ አደባባይ እንዳንወጣ መከልከል እንደማይችል መንገዱንም እንዲከፍቱልንና ሰልፋችንን እንድንቀጥል ለማናገር የተደረገዉ ሙከራ ሳይሳካ ቀረ . . . በየመንገዱ ሲጠብቀን የነበረ ህዝብ ሁላ እንዳይቀላቀለን በተለያየመንገድ ማዋከብም አንዱ የአፈናዉ አካል ነበር . . . በዚህ ወቅት ከፍ ብለዉ ይሰሙ የነበሩ መፈክሮች በጥቂቱ ይህን ይመስላሉ
♦አደባባዮች የህዝብ ናቸዉ
♦መስቀል አደባባይ የኢትዮጲያ ህዝብ ነዉ
♦ ፖሊስ የህዝብ ነዉ
♦ ፖሊስ የአምባገነን ገዢዎች መጠቀሚያ አይደለም
♦ በህግ አምላክ
♦ የፍትህ ያለ
♦ ነፃነት እና ፍትህ እንፈልጋለን
♦ ኢህአዲግ ህገመንግስቱን ያክብር
በመጨረሻም መንግስት ነኝ የሚለዉ ኢህአዲግ አፈናዉን በይፋ ስለፈፀመ! ትግሉን በተጠናከረ መልኩ ከፍ ባለ ምዕራፍ ለመቀጠል በማሰብና ካላስፈላጊ ግጭት ዉስጥ ባለመግባት ፓርቲዉ ለተነሳላቸዉ አላማዎች ፍፁም ሰላማዊ መሆኑንና መቼዉንም ቢሆን አምባገነኑ ኢህአዲግ በፈለገዉ መልኩ እንደማይሄድ በማሳወቅ ሳይጀመር የተስተጓጎለዉን ሰልፍ በፓርቲዉ ግቢ በመሰባሰብ ሰላማዊ ትግሉ በተለያዩ መንገዶች ለማስቀጠል ቁርጠኛ አቋም ተወስዷል!!! ሰልፉን ለማደናቀፍ ተደረገዉም ማናቸዉም ህገ ወጥ ተግባር ዳግም የመንፈስ ጥንካሬንና አሸናፊነትን አጎናፅፎናል! ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
♦♦♦ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ!♦♦♦
የነፃነት ቀን ቀርባለች!
ከአማሃ
No comments:
Post a Comment