Tuesday, November 19, 2013

ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም …

ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም …

እስስቱ መንግስቴ በባለፋው ሰሞን ጣልያናዊ…..ዛሬ ደግሞ ሳኡድ አረቢያዊ ሆኖ አገኘሁት፡፡ ዛሬ እጅግ ለአዕምሮ ከባድ የሆነ ነገር በገዥው መንግስት ተፈጸመብን…ሳኡድ አረቢያ ያሉት ወገኖቼ በባዕድ ሀገር…እኛ በሀገራችን እንባችን ፈሰሰ፡፡ ግን መቼ ኢትዬጵያዊ መሪ እንደሚኖረን ሳስብ ይጨንቀኛል፡፡ ነገሩ እንደዚ ነው ሰሞኑን በ ሳውዲ አረቢያ መንግስት በኢትዬጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና ሰቆቃ ይብቃ፤ የዜጎቻችን እንግልት በዛ ልንል በ ሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት አርብ 5፡30 ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው ሳውዲ ኤምባሲ ተቀጣጠርን፡፡ 

ሰማያዊ ፓርቲ ዝግጅቱን የጀመረው 3 ተከታታይ ቀናት የሀዘን ቀን በማወጅ የህሊና ፀሎት አድርጎ ጊቢው ውሰጥ አንዳንድ ለሰልፉ የሚስፈልጉን ነገሮቸ ስናዘጋጅ ቆይተን ወዳ ሰልፉ ልንሄድ ትንሽ ሲቀረን 3የአዲስ አበባ ፖሊሶች ወዳ ጊቤያችን ብቅ በማለት የት ልትሄዱ ነው፣ለምን ጥቁር ለበሳችሁ፣ ዛሬ ምን አላችሁ እያሉ መጠየቅ ጀመሩ እኛም ወገኖቻችን በሳዉዲ እየደረሰባቸው ስላላው ግፍ በቃ ለማለት ሳኡዲ ኢምባሲ ተቃውሞዋችንን እናሰማለን አልናቸው ከዚ ግቢ አትወጡም ብለው ከባላይ አለቆቻቸው ጋር የስልክ መልክት እየተለዋወጡ ባሉበት ጊዜ ተበታትነን ወዳ ሰልፉ ቦታ ለመሄድ ወሰንን፡፡
ከዛም በታለያ አቅጣጫ ወዳ ወሎ ሰፋር እያቀናን ነበረ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ ም/ሊቀ መንበሩ አቶ ስለሺ ፈይሣ ፣የህዝብ ግንኙነቱ ብርሀኑ ተክለያሬድ ፣የወጣቶች ጉደይ ሀላፊ አቶ ዬናታን እና በርካታ የፓርቲው አባላት 4 ኪሎ ስላሴ ቤተክህርስቲያን ላይ እንደተያዙ የሰማን እነሱ ያሉበትን በስልክ ማግኘት እሰከምንችልበት ሰአት ድረስ ያለውን መረጃ እየተከታተል እኛ ወደ ሳውዲ ኢምባሲ ሄድን እንደደረስን በጣም ለቁጥር የሚከብድ አትዮጵያውያን ጥቁር ልብስ ለብሰው ጥግጥጉን ቆመዋል እኔ በጣም ደስ አለኝ አብዛኞቹ ጥቁር ያላበሱ ወጣቶች የኢትዬጵያ ብሄራዊ ቡድን ቲሸርት ለብሰው የነበረ ሲሆን ተሰባስበን ድምፃችንን ማሰማት ጀመርን፡፡
ሁኔታው ብጣም ልብ የሚሰብር ነበረ በጣም ብዙ እናቶች ልጆቻችን እያሉ ያለቅሱ ነበረ ሁሉም ሰው መጮህ ጀምሯል ..ዜጎቻችንን…ወገኖቻችንን… ብቻ በጣም ብዙ እየጮህን ፌደራል ፖሊሶች ተበታተኑ….ዝምበሉ …ምን ጎደለባችሁ..ምናቸሁ ተነካ እያሉ ሰልፉን ለመበተን ጥረት አያደረጉ ብዙም ሳይቆይ መገፍተር ሲጃምሩ ግማሾቻችን መውዳቅ ጀመርን..ጋደኞቻችን አነሱን በህግ አምላክ እያልን መጮህ ጀመርን.. መንግስት የለም ወይ አያልንም አዎ ብለው ነው መሰል ህዝቡን መዳብዳብ ጀመሩ አካባቢው በሀዘን ተውጣል ..ሴቶች…እየየ እሉ ያለቅሳሉ ሰሚ ያጣን የኢትዮጵያ ወጣቶች በ ሀገራችን እያተዳበዳበን ነው ህዝቡ እየሮጠ..ፌደራል ፖሊስ እያባረረ መደብዳብ ጀመሩ፡፡
