Friday, September 27, 2013

አቶ ሬድዋን ኢትዮጵያና ቻይና በሚዲያ ዙሪያ በቅርበት እንዲሰሩ ጠየቁ

መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲሱ የኮምኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ከቻይና ከህዝብ የፖለቲካ ምክክር መድረክ ምክትል ሊቀመንበር ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያና ቻይና የመገናኛ ብዙሀንን በተመለከተ ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ሁለቱም ልማታዊ መንግስታት በመሆናቸው በመገናኛ ብዙሀን ረገድ የሚሰሩት ብዙ ስራዎች አሉዋቸው ያሉት አቶ ሬዲዋን፣ የቻይናን ብሄራዊ ቴሌቪዥንና የዢኖዋን እንቅስቃሴ አድንቀዋል።

ቻይና የመገናኛ ብዙሀንን በማፈን ከሚታወቁት አገራት መካከል አንዷ ናት።

No comments:

Post a Comment