Sunday, September 21, 2014

ወጣቶቹ የአንድነት አባላት ጥላዬ ታረቀኝ እና ዳንኤል ፈይሳ ሃገራቸውን ጥለው ተሰደዱ።

የአንድነት ፓርቲ አባል የሆነው የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ምክትል ፀሐፊ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ መሰደዱ የታወቀ ሲሆን በተያያዘ ሁኔታ የሚለዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል በተደረገው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የእስረኛ ቱታ በመልበስ የገዥው ፓርቲን አምባገነናዊነት ካሳዩ ወጣቶች መካከል ዳንኤል ፈይሳም በተመሳሳይ ሁኔታ ለስደት መዳረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡Image

Imageየባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ምክትል ፀሐፊ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ በተደጋጋሚ ግዜ የደህንነት መታወቂ በሚይዙ ግለሰቦች ደረሰበትን ዛቻ ማስፈራሪና ድብደባ ተቋቁሞ ቢቆይም በቅርብ ግዜ ወዲህ ግን ማስፈራሪና ዛቻው ቅርጹን በመቀየር ለ12 ቀናት ለእስር እንደተዳረገና 3 የክስ ፋሎች ተከፍተውበት ፍርድ ቤቱ የመከላያ ምስክሮቹን እንዲቀርብ ማዘዙን ተከትሎ ከሳሾቹ የምንሰጥህን ተግባር የማትፈጽም ከሆነና በተለይም በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ካሉ የኢህአዴግ ሰዎች ጋር በመሆን የሚሰጥህን ተልዕኮ የማትወጣ ከሆነና በነ ሀብታሙ ኤያሌው ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር መሆን የማትችል ከሆነ 4ኛው ክስ ግራዚያኒ ሀውልት መገንባትን ተከትሎ በታሰሩበት ወቅት የቀረበበት አመፅና ሁከት ለመፍጠር የሚለው ክስ እንደሚንቀሳቀስ እንዲሁም በተደጋጋሚ ከኢሳት ቴሌቢዝን ጋር ግንኙነት በመፍጠር በሚል የአሸባሪነት ክስ ሊመሰርቱበት እንደሚችና እስር ቤት እንደሚበሰብስ መግለፃቸውን ተከትሎ ከሀገር ለመሰደድ መገደዱ እንደቻለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

No comments:

Post a Comment