የፕሬዚዳንትነት ቆይታቸውን በማጠናቀቅ ላለፉት 12 ዓመታት የቆዩበትን ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ለአዲሱ ፕሬዚዳንት እንደሚያስረክቡ ለሚጠበቁት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ መኖሪያ እንዲሆን በወር 530 ሺሕ ብር የሚከፈልበት ቤት ለመከራየት የተገባው ውል ተሰረዘ፡፡
ምንጮች እንደገለጹት፣ ፕሬዚዳንት ግርማ በቅርቡ ከቤተ መንግሥት ሲለቁ ከነቤተሰቦቻቸው እስከ ሕይወት ፍፃሜያቸው ይኖሩበታል ተብሎ የተመረጠውና በወር 530 ሺሕ ብር ለመክፈል ከቤቱ ባለቤት ጋር የተደረገው ስምምነት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት ቀርቦ ውል ታስሮበት ነበር፡፡ ሆኖም የኪራይ ስምምነቱ ውል ከተፈረመ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ውሉ እንዲቋረጥ መወሰኑን አስታውቋል፡፡
አዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ የሚገኘውን ለፕሬዚዳንት ግርማ መኖሪያ የተመረጠውን ቤት ለመከራየት ከአከራዩ ጋር የኪራይ ውል ስምምነት ያደረገው የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ነበር፡፡ ቀድሞም ቢሆን ስምምነቱ የተጋነነና ለG+1 መኖሪያ ቤት ይህን ያህል ዋጋ ይከፈላል የሚል ሙግት ቀርቦ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ስምምነቱ በይፋ ከተፈረመ በኋላ ግን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጭምር ኪራይ ተገቢ አይደለም በማለት ውሳኔ በማስተላለፋቸው፣ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት በውሉ ውስጥ የተካተቱትንና ውሉን ለማፍረስ ያስችሉኛል ያላቸውን አንቀጾች በመጥቀስ እንዲሰረዝ አድርጓል፡፡ ይህንንም የመኖሪያ ቤቱን ለማከራየት ውል ለገቡት ባለንብረት በደብዳቤ ማስታወቁንም ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የኪራይ ስምምነቱን የመዘገበው የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤትም ውሉ መሰረዙን እንዲያውቅ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ ጽፏል ተብሏል፡፡
ሕጋዊ የውል ስምምነት ስለመደረጉ ማረጋገጫ የሰጠውና ምዝገባ ያካሄደው የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት፣ ለፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ተብሎ የኪራይ ስምምነት የተደረገበት ውል እንዲሰርዘው በደብዳቤ ተገልፆለታል ተብሏል፡፡
ተጋነነ የተባለው የቤት ኪራይ ውል የተፈጸመው በአገሪቱ ሕግ መሠረት ሥልጣናቸውን ለለቀቁት ፕሬዚዳንት ቀሪ ሕይወታቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲያሳልፉ አስፈላጊው ጥቅማ ጥቅም መጠበቅ ስላለበት ቢሆንም በዚህን ያህል ዋጋ ቤት መከራየት ተገቢ አለመሆኑን የሚገልጹም አሉ፡፡
እንደ ምንጮች ገለጻ ከሆነ ፕሬዚዳንቱ ከቤተ መንግሥት ሲወጡ ሊኖሩበት የሚችለውን ቤት ለማዘጋጀት የቤተ መንግሥት ጽሕፈት ቤት አምስት የተያዩ ቤቶችን በመምረጥ የተሻለ ነው ተብሎ የተመረጠው አሁን ውሉ እንዲቋረጥበት የተደረገው ቤት ነው ተብሏል፡፡
ከኃላፊነት የተነሱት የአገርና የመንግሥት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላትና ዳኞች የሚያገኙዋቸውን መብቶችና ጥቅሞች ለመወሰን የወጣው አዋጅ እንደሚደነግገውም ለተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ቤት እንደሚዘጋጅ ይጠቅሳል፡፡
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 4 መሠረት የመኖሪያ ቤት አገልግሎትን በተመለከተ የተጠቀሰው ከኃላፊነት የተነሳ …read more
Via: Ethiopian Reporter
No comments:
Post a Comment