Wednesday, November 13, 2013

የኢትዮጵያ መንግስት በሳዑዲ አረቢያ እየተፈጸመ ያለውን ግድያን አስመልክቶ በአ.አ ሰልፍ መውጣትን አልደግፍም አለ

“በዜጎቻችን ጉዳይ ከማንም ጋር አንደራደርም” – ሰማያዊ ፓርቲም
‹ከእናንተ በፊትም ሌሎች ዜጎች ደብዳቤ ይዘው መጥተው ተከልክለዋል ስለዚህ ለእናንተም አይቻልም›አቶ ማርቆስ ብዙነህ
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ደብዳቤውን አቶ ማርቆስ ቢሮ አስቀምጠው ወጥተዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ አርብ ከ5.30 ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ በር ላይ የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ ዛሬ ጠዋት 4 የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ ለማስገባት የሄዱ ቢሆንም ደብዳቤውን የተቀበሏቸው የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ኦፊሰር አቶ ማርቆስ ብዙነህ ‹ከእናንተ በፊትም ሌሎች ዜጎች ደብዳቤ ይዘው መጥተው ተከልክለዋል ስለዚህ ለእናንተም አይቻልም›በማለት ላለመቀበል ቢያንገራገሩም አመራሮቹ በቁርጠኝነት ደብዳቤውን አቶ ማርቆስ ቢሮ አስቀምጠው ወጥተዋል፡፡
አቶ ማርቆስ ብዙነህም ከንቲባው ከሰአት ስለሚገቡ እሳቸው ካልፈቀዱ ቀሪ ደብዳቤ ላይ አልፈርምም ቢሉም ሰማያዊ ፓርቲ አዋጁ በሚያዘው መሰረት ከ48 ሰአት በፊት የማሳወቅ ስራውን ጨርሶ በፅ/ቤቱ ለተቃውሞ እንቅስቃሴው ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)በሳውዲ አረቢያ በዜጎች ላይየሚፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት አውግዞ በቅርቡ በሚጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ሕዝቡ በነቂስ በመውጣት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል በመቃወም ድምፁን እንደዲያሰማና ወገናዊ አጋርነቱን እንዲያሳይ መድረክ ጥሪ አቀረበ።
source . zehabesha

No comments:

Post a Comment