Monday, September 30, 2013

የ‘ፍም እሳቶች’ እምቢ ባይነትና ጽናት የሚያኮራን ነው

ማን ነው የሚለየው? የሚደፍረው?
ይህም ትውልድ ፍም እሳት ነው።
የታለ አንድነቱ…. የፍቅር ተምሳሌቱ?
አረ ጎበዝ…..
እምቢ በል!
እምቢ…. እምቢ…እምቢ…..

የማደንቃቸው ሮቤል አባቢያ ዲሞክራሲ ከደጅ እያንኳኳ ነው በሚለው ጽሁፋቸው ዘመነኛ ቀስቃሽና ነገን አመላካች የሆኑ የዜማ ርዕሶችን እያደናነቁ የሀገራችንን ትንሳዔ ህልውና አብሳሪ የሆነውን ቀስተደመና መሰል ሰንደቅዓላማ ወጣቶች ከፍ አድርገው ስለማውለብለባቸው በውብ ብዕራቸው ከኛም አልፎ ሌሎች እንዲረዱት በእንግሊዝኛ አቅርበውት ነበር። ፕሮፌሰር አለማየሁም ይህንን ከሰጡት በላይ መልሶ ለመስጠት የተዘጋጀን አቦሸማኔ ወጣት ትውልድ አድንቀው ጽፈዋል። ልሂቃኑ ባሉት ላይ በማከል የሀገራችንን ትንሳዔ በወጣቶቻችን ለነፃነት ቀናዒነትና አልበገር ባይነት እናይ ዘንድ እውነት መሆኑን የሚያመለክት ከዘረኝነት በላይ፣ ከሀይማኖት ልዩነትም ያለፈ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች አጥርም የዘለለ ሀገራዊ አንድነቱን ከፍ ያደረገ ማንነትን ሲገልጹ ማየት እጅግ አኩሪ መሆኑን ደግሞ ደጋግሞ መናገር ያስደስታል።

አዛውንቱን አግልሎ ወጣቱን በሉ በሉ የሚል ወይም ወጣቱን አርክሶ ጀግና ድሮ ቀረ የሚል ዘመናትን አገናኝ የሆነውን ድልድይ አፍራሽና የትውልድን ቅብብሎሽ የሚያረክስ ሀሳብ ስሜታዊ በሆኑ ወገኖች እየተነገረ ሚዛናዊነት ሲጠፋ፣ ተስፋ ቆራጭነትም ሲስፋፋ ተመልክተን ነበር። ከወጣቶቹ አንዱ ቴዲ አፍሮ “ያለ ትናንት ዛሬ የለም።” እንዳለው መወራረስና መደጋገፍን ከፍ ማድረጉ አስፈላጊ ነው። ዛሬ ያለው እውነት ትናንት ሆኖ ባለፈው ድርጊት ላይ መሰረቱን ይጥላልና። ለዚህም ነው በትናንቱ ሁሉን አቀፍ ታሪካዊ ስህተት ተቀፍድደን፣ ዛሬን ሁሉን ነገር ተነጥቀን ላለማለፍ የትናንቱ ስህተት እንዳይደገም፣ ሸፍጥና መጠላለፍም የነገን ተስፋ እንዳያሳጣን አምቢ በል ለሚሉት ተረካቢ ወጣቶች እውቀትና ብልህነት በትግሉ ለሰነበቱ አዛውንቶችም ለብሄራዊ እርቅ ብርታትና ጥንካሬን መመኘት ተገቢ የሚሆነው።
የወጣት እድሜ ክልሉ እስከ 30 ከዘለቀ የዛሬዎቹ ወጣቶች በዚህ ምድር በተመላለሱበት ጊዜ ሁሉ ሀገራቸውን እንዲጠሉ፣ በሀገራቸውና በታሪካቸው እንዳይኮሩ የተገደዱና ሀገር ለዜጎችዋ ልትሰጥ የሚገባት ሁሉ ያልተሰጣቸው እንዲያውም ህልማቸው ስደት፣ ስኬታቸውን በግርድናና ባርነት እንዲለኩ የተገፉቱ ናቸው። የአምባገነኖች አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ፣ ጎሰኛነትንና ጥላቻን በሚያስፋፉ ቡድኖች ሁሉ በግድ ጥላቻን በጡጦ የተጋቱት ናቸው በወጣት ቅንፍ ውስጥ ያሉትና ሀገር ከተረፈችላቸው የነገዎቹ ተረካቢዎች የሚሆኑት። ሀያ ሁለት ዐመት በአዋጅና በተግባር የተደረገው የጥላቻ ዘመቻ ሁሉ ከሽፎ ክፋትን የዘሩ ቁንጮዎቹ የሰረቁትን እንኳን ሳይበሉ በጠሉት ባንዲራ ተጠቅለው አፈር ሲረግጣቸው ወጣቱ ግን በመቃብራቸው ላይ ቆሞ ስለሀገሩ ይዘምራል፣ ስለመብቱ ይታገላል፣ ስለነፃነቱም ባደባባይ ይሰለፋል ነፍጥ አንስቶም ይፋለማል። “ማን ነው የሚለየን?” የሚለው ዘመነኛ ዜማ በቀረርቶ ታጅቦ ሲንቆረቆር ወጣቱ …read more
Via: Zehabesha

No comments:

Post a Comment