Thursday, November 21, 2013

ቪኦኤ የሣዑዲን ተመላሾች አዲስ አበባ ላይ አነጋገረ

ኢትዮጵያዊያን በየአቅጣጫው እየተንቀሣቀሱ ነው፡፡
ከራሣቸው ይልቅ እስካሁን ወደ ሀገራቸው ያልገቡት ዜጎች ጉዳይ እንደሚያሳስባቸው ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ያሉ ኢትዮጵያዊያን አስታወቁ።
እዚያ ያለው ሁኔታ አሣዛኝ መሆኑን የገለፁት ተመላሾች ሁላችንም ወደ ሀገራችን እንድናስብ ያደረገ ነው ብለዋል።
ዘጋቢያችን እስክንድር ፍሬው ቦሌ አይሮፕላን ጣቢያ ተገኝቶ አንዳንዶቹን አነጋግሯል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን የውጭ አገር ሠራተኞች ከአገር ለማስወጣት በያዘው ዘመቻ በሳዑዲ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ነው የተባለውን እጅግ የከፋ ግፍና በደል በመቃወም በዓለም ዙሪያ ድምፃቸውን በማሰማትና በመንቀሳቀስ ላይ ካሉ ኢትዮጵያዊያን ቡድኖች በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዊያን የሲቪክና የፖለቲካ ማኅበራት ግብረኃይል አንዱ ነው።
ሠሞኑን በዋሽንግተን ዲ.ሲና አካባቢው በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የመጡትን ጨምሮ ቁጥራቸው የበዛ የዋሽንግተን ዲ.ሲና አካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያዊያንን ያስተባበረው ይህ ቡድን በትላንትናው ዕለት ለሳዑዲ አረቢያ መንግሥትና ለሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የላከውን ደብዳቤ ጨምሮ በቡድኑ እንቅስቃሴዎችና ዓላማ ዙሪያ የግብረ ኃይሉን ሊቀመንበር ፕሮፌሰር አቻምየለህ ደበላን አሉላ ከበደ አነጋግሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ሴቶች በሰፈር ወሮበሎች ለመደፈርና ሌላም የከበደና የሰፋ አደጋ መጋለጣቸውን በመጥቀስ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚንቀሣቀሰው የኢትዮጵያዊያን ሴቶች መብቶች ማዕከል ውግዘት አሰምቶ የተግባር ጥሪም አድርጓል፡፡
የማኅበሩን አመራር አባል ወ/ሮ ማኅደረ ጳውሎስን ቆንጂት ታየ አነጋግራለች፡፡
ለተሟላ ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
source: VOA Amharic

No comments:

Post a Comment