Thursday, November 14, 2013


Ethiopian sisters fighting back a Saudi thug

በሳዑዲ አረቢያ የተጀመረው የማባረር፣ መግደልና ማሰቃየት ወደ ሌሎቹ ለመዛመት ፍንጭ አሳይቷል
በግሩም ተ/ሀይማኖት
በአረቡ ዓለም ላይ በተደጋጋሚ እንደሚታየው አንድ ነገር (ድርጊት) አንዱ ሀገር ካደረገ ሌላውም ለምን ይቅርብኝ አይነት መከተል አለው፡፡ ለዚህ ደግሞ የአረቡ አለም አብዮትን ማረጋገጫ አድርጎ ማየት ይቻላል፡፡ አሁንም በሳዑዲ አረቢያ የተጀመረው የውጭ ዜጋን ማባረር፣ መግደልና ማሰቃየት ወደ ሌሎቹ አረብ ሀገራት አይዛመትም ብሎ መጠበቅ አይቻልም፡፡ ለሁሉም ነገር ተጠንቅቆ መጠበቅ ግድ ይላል፡፡
እዚህ የመን ውስጥ ፍንጭ መታየቱ ደግሞ የበለጠ አስጊ ያደርገዋል፡፡ በትላንትናው ዕለት የUNHCR ተወካዮችን ያካተተ ስብሰባ ተደርጎ ነበር፡፡ የስብሰባው አላማ በUNHCR ስር ያሉትን ስደተኞች UN እንዲያነሳ እና የተቀሩትንም ህጋዊ ያልሆኑትን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ውይይት ነው፡፡ የመገናኛ ብዙሀኖቻቸውም በዚህ ዙሪያ ትላንት እና ዛሬ አጠንክረው ይዘውታል፡፡ በትክክል ወደ ሀገር የመመለሱ ሁኔታ ቢፈጸም ጥሩ ነበር፡፡ ግን አያደርጉትም ጎረቤት ሀገር ሲደረግ ያዩትን እናድርግ ማለታቸው አይቀሬ ነው፡፡
አረብ ማለት አንድ ነው ይላሉ ራሳቸው፡፡ አንድ ከሆኑ ደግሞ ሳዑዲ አረቢያዎቹ ጭካኔና ሴጣናዊነት ይደገማል ማለት ይሆን? እንዲያውም እዚህ ሲቀለድ እንደሰማሁት ሴጣን ፓስፖርት አውጥቶ ቪዛ ጠይቆ መጣ በኋለ ሲያይ ከእሱ ይበልጣሉ፡፡ እነዚህስ እኔንም ያስቱኛል ብሎ ደንግጦ መመለሻ ጊዜው ሳይደርስ በባህር አመለጠ ይላሉ፡፡ ይህን ያስባለኝ እዚህም በደህናው ጊዜ ጥሩዎች ቢሆንም አሁን ካዩት አንጻር ወገን ላይ ጉዳት አያደርሱም ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ ከየመን ውጭ በኩዌትም ፍንጭ መታየቱን ወዳጄ ነዛር ዳጊ በዛሬ ዘግባው አስነብቦናል፡፡ አንድ ድርጅት ብቻ 1000 ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞችን ከስራ አባሯል፡፡ ቀጣዩ ምን ይሆን

No comments:

Post a Comment