Tuesday, December 16, 2014

ሕዝባዊ ዕንቢተኝነት ለኢትዮጵያ ትንሳኤ!

ነብዩ ኃይሉ
ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም ዘጠኝ ፓርቲዎች ያቋቋሙት ትብብር የጠራው የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ፣ በገዢው ቡድን ውንብድና ከተስተጓጎለ በኋላ ስለሰላማዊ ትግል አይረቤነት የተለያዩ አስተያየቶች በመሰጠት ላይ ናቸው፡፡ የተወኑት አስተያየቶች “ትግሉ አልጋ በአልጋ መሆን አለበት” ከሚል የዋህ ልቡና የመነጩ የተስፋ መቁረጥ ስሜቶች ቢሆኑም፤ ጥቂት የማይባሉት ግን የህብረተሰቡን ቀልብ ከሰላማዊ ትግል አውድ ለማፋለስ ታቅደው የሚሰነዘሩ ይመስላሉ፡፡
Tensaye
በመሰረተ-ሀሳብ ደረጃ የትኛውንም የአገዛዝ ስርዓት ለመጣል የሚደረግ ትግል በአንድ ወጥ ቀኖናዊ የትግል ስልት ላይ ብቻ መመስረት ይገባዋል የሚል ድምዳሜ መስጠት አይቻልም፡፡ ሆኖም ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የትኛው የትግል ስልት ያዋጣል የሚለውን በኃላፊነት ስሜት የመምረጡ ተግባር ለታጋዩ የሚሰጥ ነው፡፡ በየትኛውም መለኪያ በትግል ላይ የሚፈጠር እንቅፋት ሁሉ ስልቱን ጥያቄ ምልክት ውስጥ ሊከት ግን አይችልም፡፡

