አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ መስከረም 19 ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 15 አባላቱ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው፡፡ አባላቱ ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው ጎዳና በመኪና ላይ እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት ሚኒሊክ ት/ቤት ፊትለፊት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የሚተላለፈውን መኪና መንገድ በመዝጋት ቅስቀሳውን አደናቅፈዋል፡፡
በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች “ቀስቃሾቹ ህጋዊ ወረቀት ይዘዋል፤ልቀቋቸው” በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል ከአንድነት ፓርቲ ጎን እንደሚቆሙም ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ 15 የሚሆኑትን የቅስቀሳ ቡድን አባላት ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አባላቱ ወደ ታሰሩበት 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ረ/ኢ መንግስቱ ለማ የተባሉትን የፖሊስ ጣቢያው ኃላፊ የታሰሩት አባላት እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡ ኃላፊውም “ህጋዊ ሰልፍ እንደምታደርጉ እናውቃለን ይቀስቅሱ የሚል መመሪያ አልደረሰንም ብለዋል፡፡ አመራሮቹ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነርንና የከተማዋን መስተዳድር ሃላፊዎች ለማነጋገር ተንቀሳቅሰዋል፡፡
በተለያየ አቅጣጫ የተሰማሩት ሌሎቹ የአንድነት ፓርቲ ቅስቀሳ ቡድን አባላት ስኬታማ የመኪና ላይ ቅስቀሳ በማደረግ ላይ ናቸው፡፡
በተያያዘም ዜና የአራት ኪሎ ነዋሪዎች እውቅና ተችሮታል የተባለን የአንድነት የመስከረም 19 ሰላማዊ ሰልፍ ህዝብ አሳታፊ ለማድረግ ዛሬ ማለዳ ከአንድነት ቢሮ በዛ ያሉ መኪኖች ለቅስቀሳ ወጥተዋል፡፡በአራት ኪሎና በአካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ለመቀስቀስ ከወጡ መኪኖች መካከል የተወሰኑት በፖሊስ በህገ ወጥ መንገድ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርገዋል፡፡
በመኪኖቹ ውስጥ የነበሩትን የአንድነት አባላት ፖሊስ ወደ ጣብያ ለመውሰድ ባደረገው ሙከራ ህዝብ መሰብሰብ ችሏል፡፡ሁኔታውን በአንክሮ ይከታተል የነበረ ህዝብ ፖሊሶቹን ልጆቹን መውሰድ አትችሉም፣ሰልፉ እንደተፈቀደ እየታወቀ መቀስቀስ አትችሉም ማለታችሁ ህገ ወጥ ድርጊት ነው››በማለት እጅግ በሚያስደስት ሁኔታ ተከራክረዋል፡፡
አዎን ህገ ወጥ ድርጊት ሲፈጸም በእኔ ላይ ካልሆነ ምን አገባኝ ብለን የምናልፍበት ዘመን ማብቃት ይኖርበታል ፡፡ይህንን ደግሞ የአራት ኪሎ ሰዎች ስለ ጀመሩት ከወዲሁ ምስጋናችን ይድረሳቸው፡፡
No comments:
Post a Comment