Wednesday, August 27, 2014

የማለዳ ወግ … ይድረስ ለ”ጥቁር እንግዳዋ” ፈርጥ ተዋናኝ …ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ብሶታችን ንገሪልን ! * ለባህሬኗ ወዳጀ ለአርቲስት እስከዳር ግርማይ

ብርቱ ወዳጀ እስከዳር Esky አንች የብርቱም ብርቱ ሰው መሆንሽን አውቃለሁ ። ከባህሬኑ የስደት ኑሮ ግብግብ ፣ ለወገን ድጋፍ ማድረግና ባህልን ከማስተዋወቅ አልፈሽ ተርፈሽ ” የጥቁር እንግዳን” ፊልም ለዛሬ ያበቃሽ ድንቅ እህታችን ነሽ ። ፊልሙን በቡድን ከማዘጋጀት እስከመተወን ባደረግሽው ድንቅ ጥረት በባህሬን ምድር የክብር ቀይ የክብር ምንጣፍ አስነጥፈሽ ስማችን በረከሰበት የአረብ ሃገር ፊልምሽን ስታስመርቂ የኮራሁት ኩራት ከውስጤ አይጠፋም ። ያንን ስሜት ሌላ ጊዜ አወራዋለሁ … ዛሬ ወደሳበኝ ግስጋሴሽ እና ልታደርሽልኝ ስለምፈልገው መልዕክት ጭብጥ ላምራ … !
ወዳጀ እስከዳር ግርማ ልጆችን ከማሳደግ የአረብ ሃገር ስደት ኑሮን ግብግብ ጋር ታግለሽ ዛሬ “ጥቁር እንግዳ ” የሚለው ከ25 ዓመት በኋላ ወላጆችዋን ፈልጋ ስለተመለሰችው ስለማደጎዋ ልጅ ምስኪኗን ሳራ ሆነሽ የተወንሸው አስተማሪ ፊልም በሃገር ቤት ፊልም መናኘት መታየት በመጀመሩ የተሰማኝን እርካታ ከፍ ያለ ነው።
ይህንን በአይነቱ ልዩ የሆነውን በማደጎ ችግር ላይ ያተኮረ ፊልም ስታስተዋውቂ ከበርካታ ታዋቂና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችን የማግኘት እድሉን በማግኘትሽ ደስታ ተሰምቶኛል። ደስታየ ወሰን ያጣውም ከፊልም ማስተዋወቁ በተጓዳኝ በአረቡ አለም እና በቀረው አለም እኛ ስንጮህ አልሰማ ያለውን የጩኸት መልዕክት በቀጥታ ለሹሞቻችን ትነግሪ ታስረጃቸዋለሁ በሚል ነው ። እርግጥ ነው በዋናነት ፊልምሽን ማስተዋወቅ ቢኖርብሽም በአረቡ ስደተኛ ህይወት መልዕክት ሳታስተላልፊ ትቀሪያለሽ አልልም ። መብት ጥበቃው ጎድሎብን ኑሯችን ማክበዱን ፣ ሰቆቃችን መቀጠሉን ታስተላልፊያለሽ የሚል ጽኑ እምነት ቢያድርብኝም አሁን በአደጋ ተከበናልና የወዳጅነቴና ማስታወስ ግድ ብሎኛል !
ወዳጀ ሆይ … በጥረት ትጋትሽ ፣ የብርቱም ብርቱ እየሆንሽ በማየቴ ደስ ቢለኝ በመንገድሽ የስደተኛውን መከራ ታስታውሽ ዘንድ ደጋግሜ ልማጸንሽ ወደድኩ … በተለይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስን አድሃኖምን እንዳገኘሻቸው በገጻቸው ካንች ጋር የተነሱትን ፎቶ ስመለከት የተሰማኝ ደስታ የማደንቀው ትጋት ብርታትሽን ነው ። አሁንም ደግመሽ ካገኘሻቸው ግን በፈጣሪ ብለሽ ብየ የምማጸን፣ የማወራሽ መልዕክቴን እና ለስላስ ያደረግኳትን ለእሳቸውና ለሚመሩት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ወቀሳየን አድርሽልኝ ! ስለ አረቡ አለም የዜጎች ስቃይ ሰቆቃ አንችን ቢሰሙሽ በአጽንኦት ንገሪልኝ !
