Wednesday, April 23, 2014

ምክር ለሰማያዊ ፓርቲ

በክፍያለው ገብረመድኅን
የተነጠቁ መብቶቻችን እናስመልስ” በሚል መሪ ዓላማ ስማያዊ ፓርቲ ያደረገው ጥሪ የተከበረ ግብ ቢሆንም፤ ውጥንቅጥና ውስብስብ በሆነው፡ ሕወሃት በፈንጂ ባጠረው የተግል ጎዳና የሰማያዊ ፓርቲ ብቸኛ ጉዞ መምረጡን በክፍተኛ ኃዘንና ቅሬታ እንድመለከተው ተገድጃለሁ።demonstration in Addis Ababa

ጥያቄው ሰማያዊ ፓርቲን የመቀበልና አለመቀበል ጉዳይ መደረግ የለበትም። መግለጽም ካስፈለገ፡ ለሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አድናቆት አለኝ። ይህንንም በተደጋጋሚ በዚህ ድህረ ገጽ ላይ አስረግጬ መስክሪያለሁ።

በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ክትትል ለረዥም ዓመታት የቆየሁ ሰው በመሆኔ፡ ድጋፌ የተመሠረተው በድርጊቶቻቸው ላይ ነው። ከዓመታት በኋላ፡ ባለፈው ስኔ ወር ሳይታስብ የመጀመሪያው ሰላማዊ ሠልፍ አንቀሳቃሽ ሆነው ከወጡ በኋላ ለሰማያዊ ፓርቲ፡ ለፓርቲው ሊቀመንበርና በተለይም ለወጣት አባሎቹ ያለኝ አድናቆት ክፍተኛ ነው።
ፓርቲው ይህንን አድናቆቴን በተግባሩ ፈንቅሎ ነው የወስደው። በመደዳ በተመለክትኩት ድርጊቱ፡ ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ የቅርብ ዘመን ትግል፡ እንደነበልባል ሆኖ ቀርቧል። ከዚያን ጊዜ ወዲህም፡ በሀገራችን የተለያዩ ክፍሎች በሕወሃት/ኢሕአዴግ ላይ የሕዝቡ ቁጣም፡ ከዕለት ዕለት ኮስተር እያለ እንዲመጣ አደፋፍሯል – ምንም እንኳ ይህ ሁሉ የሰማያዊ ፓርቲ ብቸኛ ጥረት ውጤት ነው ለማለት ባልችልም።
ከሰማያዊ ፓርቲ ዓላማ ጋር ተዛማጅ የሆነውን ወገን ሁሉ አድሰዋል። በተጨማሪም፡ ሰማያዊ ፓርቲ ይዞት የመጣው ኃይል፡ ሌሎቹንም የፖለቲካ ድርጅቶች – በተለይም አንድነት – ይበልጥ እንዲንቀሳቀሱ፡ ብርታት ሆኗቸዋል። በዚህም ምክንያት – ከብዙ ጠላቶቹ ይልቅ – ሕወሃት ሶስት ነገሮችን አበክሮ እንደሚፈራ በተደጋጋሚ አሳይቷል – አንደኛ፡ ኢሳትን፤ ሁለተኛ የኢትዮጵያውያን እስላሞችን የመብት ጥያቄ፡ ሶስተኛ ስማያዊ ፓርቲን ነው!
ይህ ማለት ግን በሰማያዊ ፓርቲና በአንድነት መካከል ትብብር አለ ማለት አይደልም። እንዲያውም ከጎሪጥ መተያየት አልፈው፡ ግንኙነታቸው በሁለቱ መካክል ትግል ያለ እየመሰለ መጥቷል።
እኔ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ/እንቅስቃሴ አባል አይደለሁም። ጥሩ የሚሰሩትንና ሕዝቡን የሚያንቀሳቅሱትን ሁሉ እደግፋለሁ። የዚህ እምነቴ መሠረትም፡ የሕወሃትና ተላላኪዎቹ ዓላማ ዘረፋ፡ የመብት ረገጣዎችና የሃገር ጥፋት ነው ብዬ ሰለማምን ነው። የሕዝቡም ተሳትፎ እይጎላ ይሄዳል ብዬ እጠብቅ ነበር። ነገር ግን ይህ ከመሆን ይልቅ፡ የሃገራችን አመራር በጥቂት ግለስቦች ታፍኖና በመሣሪይ ኃይል ተረግጦ፡ የፓሊሲዎች አተረጓጎምና አሠራር በሁሉም መልኩ ወደ ቡድን ጠባብነት አዝቅጧል።
ለምን የዚህ ዐይነት አስተሳስብ ኖረኝ?
አንደኛ፡ ኢትዮጵያ ልትቀየር (transformed) ልትሆን ትቻላለች ብዬ እስክ 2005 ድረስ አምን ነበር። እስከቅርብ ጊዜ ድረስም፡ Transforming Ethiopia ድህረ ገጽ ነበረኝ። ዓላማውም ዕድገትና ልማት ተኮር፡ በዚያ ዙርያ ይታዩ የነበሩና አሁንም ያሉ የውስጥም ሆነ የውጭ ችግሮች ላይ (land grab, capital flight, human rights violations, macroeconomic problems, etc.) የሚያተኩር ሆኖ፤ “መንግሥትም” ጥሩ ሲሠራ፡ ጥሩውን ይቀበል የነበረ እንዲሁም መጥፎውን የረገመ ነበር።
