Tuesday, November 19, 2013

በፍሎሪዳ እስቴት ውስጥ ኗሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን የተሰጠ መግለጫ።

በፍሎሪዳ እስቴት ውስጥ ኗሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን የተሰጠ መግለጫ።
የወገን ያለህ አለቅን ከሚለው ወገናችን ጎን እንሰልፍ።
ወገናችን ተወልዶ ባደገባት አገሩ አቅሙ በሚፈቅድለት መሰረት ትብዛም ትነስም ያገኛትን ከቤተሰቡና ከሀገሩ ሕዝብ ጋር ተካፍሎ በመተዛዘን የሚቀምሳትን ቀምሶ የሰላም ዓየር እየተነፈሰ እንዳይኖር ዜግነቱ፣መብቱና ክብሩ በማያከብሩለት ከአብራኩ በወጡት ሥብዕና በጎደላቸው ስግብግብ መሪዎች የተነሳ እትብቱ ከተቀበረባት አገር ገፍትረው ሲያባርሩት ተስፋው ተሟጦ አማራጭ በማጣቱ የተነሳ ሳያስበው ብድግ ብሎ ስደትን እንደ የችግሩ መፍትሄ በመውሰድ ወደ ተለያዩ ክፍለ ዓለማት በመሰደድ የቤተሰቦቹንና የራሱን አፍ ከድኖ ለማደር ሲል ከብሩን ሸጦ የባርነት ሥራዓት መቀበል የግድ ሆኖበት ነው።
ይህ በመሆኑም ይሄውና አሁን በሳውዲ አረብያ የተከሰተው መጨረሻ የለለው ገፍና በደል ሊደርስበት የቻለው።
የሳውዲ መንግሥት በዓለም አቀፍ የስደተኞች ህግ መሰረት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ሰባአዊ መብታቸውን ማክበርና በተደነገገው ህግ መሰረት ወደ መጡበት መመለስ ካልቻለ ወደ ስወስተኛ ሀገራት ለማሰማራት ጥረት ማድረግ ሲገባው በቅልብ ወታደሮቹና ባሰለጠኗቸው ዉሾች ሃላፊነት በጎደለው ድርጊት ኢ-ሰብአዊ እንግልት፣ድብደባ፣ ግድያና ሴት እህቶቻችንን አስገድዶ መድፈርን የተፈፅመባቸው እና አሁንም እየተፈጸመባቸው ባሉት ወግኖቻችን ላይ በአስቸኳይ እንዲቆም በጥብቅ እንጠይቃለን። በዚህ በያዝነው 21ኛው ክፍለዘመን እንዲህ የመሰል የባርባራውያን ተግባር በሳውዲ መንግስት መፈጸሙ በጣም አስቆጥቶናል። የሳውዲ መንግስት የታሪክን ሂደት ጠለቅ አድርገው ቢያስታውሱ ኖሮማ ይህ አይነት ግፍ በኢትዮጵያውያን ላይ ማድረሳቸውን የሚያሳየው የታላቁ ነብይ ሞሃመድ የአደራ ቃል መሻሩን የሚያመለክት አሳፋሪ ስህተት መስራቱ የሚያስነውር ድርጊት ነው ያውም ደግሞ ቅድሱነቱ በአልም ዙርያ ሁሉ አድናቆት ባተረፈው ቦታ።
ኢትዮጵያውያን ለዚህ ሁሉ ውርዴት የተዳረግነው የራሳችን ብለን የምንተማመንበት መንግስት ባለመኖሩ ነው እንጅ ቢኖረን ኖሮማ ዜጎቻችን ያለምንም ጥፋት በሰላ ጎራዴ አንገታቸው ሲቀላ እያዬ አጥፊዎች ናቸው ብሎ ባልፈረጀን ኖሮ የሳውዲ መንግስትም አጋር የሆነ መንግስት እንደለለን ቀደም ብለው ሥላጤኑ ነው ይህን ድርጊት ሊፈጽሙብን የቻሉት። በባርያው ሥርዓት እንኳ እንዲህ ያለ አጸያፊ ተግባር ይፈጸማል ብለን አናምንም።