አዎ ከ12 ዓመት በኋላ ከእገታ ስላዳንሻት ፣ ስለታደግሻት የኮንትራት ሰራተኛ እህትን ዋቢ አድርገሽ በአረቡ አለም ስላለው የዜጎች መከራ ከፕሮፓጋንዳ ባለፈ ለዜጎች መብት መከበር የሚቆም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንደናፈቀን ንገሪልኝ ፣ ስደተኛው ይህ ናፍቆታልም ብለሽ ምሬቱን ንገሪያቸው ! አደራ እህታለም ! ንገሪያቸው ፣ አንችን ከሰሙሽ ተማጸኛቸው !
ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም ያኔ ሳውዲ ላይ ወገን ሲበደል ፣ የበደሉ ብድር መላሽ እንደሆኑ ፎክረው ሳያደርጉት ስለቀሩ “በቀል የእግዚአብሔር ነው!” በሚል ተጽናንተን ትተነው እንጅ ከፍቶናል። የዚያ በደል ቁስል ሳያሽር በኮንትራት ሰራተኞች ላይ በደል ተደጋግሞ ሲፈጸም ተመልክተን በዶር ቴዎድሮስ እና ሳውዲ ውስጥ ያስቀመጧቸው የውጭ ጉዳይ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ስለመብታችን መደፈር የፈየዱትን ማየት አልቻልንምባ አዝነን አላበቃንም ። ከሁሉም የሚያስከፋው ካንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ራሳቸው ዶር ቴዊድሮስ በአካል ላዩ ፣ ለጎበኟቸው በህግ ማዕቀፍ ወደሳውዲ ለመጡ የኮንትራት ሰራተኛ ግፉአን የፈየዱት ነገር ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ ማድረግ እንጅ ለበደላቸው ፍትህ ርትዕ እንዲያገኙ ማድረግ አይደለም። ይህን ባለማድረጋቸው በቅርብ የምናውቅ ፣ አግብቶን የምንቆረቆር ዜጎች አንገታችን መድፋታችን ንገሪልን … !
አሁን አሁን እኔ በግል በነጻነት እጽፍ እናገርበት የነበረው ሃገር ከፍቶብኛል ፣ ለሁለት አስር አመታት እንደ ሃገሬ በነጻነት እንቀሳቀስ የነበረበትን ሃገር ያከፉብኝ ያገሬው ሰዎች ብቻ አይደሉም ! … ሳውዲ ያለውን መከራ ስቅየቱን እየሰማሁ ” የዝሆን ጀሮ ይስጠኝ ” በሚል መረጃ ቅበላው ላይ በአደባባይ መታየቱን አለመሻቴ ቢያምም ከአደጋ ለመጠበቅ የተወሰደ ራስን የመውደድ አሳፋሪ አማራጭ መከተሌ እያሳዘነ እያሳፈረኝ የማጫውትሽ ነገር ቢኖር የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤታቸውና ደጋፊዎቻቸው የወገኖቻችን መከራ ስለተናገርን በአይነ ቁራኛ እያዩን መቸገራችንም ጭምር ነው! ይህንንም ክሽፈት ንገሪያቸው !
ወዳጀ ዛሬም ደፍሬ በደፈናው የምነግርሽ በዚህ ወቅት ከቀናት በፊት በሪያድ የተስተዋለው አሳዛኝ ድርጊት ነው። የዚህ አይነቱ ዘመቻ ወደ ሌሎች ክልሎች እንደሚዛመት ሰምቻለሁ ። በዚህ ዘመቻ “ለህገ ወጦች” ተብሎ የሚጀመረው በእኛ ላይ የገነነው የማጥራት ፣ ማጥቃት ዘመቻ ህጋዊውን ነዋሪ ጭምር በከፋ ፈተና ውስጥ እንዳይጥለው ስጋቴ ከልምድና ተሞክሮ የመነጨ ነውና ይረዱልኝ ዘንድ አሳውቂያቸው ። እናም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃላፊቅም ሆኑ ሹሞቻችን ስለምንዋረድ፣ ስለምነገፋ ስደተኞች ተቆርቋሪነታቸውን ያሳዩን ዘንድ ድምጽሽን ከፍ አድርገሽ እኔንም አንችንም ሁላችንንም ሆነሽ በተበደለው ወገን ስም አሳውቂያታቸው !