ነገር ግን የ2005 ጭፍጨፋ ቁርሾ ሳይጠፋ፡ እስራቱ፡ ግርፋቱ፡ ግድያው አሁንም ተጠናክሮ በመቀጠሉ፡ ምንም የዲምክራሲያዊ ለውጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ይመጣል የሚል እምነት አሳጥቶኛል። እንዲያውም ከዕለት ዕለት – እስከዛሬ ድረስ – አመራር በጉልበት፡ ማታለልና ዘረፋ ላይ ምስረታው ሲጠናከር፡ ሃገራችንና ዚጎቻችን በምንም መንገድ ከሕወሃት ወንበዴዎች ምንም በጎ ነገር መጠበቅ እንደማይገባቸው የማምንበት ደረጃ ከደረስኩ ስንበት ብያለሁ።
በዚህም ምክንያት የድህረ ገጼ ስምም ወደ The Ethiopia Observatory ክተለወጠ የመጀመሪይ ዓመቱን በዚህ ወር ድፍኗል። ዓላማውም እንዳለፈው ሁል፡ ለሃገር ልማት ቅድሚያ ይሰጣል። ከበፊቱ በተሻለ መንገድ ግን አሁንም ትኩረቱ ፖሊሲ ላይ ቢሆንም፡ ማናቸውንም የጥፋት፡ ዘረፋ፡ የሃገር ክህደትና፡ ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ በደሎች፡ ችግሮችና ድርጊቶች ላይ ያተኩራል። ይመዘግባል።
ሁለተኛ፡ ሕወሃት ዘረኛ ድርጅት ነው። በአማሮችና ኦሮሞች በግንባር ቀደምነት የሚፈጸመው የረቀቀ የማፈራረስ፡ የመስበርና የመበታተን ድርጊቶች ተጠናክረው በመቀጠላቸው (systematic destruction) ዚጎች ኅብረታቸውን በማጠናከር ሊታገሉት የሚገባ አገር አፍራሽ ድርጅት መሆኑን ያለአንዳች ጥርጥር ወደምናምንበት ደረጃ መሽጋገር ስለሚያፈልግ፡ ይህንን ጥረት የሚያግዝ ሥራ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሥራት አስፈላጊ ሆኖአል። ይህን የምተርከው፡ አንተ ምነው ከሰማያዊ ፓርቲና ሌሎቹም ተቀባይ ብቻ ሆንክ የሚለውን ጥያቄ ከወዲሁ ለመገደብ ነው።
ታዲያ በዚህ ሁኔታ ውስጥ፡ እኔ የወደድኩት ስማያዊ ፓርቲ እንደተኩላ የብቸኛ ታጋይነትን ጎዳና ማፍቀሩን ሳይ፡ የዛሬውን ችግር ብቻ ሳይሆን፡ ለነገውም ሥጋት አሳድሮብኛል።
ምን ማለቴ ነው?
ለምሳሌ፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር፡ ለምድንነው ሚያዝያ 19 የተቃውሞ ስልፍ ለብቻው የጠራው? እስከዛሬ ሌሎች በሜጠሩትስ ሠልፍና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ለምንድነው ተባባሪ የማይሆነው? ይህ ጥያቄ ገለልተኛ (neutral) ነው – ማለትም ጥፋቱ የስማያዊ ፓርቲ ብቻ ነው የሚል ፍርድ የማስተላለፍ ዓላማ የለውም።
እኔ አንድነትና ስማያዊ ፓርቲ ለምን አትዋሃዱም የሚል ጥያቄ ዛሬም፡ ነገም ተነጎዲያም አላነሳም። እንዲያውም እንደድርጅት ራሳችሁን በየፊናችሁ ችላችሁ -ሕዝቡን በማስተባበር፡ የአንድ አፍራሽ ኃይልንጭቆናና ዘረፋ ለማቆምና ሕዝብን ከባርነትና ድህነት ለማላቀቅ ሃገርን ወደ ዲሞክራሲያዊ ጎዳና ለማድረስ፡ በጋራ ጥረታችሁንና ጉልበታችሁን አስተባብራችሁ ለአንድ ዓላማ የምትታገሉ መሆናችሁን ማየት ራሱን የቻለ ክፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብዬ አምናለሁ።
ተመሳሳይ ቅሬታ ተሰምቶኝ የነበረው፡ አንዲ ጊዜ ኢንጂነር ይልቃል፡ ሕገ መንግሥት ማስረቀቁን ሰሰማ ነበር። ይህም ተስፈንጣሪነትና የድርጅቱ አመራሮች ለብቸኛ ሥልጣን የቸኮሉ አስመስሏቸው ነበር።
እነዚህ የሚታትዩት ችግሮች ከዕድገት ጋር የሚመጡ ናቸው፡ ፈረንጆች Growing pains የሚሏቸው ሊሆኑ ይችላሉ። የጎረምሳ ወላጆች ስለሆን – ባንሆንም ደግሞ የጓደኞች ልጆች ስለምናይ ወንድሞችና እህቶች ሳላሉን – እነዚህን ችግሮች እንገነዘባለን። አሳሳቢውና አስፈሪው ነገር ግን፡ የሰማያዊ ፓርቲ የጎርምሳና የኤሊት ፓርቲ (elitist) የመሆን እርሾ ይጎዳው ይሆን ብዪ ማሰቤም አልቀረም። ችግሩ እሱ ከሆነ ግን፡ አደገኛ አዝማሚያ ሊሆን ስለሚችል፡ ከወዲሁ ሊታረም የሚገባ ይመስለኛል!
ምክር ከተሰጠ በኋላ፡ ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ትብብርና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመሥራት አለመቻሉን ብታዘብ፡ እንደ አንድ ተራ ገለስብ፡ ግለስባዊ ፊቴን ከፓርቲው ለማዞር እገደዳለሁ!

No comments:

Post a Comment