በዓለም ዙርያ ለምትኖሩ ኢትዮጵያዉያን በሞላ በወገኖቻችን እየደረስ ያለው ሰቃይና በደል ከሥረ መሰረቱ ቀርፈን መጣል የምንችለው በጎሳ፣በሃይማኖትና በዘር መነታረኩ አቁመን ለስወስት ሺ ዘመን አቅፋና ተነከባከባ ባኖረችን እናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ጥላ ሥር በአንድነት ሥንሰባሰብ ብቻ ነው ልናድግና የመጣብንን ጠላት መክተን ወደ መጣበት አሳፍረን መመለስ የምንችለው። እንዲህ ዓይነት ህብረት ስለነበረ ነው አለምን ያርበደበደው ሃያል እየተባለ ሲሰገድለት ለነበረው ለፋሽሽቱ ጣልያን አያቶቻችን አፈራችን የባዕድ ዱካ አይረግጣትም በማለት እንደሻማ ቀልጠው ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ሰጥተው በዓለም ሕብረተሰብ ተከብረን ልንኖር የቻልነው በጋራ ስለመከትን ነው።በአንድነት ያለማበራች ያገኘነው ጥቅም ቢኖር ስቃይ፣ውርዴት፣መናቅና በአደባባይ ላይ ያለምነም ምክንያት መጨፍጨፍን እንጅ ላደረግነው ውለታ መስጋናን አይደለም የሳውዲ መንግስት የቸረን።ሥለዚህ ከእንግዲህ በኋላ አብረን በመነሳት የተቀማነውን ቅርስና ክብር ማስመለስ የግድ ይላል።
የሳውዲ አረብያ መንግስት በየኮርነሩ ለተገደሉት፣ለተደበደቡትና ለተሰቃዩት ወገኖቻችን ተጠያቂነት አለው ሥልዚህ፣
1ኛ-ወንጀል የፈጸሙትን ግለሰቦች ሆኑ ተቋማት በአስቸኳይ ለዓለም ፍርድ ቤት እንዲያስረክብ።
2ኛ-የዓለም የስብዓው መብት ተከራካሪ ድርጅት ወደ ሳውዲ በመሄድ ጉዳዩን እንዲያጣራ ትብብር እንዲደረግለት።
3ኛ-ለተገደሉትና ለተሰቃዩት የደም ካሳ እንዲሰጣቸው።
4ኛ-የወደመውና የተዘረፈው ንብረት ለባለንብረቱ ባስቸኳይ እንዲመለስ።
5ኛ-ክብረ ሰብዕነታቸው ለተገፈፉት እህቶቻችን አስቸኳይ ህክምና እንዲደረግላቸውና ተግባሩ የፈጸሙት ግለሰቦችም የሳውዲ መንግስት አሳልፎ ለሚመለከተው የዓለም ፍርድ ቤት እንዲያስረክብ፡፡
6ኛ-የኢትዮጵያ መንግስት ከሳውዲ ያለውን ዲፕሎማቲካዊ ግኑንነት ባአስቸኳየ ያቁም።
7ኛ-ሳውዲ በኢትዮጵያ ውሰጥ በጉቦ የገዛችውን መሬት ዉሉ ተሰርዞ ለድሮ በለቤቶች በአስቸኳይ እንዲመለስ።
8ኛ-የኢ ትዮጵያ ፓርላማ በሳዉዲ ከተማዎች ለተፈጸመው ወንጀል አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ውሳኔ እንዲደርግ እንጠይቃለን።
ከዚህ በላይ ከተራ ቁጥር 6 እስክ 8 የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች መንግስት መፈጸም ካልቻለ በትረ መንግስቱን ለቆ ብቃት ላላቸው መሪዎች ባስቸኳይ ያስረክብ።
በሳውዲ አረብያ ላላችሁ ወግኖቻችን በሞላ እናንተ ስትሞቱ እየሞትን፣ሰትቆስሉ እየቆሰልን፣ሰትጮሁ አብረን በመጮህ ከጎናችሁ መሆናችን እንድታውቁልን ችግርና መከራ ያልፋል በርቱ እንወዳችህ አለን።
ማሳሰብያ፦ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የተቋቋመው ግብረ ሀይል(ታስክ ፎርስ) በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ አቅማችን በሚፈቀደው መሰረት ሙሉ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆናችን እንግልጻለን በርቱ እንበርታ።
ጌታችን ፈጣርያችን ሆይ እጆችህን ወደ ተበደሉት ዜጎችህ ዘርጋ።
በፍሎሪዳ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን።

No comments:

Post a Comment