Wednesday, September 25, 2013

የናይሮቢው ጥቃትና የኢትዮጵያ አቋም

2222
በኬኒያ ናይሮቢ ባለፈው ቅዳሜ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት ኣጥብቃ እንደምታወግዝ ኢትዮጵያ አስታወቀች የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቃል ኣቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ እንደሚሉት ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃትን ለመከላከል ከኬኒያ ጋር ተባብራ ትሰራለች የአፍሪካ ቀንድ
ሃገራትም በዚህ ረገድ ተባብረው
እንዲሠሩ ጥሪ ኣቅርባለች
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል ኣቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ከኒውዮርክ ለዶቸቬሌ
እንደገለጹት ኢትዮጵያ የኬኒያውን ጥቃት የሰማችው በጥልቅ ሃዘን ነው ማዘን
ብቻም ሳይሆን ኣሉ ኣቶ ጌታቸው ኢትዮጵያ የዚህ ኣይነቱን የሽብር ጥቃት
ለመከላከል የበኩልዋን ድጋፍ እንደምትሰጥም ለኬኒያ ኣረጋግጣለች።
ጥቃቱን በተመለከተም ከኣልሸባብ ዓይነቱ ኣሸባሪ ድርጅት የሚጠበቅ እንጂ
የሚገርም ሊሆን ኣይችልም ብለዋል አቶ ጌታቸው።

ኬኒያ ምን ኣይነት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባት መግለጹ የኬኒያውያን ፋንታ
ነው ያሉት አቶ ጌታቸው በኢትዮጵያ በኩል ግን መንግስት ይከተለዋል ያሉትን
የጥንቃቄ ስልቶች ለማስረዳት ሞክረዋል አልሸባብ ብቻም ሳይሆን ሌሎች ኣገር በቀል ድርጅቶችም ሲሞክሩት የነበረውየሽብር ጥቃቶች ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሽፈዋል ያሉት ቃል ኣቀባዩ ጥረቶቹ
እንዳሉ ግን ኣልሸሸጉም
ጃፈር ዓሊ
ሂሩት መለሰ
AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC

No comments:

Post a Comment