ዓለም-አቀፍ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት የአገዛዝ ስርዓት የሚወገድባቸው በርካታ መንገዶች አሉ፡፡ከሚያስከፍሉት መስዋዕትነት አንፃርም በደረጃ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው የትጥቅ ትግል ነው፡፡ የትጥቅ ትግል መጠነ-ሰፊ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት የሚያስከትል ከመሆኑም በላይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማንበር እጅግ ፈታኝ ነው፡፡ በሰላማዊ ትግል ላይ የረጅም አመታት ጥናት ያደረጉትና በቅርቡ “ሰላማዊ ትግል 101” በሚል ርዕስ መጽሀፋቸውን ያሳተሙት አቶ ግርማ ሞገስ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ከጦርነት ጋር የተጋመደ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ “ሀገራችን በስልጣኔ እንዳትገሰግስ ደንቃራ የሆነባት አገዛዞችን በጦር ሀይል ለማስወገድ የሚደረጉ የእርስ በርስ ጦርነቶች ናቸው” ሲሉም ይሞግታሉ፡፡
“ለዘጠኝ መቶ አመታት ላላነሰ ጊዜ ኢትዮጵያ በዘመናዊ (Secular) ትምህርት፤ ትምህርቱን ተከትሎ ለሚመጣ ዘመናዊነት እና ስልጣኔ ጀርባዋን መስጠቷ ለኋላ መቅረቷ አንዱ አውራ ምክንያት እንደነበር ከላይ ለመግለፅ ተሞክሯል፡ ፡በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ደግሞ ቢያንስ ቢያንስ ከአክሱም ስልጣኔ መውደቅ በኋላ አምባገነኑ ህወሓት/ ኢህአዴግ በ1983 ዓ.ም ስልጣን እስከጨበጠበት 1983 ዓ.ም ድረስ የእርስ በርስ ጦርነት (ትጥቅ ትግል) አካሂዶ ስልጣን መያዝ ጀግና የሚያሰኝ ባህል ነበር/ነው፡፡ ነፍጥንና ጉልበትን መሰረት ያደረገው የመንግስት ሽግግር ባህሏ ኢትዮጵያን እጅ እና እግሯን ተብትቦ ስለስልጣኔ የምታስብበት መተንፈሻ ጊዜ እንኳን እንዳይኖራት
አድርጓት
ሞገስ፡ ትግል101”
ነበር።
ግርማ “ሰላማዊ 2006፡33-34
ሌላው የትጥቅ ትግል ደካማ ጐን፣ ትግሉ በሶስተኛ ወገን ጣልቃ-ገብነት ጭምር የሚወሰን መሆኑ ነው፡ ፡ በዘመናዊው የኢትዮጵያ ታሪክ እንደተመለከትነው ከሀገራችን ጋር መሠረታዊ የጥቅም ባላንጣነት ያላቸው ጐረቤት ሀገራት ለደፈጣ ተዋጊዎች ድጋፍ እንደሚሰጡ ተመልክተናል፡፡ አገራቱ የደፈጣ ተዋጊዎቹን የሚረዱት ኢትዮጵያን ከአገዛዝ ስርዓት ለማላቀቅ ሳይሆን፣ አማፅያኑ የመንግስትነት መንበር ሲይዙ የመንግስታቸውን ጥቅም ማስከበር ነው፡፡
ሌላው የአገዛዝ ስርዓቶች የሚወገዱበት መንገድ መፈንቅለ-መንግስት ነው፡ ፡ መፈንቅለ መንግስት፣ የጥቂት ባለስልጣናትና የጦር መሪዎችን ለስልጣን ከማብቃት ባለፈ ህዝብን የስልጣን ባለቤት በማድረግ አገዛዝን ሲያስወግድ አይታይም፡፡ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት ሲተገበር እንዳስተዋልነውም፤ መፈንቅለ መንግስት የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት ነው፡፡ በቅርቡ ነፃነቷን ያገኘችው ደቡብ ሱዳን አሁን ያለችበትን ምስቅልቅል መመልከቱ የመፈንቅ ለመንግስትን አደገኝነት የሚያመላክት ነው፡፡ በውጤቱም ሆነ በሂደቱ አምባገነንን በሌላ አምባገነን ከመተካት አንፃርም ከትጥቅ ትግል የተለየ አይደለም፡፡ የበርካታ ሀገራት ዜጐች የስልጣናቸው ባለቤት የሆኑት ከላይ በተጠቀሱት ሁለት መንገዶች ሳይሆን በሀይል አልባ ህዝባዊ እንቢተኝነት ነው፡፡
የህዝባዊ እንቢተኝነት የትግል ስልት፣ ከክርስቶስ ልደት በፊት በጥንታዊያኑ ግሪክና ቻይና እንደተተገበረ የዘገቡ የታሪክ ድርሳናት ቢኖሩም፣ በይበልጥ ያስተዋወቀው ግን ህንዳዊው የነፃነት ታጋይ ማህተማ ጋንዲ ነው፡ ፡ የጋንዲ የህዝባዊ እንቢተኝነት አስተምህሮ፣ በሂንዱ ቋንቋ Sanskrit ahimṣṣ በመባል ይታወቃል፤ አስተምህሮው በትግል ሂደት ውስጥ በራስም ሆነ በሌሎች ላይ በየትኛውም ሁኔታ ጉዳት እንዳይደርስ የሚያስችል ነው፡፡ የትግል ስልቱ ሰላማዊነት የሚንፀባረቀው ሞራላዊ፣ ሀይማኖታዊና መንፈሳዊ ዕሴቶችን የያዘና አንድን ውጤት ለማምጣት በሰው፣ በእንስሳትም ሆነ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ የሚያደርስ መሆን እንደሌለበት ያስተምራል፡፡ ህዝባዊ እንቢተኝነት ሀይል አልባ መሆኑም የአገዛዝ ስርአትን ለማስወገድ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ውሱን ያደርገዋል፡፡ ህዝባዊ እንቢተኝነት በጥናትና በዕቅድ የሚከወን ነው፡፡ ባልተቀናጀና ግብታዊ በሆነ መንገድ የሚደረግ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ግን ህዝብን ሽንፈት ከማለማመድ ባለፈ ህዝባዊ እንቢተኝነትን ይወልዳል ብሎ መጠበቅ አላዋቂት ነው፡፡
