Tuesday, December 23, 2014

አሁን የተጀመረው ትብብር በአጭር ግዜ የሚከስም ሳይሆን ግቡን ውህደት አድርጎ መንቀሳቀስ የሚፈልግ ከሆነ አንድነትም …

አቶ በላይ ፍቃዱ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዘዳንት
አንድነት ትብብሩ ውስጥ የሚገባ ከሆነ በየደረጃው ክፍለ ሀገር ያለው መዋቅር አዲስ አበባ ያለው መዋቅር እስከላይ አመራር ድረስ ያለው መዋቅር ከሰማያዊ መዋቅር ጋር መዋሀድ አለበት ብለን ነው የምናምነው፡፡ስለዚህ እኔ ባህርዳር ሄጄ የአንድነት መዋቅር ፤የመኢአድ መዋቅር ወይም የአንድነት መዋቅር የሚባል አይደለም የሚያስፈልገው አንድ ወጥ መዋቅር ነው የሚያስፈልገው፡፡በዚህ አግባብ ከተስማማን ትብብሩን አንድነት ጆይን አድርጎት ለተሻለ ውጤት እንሰራለን፡፡አሁን የተጀመረው ትብብር በአጭር ግዜ የሚከስም ሳይሆን ግቡን ውህደት አድርጎ መንቀሳቀስ የሚፈልግ ከሆነ አንድነትም ተቀላቅሎ የተሸለ ስራ ይሰራል ብለን ነው የምናምነው፡፡

Belay Fekadu
አቶ በላይ ፍቃዱ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዘዳንት

No comments:

Post a Comment