Monday, December 22, 2014

“የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም” አዳም ረታ (መብትን መጠየቅ በረብሻ ሃራራ የማደግ ውጤት አይደለም)

adam reta

“. . . ፖለቲካ ለሀገር ማሰብ ነው፡፡ ፖለቲካ መታደል ከተጨመረበት ለአገርና ውስጥዋ ለሚኖረው ለሕዝብ መልካም ለመስራት መጣር ነው፡፡ ከራስ በላይ ነፋስ በሚባለው ነገር አላምንም፡፡ ከራስ በላይ ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ሰፈር፣ ወረዳ፣ አውራጃ ክፍለሀገርና አገር አሉ፡፡ የቻለበትም አህጉርና አለምን በልቦናው ይከታል፡፡
“የአገራችን አንድ የሚታይ ማንም የሚያወራበት ፀባይዋ በደሃና በተራራ የተሞላች መሆኗ ነው፡፡ አንድ ሰው በሀገሩ ደሃ መሆን የለበትም:: ቢያንስ መሰረታዊ ፍላጎቶቹና መብቶቹ መጠበቅ አለባቸው፡፡ የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም፡፡ የለፉበት ውጤት በጥቂት ማንአለብኝ ባዮች ስለሚዘረፍ ነው፡፡

“እነዚህም ዘራፊዎች ዝርፊያቸውን ያለሀሳብ ለማካሄድ ማስፈራራትንና ራሳቸው ያወጡትን ህግ ይጠቀማሉ፡፡ ድሆች ወይም ጭቁኖች መብታቸውን ለማስከበር የሚነሱት ከወደቁበት የድህነት አዘቅት ለመውጣት እንጂ በሀብታሞቹ ቀንተው አይደለም፡፡ ወይም በረብሻ ሃራራ ስላደጉ አይደለም፡፡” (ምንጭ: ከአዳም ረታ ፌስቡክ ገጽ)

No comments:

Post a Comment