Wednesday, December 24, 2014

ለመኢአዶች ያለኝ መልእክት – ግርማ ካሳ

መኢአድ (የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት) አንጋፋ ድርጅት ነው። ከመስራቹ ከፕሮፌሰር አስራት ጀመሮ የዚህ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች እጅግ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል። ብዙዎች ሞተዋል፤ ብዙዎች ታስረዋል። ከማንም ድርጅት ባልተናነሳ ገዢው ሙሸት አማረ በሚመራዉና በአቶ አበባው በሚመራው ቡድን መካከል ያሉ ልዩነቶች በአሁኑ ወቅት መኢአድ ትንች በተጠናከረ መልኩ ወደፊት እንዳይሄድ አድርጎታል።

የነዚህ ሁለት ቡድኖች ዉዝግብ ገና አልተፈታም። ሕጋዊዉ የመኢአድ አመራር የቱ እንደሆነ ገና አልታወቀም። ምርጫ ቦርድ ያሉ መረጃዎችን መርምሮ ዉሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። አንዳንድ ምንጮች እንደሚጠቁሙት ምርጫ ቦርድ ለአቶ አበባው መሐሪ እውቅና ሳይሰጥ እንደማይቀር ነው። ይህ ከሆነ የነ አቶ ማሙሸት ቡድን ምንድን ነው የሚሰማው የሚል ጥያቄ ብዙዎች ሊያነሱ ይችሉ ይሆናል።

ሁለቱም ቡድኖች ይነሰም ይብዛም ደግፊዎች አሏቸው። አንዱ ቡድን ተሸንፎ፣ ሌላው አሸናፊ የሆነበት መስመር ለመኢአድ አይጠቅም፣ ለትግሉም አይጠቅምም። ምርጫ ቦርድ እውቅና ለአቶ አበባው ቢሰጥም፣ አቶ አበባው የመኢአድ ሊቀመንበር ከመሆን ጋር ትልቅ ሃላፊነት ነው የሚይዙት። “ከምርጫ ቦርድ እውቅና አገኘው” ብለው “አሸነፍኩ” የሚሉበት ሁኔታ ሊኖር አይገባም። እርሳቸው “የፈለጉት ቢሆንላቸውም መኢአድ አላሸነፈም። ይልቅ፣ ከአንድ ዘመናዊ መሪ የሚጠበቅ ሥራ መስራት አለባቸው። ትሁት ሆነው፣ እነ አቶ አማረ ማሙሸትን በፍቅርና በይቅርታ ማሸነፍ መቻል አለባቸው።
እንደዉም የሚመረጠው ፣ አቶ አበባው ከአቶ ማሙሸት ጋር በመነጋገር፣ ማንም ሳይገባባቸው፣ እንደ መኢአድ ቤተሰቦች፣ ይቅር ተባብለው፣ በአገሪቷ በሙሉ ላሉ የመኢአድ አባላትና ደጋፊዎች የምስራች እንዲያበስሩ ነው። አቶ ማሙሸት የመኢአድ ም/ሊቀመነበር ሆነው፣ የሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴው ከሁለቱም ተወጣጥቶ ሥራ ቢጀመር ነገሮችን ሊያቀል ይችላል።
የመኢአድን መከፋፈልን እና የአንድነት ኃይሎች በጋራ አለመስራት የሚፈልጉ ኃይላት ለምንስ ደስ ይላቸዋል ? ለምን በኢቲቪ ወዘተረፈ መኢአድ መሳቂያ ይሆናል ? እንደ ፕሮፌሰር አስራት፣ ከግል ዝናና ስልጣን ይልቅ አገርን እና ሕዝብን አስቀድመን፣ በአንድነት የምንቀሳቀስበት ጊዜው አሁን ነው። መኢአድ ብዙ ሥራ ይጠበቀዋል ከፊቱ። መኢአዶች መንቃት አለባችሁ እላቸዋለሁ።
የአጼ ሚኒሊክ ወታደሮች ወላይታን ለማስገበር ሲሄዲ ትላ ሽንፈት አጋጠማቸው። አጼ ሚኒሊክ ራሳቸው አዝማች ሆነው ነው ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ጦርነት ተደረጎ፣ ንጉስ ጦና የተማረኩት። አጼ ሚኒሊክ ብዙ ወታደር ሞቶባቸዋል። ሆኖም ንጉስ ጦናን መልሰው ሾሟቸው። ንጉስ ጦና ቢሸነፉም አሸነፉ። ንጉስ ጦና ከዚያን ጊዜ በኋላ ከአጼ ሚኒሊክ ጋር ወዳጅ እንደሆኑ ከታሪክ አንብቢያለሁ። አገር የምታሸንፈው አንዱ ወገን ተሸንፎ ሌላው ሲሸነፍ ሳይሆን፣ ሁሉም ሲያሸንፉ ነው። የመኢአድ አመራሮች ከአጼ ሚኒሊክ ይማሩ እላለሁ።
(በነገራችን ላይ ምርጫ ቦርድ እውቅና ለአቶ አማረ ማሙሸት ከሰጠ ደግሞ ፣ አቶ አበባ በሚለው ቦታ ለአቶ አበባው የጻፍኩት ለአቶ ማሙሸት ይሆናል)

No comments:

Post a Comment