Friday, November 29, 2013

አላማ በወጣትነት ሲቀጭ

ደረሰባት የመኪና አደጋ ህይወቷ የተቀየረው እና የአልጋ ቁራኛ የሆነችው የሺወርቅ ምህረቴ
አንዳንዶች ጥሩ ገቢ አግኝተው ህይወታቸውን ለመቀየር ወደ ባህር ማዶ ተጉዘው ባዶ እጃቸውን ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ። ሌሎች በህመም ወይም በአደጋ ህልማቸውን ዕውን ከማድረግ ይሰናከላሉ። በዚህ ክስተት እነሱ ብቻ ሳይሆኑ የሚረዱት ቤተሰባቸውም ጭምር ችግር ይገጥመዋል። የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት « አላማ በወጣትነት ሲቀጭ» ይሰኛል።

እንግዳችን የሺወርቅ ምህርቴ ትባላለች። የአልጋ ቁራኛ ከሆነች አንድ አመት አለፋት። የሺወርቅን ቅስም የሰበረው አደጋ ከመድረሱ በፊት ተወልዳ ካደገችበት ጎንደር ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሄዳ ስራ እየሰራች ቤተሰቧን መርዳትም ችላ ነበር። ይሁንና የ 27 ዓመቷ የሺወርቅ የአንድ ቀን ገጠመኟ የህይወት ጉዞዋን ወዳልገመተችው አቅጣጫ ቀየረው። ለበርካታ ወራት ሆስፒታል ተኝታለች። ህክምናዋን መከታተል እንድትችል ስትልም በአዲስ አበባ በተከራየችው ቤት ትኖራለች። እናቷ ከጎንደር ሊያስታምሟት ሄደው አብረዋት ቀርተዋል። አልተሻላትም፤ አይኗን ስትከድን ትዝ የሚላት አደጋው ነው።
ከፍተኛ ስነ ልቦናዊ ጉዳትም ደርሶባታል።
ህይወቷን ስለቀየረው አደጋ አጫውታናለች። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
source.dw.de

No comments:

Post a Comment