በዚህ መሀል ግን የፓርቲው የፋይናንስ ሀላፊ አቶ ወረታው ዋሴ፣ የድረጅት ጉዳይ ሃላፊው ኢ/ር ጌታነህ ባልቻ እና ወደ 70 አካባቢ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት ከበቡዋቸውና ሁለቱ አመራሮች ላይ ላይን የሚከብድ ድብዳባ አደረሱባቸው፡፡ በጣም በ መንግስቴ አፈርኩ፡፡ እሰካሁን በዛ በጫካ ህጉ እንዳሚመራ አመንኩ፡፡ ኢትዮጵያዊ መንግስት ኢትዮጵያውያን እንደሌለን አረጋገጥን፡፡
በዚ መሀል እኔን ያዙኝ እና ለ 3 መዳብዳብ ጀመሩ 2ቱ በዱላ ሲሆን አንዱ ቆሞ ያያል…አንድ ትልቅ ሰውዬ በ ሴት ልጅ አምላክ..አሁን ይቺ ልጅ ምን ታዳርጋለች ብላችሁ ነው እንደዚ ምታዳርጓት..በ ህግ አምላክ እያለ ሲጮህ ይሰማኛል፤ እኔ ወንጀለኛ ከሆንኩ ለህግ አቅርቡኝ ልዳበድቡኝ መብት የላችሁም እያልኩ እጮህ ነበረ ግነ ጭራሽ አይሰሙኝም…በሏት ይቺ ነች አንዷ ሰልፉን ስትመራ የነበረ..ምን የምታጪ መሰለሽ ..ዝም በይ ይሉ ነበረ አብዝተው እግሬ አካባቢ ዳበደቡኝ..በጣም ብዙ ነገር ይሉ ነበረ..ከመሀል አንድ ኮማንዳር ፖሊስ እሷን ልቀቋት አላቸውና ተውኝ ያየኝ ሰው ሁሉ ምተርፍ አልመሰለውም….ጥለውኝ ሲሄዱ ጓዳኛዬ እያስፔድ ድጋሚ ሊደባድቡን በመጡ ጊዜ እኔ መሄድ አቅቶኝ ተሸክሞኝ እሮጠ..ሚገርመው እሱንም የደበደቡት ሲሆን የሱን ህመም ችሎ ነው ለኔ ያን ሁሉ እርዳታ ሲያደርግልኝ የነበረ ከቶ እንደዚ አይነት ፍቅር የት ይገኛል..ይሄው እኔ ግን ሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ አገኘሁት፡፡
አካባቢው ጥቁር በለበሱ ሰዎቸ ተሞልቷል ነዋሪው የተጎዳውን ሰው በመርዳት፣ ህዝቡ በማዘን ፣ ወጣቱ ዛሬስ ትንሽ ሆነን እንደዚ አደረጋችሁን ..ነገ ኳስ ላይ ምን እንደምታደርጉን እናይ የለ በማለት በንዴት እየፎከ ተበታተነ፡፡አመራሮችን እና ወደ70 አካባቢ ሚሆኑትን ወጣቶች አስረዋቸው ማታ ልናያቸው በሄድን ጌዜ አብዛኞቹን ለቀው ወደ 15 ሰዎች አካባቢ ቀርተዋል፡፡ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊው ኢ/ር ጌታነህና የፋይናንስ ጉዳይ ሀላፊው አቶ ወረታው በጣም እንደተጎዱ አየሁ ሌሎቹ ከሞላ ጎደል ደና ናችው፡፡ሁልጊዜም ግን ከፊት ቀድመው የሚመሩን፣ከህዝብ በፊት የሚደበደቡልን፣የሚታሰሩልን፣ተተኪ ለማፍራት የሚጥሩትን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን አመስግኘ ለዛሬው በዚሁ ልሰናበት፡፡
አትዬጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
በ ወይንሸት ሞላ

No comments:

Post a Comment