Thursday, December 24, 2015

ኦቦ በቀለ ገርባ ታሰሩ

(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተነሳውን የሕዝብ ቁጣ ተከትሎ በርካታ ወጣቶችን እያሰረ የሚገኘው ሕወሓት መራሹ መንግስት ባለፈው ማርች 2015 ከ እስር የተፈቱትን አቶ በቀለ ገርባን እንደገና አሰረ::
ዘ-ሐበሻ ከአዲስ አበባ ምንጮቿ እንዳገኘቸው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ኦቦ በቀለ ገርባ ዛሬ የታሰሩት በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ከተከሰተው የሕዝብ ቁጣ ጋር ተያይዞ እንደሆነ ይገመታል::
ኦቦ በቀለ ከቤታቸው ሲወሰዱ በርካታ የደህንነት ሃይሎች እና ፖሊሶች እንደነበሩ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያስረዳል::

እንዲሁም ከአቶ በቀለ ጋር የኦፌኮ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ደጀኔ ታፋም መታሰራቸው ተሰምቷል::
የኦሮሞ ተማሪዎች; ገበሬዎች እና ሌሎች ሕብረተሰብ ክፍሎችን የሰሞኑን ሕዝባዊ ቁጣ ተከትሎ ሕወሓት የሚመራው መንግስት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ማሰሩን ዘሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል::
አዳዲስ መረጃዎች እንደገኘን እንመለሳለን::

No comments:

Post a Comment