ያልተጠኑ፣ በግብታዊነትና በተናጥል የሚደረጉ ያልተሳኩ የተቃውሞ ትዕይንቶች በህዝቡ ውስጥ ሽንፈትን የሚጠሩ ናቸው፡፡ ህዝባዊ እንቢተኝነት፣ ከአነስተኛ የተቃውሞ ትዕይንት ወደ “ምድር አንቀጥቅጥ” የተቃውሞ ትዕይንትነት የሚያድግ እንደመሆኑ መጠን ከጅምሩ የሚደረጉ ተቃውሞዎች የተጠኑና ታቅደው የሚደረጉ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ለራስ የሚሰጡ የተጋነኑ ወይም የተንኳሰሱ ግምቶችም ሆነ ለተቀናቃኝ የሚሰጡ የተጋነኑ አሊያም የተንኳሰሱ ግምቶች የሚፈጠሩት ጥናትና እቅድ ላይ የተመሰረቱ እንቅስቃሴዎች ባለመደረጋቸው ሳቢያ ነው፡፡ ባሳለፍናቸው ጥቂት አመታት እንኳን የተደረጉ የተቃውሞ ትዕይንቶችን ብንፈትሽ፣ የምናገኘው ውጤት አብዛኞቹ በተጠና እና በታቀደ ሁናቴ የተከወኑ እንዳልሆኑ እንረዳለን፡፡ ማንኛውም ተግባር አመቺ ጊዜ ይፈልጋል፤ ጥሩ የሚባል ጥናት የተሰራለትን አንድን ተግባር ውጤታማ እንቅስቃሴዎች ውሱኑንት ታይቶባቸዋል፡ ፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎቹ ውጤትን ሊያመጡ እንዲችሉ ተደርገው ያተጠኑና አመቺ ጊዜ ተመርጦላቸው ያልታቀዱ በመሆናቸው ግብታዊነት የሚስተዋልባቸው ሆነዋል፡፡
ሌላው ሊነቀፍ የሚገባውና ህዝቡን ሽንፈት የሚያለማምደው የተቃውሞ እንቅስቃሴዎቹ የተናጠል መሆናቸው ነው፡፡ ህዝባዊ እንቢተኝነትን ያመጡ፣ በሂደትም ለውጥን ያበሰሩ እንቅስቃሴዎች ሁሉ የህዝቡን ትኩረት ያገኙት፣ ሁሉንም ህዝብ በአንድ የጋራ ተተኳሪ ነጥብ ላይ ያሰባሰቡ በመሆናቸው ነው፡፡ በሀገራችን የተደረጉና እየተደረጉ ያሉት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ግን የህዝቡን የለውጥ ፍላጐት እውን እንዲሆን፣ ወደአንድ የትኩረት ነጥብ የሚስቡ ለመሆን አልቻሉም፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት የተናጠል የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው ዋነኛው ምክንያት ነው፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆኑ ይፋዊ ያልሆኑት የቡድን መብት አራማጅ ስብስቦች፤ እንቅስቃሴያቸውን ወደአንድ የትኩረት ነጥብ እንዲወስዱ ይጠበቅባቸዋል፡፡ይህ መደረጉ በተቃውሞ ትዕይንቶቹ ላይ የሚገኘውን ተሳታፊ ቁጥር ከፍ እንዲል የሚያደርግ በመሆኑ፣ አገዛዙን የሚያንበረክክ ይሆናል፡፡ በየትኛውም መለኪያ ተፅዕኖ ከቁጥር ጋር ያለውን ትስስር ማስቀረት ስለማይቻል፣ የተናጥል እንቅስቃሴዎችን ማሰባሰብ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ግዙፍ ውሱንነቶች፣ የነፃነት ትግሉን እጅ ከወርች ያሰሩ ከመሆናቸውም በላይ በህዝቡ ውስጥ የሽንፈት ስሜትን የሚዘሩ ናቸው፡፡ በተቃውሞ ትዕይንቶች ላይ የሚታየው አነስተኛ የሰው ቁጥር ለውጥን ሊያመጣ የሚችል የሀይል ሚዛን ተቃዋሚዎች ጋር እንዳለ ዋስትና ስለማይሰጥ፤ ህዝቡን ለተስፋ መቁረጥ አሳልፎ እንደሚሰጥ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡
የያዝነው አመት ምርጫ የሚካሄድበት እንደመሆኑ ዘጠኙ ፓርቲዎች ምርጫው ፍትሀዊ እንዲሆን በመጠየቅ ሊያካሂዱት የነበረውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ፣ ጭካኔን በቀላቀለ ሁኔታ እንዲደናቀፍ መደረጉ ገዢው ቡድን ለሰላማዊ የስልጣን ሽግግር አሁንም አለመዘጋጀቱን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህን በዕብሪት የተወጠረ፣ በመሳሪያውና በሰራዊቱ ብዛት የሚመካ ቡድንን ለማስወገድ ተመጣጣኝ አቅም መገንባት የግድ ይላል፡፡ ገዢው ቡድን የያዘው መሳሪያና የሰራዊት ብዛት ከኢትዮጵያ ህዝብ አቅም ጋር ሊወዳደር አይችልም፤ ይህን የግብፅ፣ የቱኒዝያ፣ የዩክሬንና ሌሎች በህዝባዊ ዕምቢተኝነት ግብአተ-መሬታቸው የተፈፀሙ አንባገነኖች ታሪክ ይመሰክራል፡፡

No comments:

Post a Comment