አደራ በሰማይ አደራ በምድር !
አክባሪና አድናቂ ወዳጅሽ
ነቢዩ ሲራክ
Sent from Samsung Mobile
——– Original message ——–
From: Nebiyu Sirak
Date:2014/08/08 1:58 AM (GMT+03:00)
To: “Zehabesha. com” ,info@ecadforum.com,info@abugidainfo.com,samson asfaw ,quatero_webmaster@hotmail.com,Bette Mera ,editor@ethsat.com,Golgul/ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ,EMF Media ,editor@awrambatimes.com,editor@addisvoice.com,zelalem@maldatimes.com
Subject: የማለዳ ወግ… በፈራረሰችው ጋዛ የጨለመው ተስፋ !
የማለዳ ወግ …በፈራረሰችው ጋዛ የጨለመው ተስፋ !
* በደም ምድሯ የሚንሰራፋው ጥላቻ!
ወር በተጠጋው የእስራኤል ጋዛን የማጥቃት ዘመቻ በአሳር በመከራ የተደረሰው የ 72 ሰዓቱ የጦርነት ማቆም ሊያልቅ የቀሩት ጥቂት ሰአታት ብቻ ናቸው። በእስራኤል የአየር የየብስና የባህር ድብደባ ከ1800 በላይ አብዛኛው የጋዛ ንጹሃን ፍልስጥኤማውያንን ተገድለዋል። ከ 9000 የማያንሱትን ቆሰለዋል። በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ በሃገራቸው ተሰደው ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ጋዛ እንዳልነበረች ሆናለች :(
ይህ ሁሉ ሆኖ ጦርነቱ እንዲያቆም በተደረሰው የ 72 ሰአታቱ የሶስት ቀን የጦርነት ማቆም ስምምነት በቀጣይ ጦርነቱን ለማስቆም በግብጽ ካይሮ በዋናነት ሃማስና ፋታህን በተሳተፉበት የፍልስጥኤም እና በእስራኤል የጦርነት ማቆም ድርድር የተሳካ አይመስልም። ለአልህ አስጨራሹ ድርድር የመክሸፍ ምክንያቶች ፍልስጥኤማውያን “ጋዛ ከእገታ ትውጣ !” የሚለው ጥያቄ ሲያነሱ እስራኤል በበኩሏ “ሃማስ ትጥቁን ይፍታ !” በሚል የማይሞከር ቅድመ ሁኔታ ተስፋውን አጨልሞታል !
ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው የፍልስጥኤምና የእስራኤል ግጭት በተቀሰቀሰ ቁጥር በአቅመ ደካማና በንጹሃን ታዳጊ ህጻናት ላይ የሚያርፈው በትር ልብን በሃዘን እንደሰበረ መሆኑ ውስጥን ያደማል ። በደል ግፉ ባላባራባት የፍልስጥኤም የደም ምድር በጋዛ በሞት የሚቀጠፈው የንጹሃን ነፍስ ፣ አካለ ስንኩል የሚሆነው ግፉዕ ፣ ከተወለደበት ቀየ የሚፈናቀለውን ዜጋ አበሳ ሁኔታ መመልከት ሰላም ይነሳል !
በፍልስጥኤማውያን የውስጥ ምርጫ ውዝግብን ተከትሎ ፖለቲከኞቸ ለሁለት ሲከፈሉ እስራኤሎች ስራውን ሰርተውታልና ያገኙትን እድል ተጠቀሙ ጋዛንና “ነውጠኛ አሸባሪ ” የሚሉትን ሃማስን ከቀረው ቀረው ፍልስጥኤም ጋር ለያዩት ። ወላጅ ከልጅ ፣ ቤተሰብ ከቤተሰብና ፣ ዘመደ ከአዝማዱ በገዛ ሃገሩ ተለያየ ። ፍልስጥኤም በገዛ ሃገራቸው በሰማይ ምድሩ የማያዙ ከመሆን አልፈው በቀያቸው ስደተኛ ሆነው መኖር ግድ አላቸው። መከራቸው በዚህ ቢያከትም መልካም ነበር … ግን አልሆነም ! እውነቱ ይህ ሆነና ትናንትም ዛሬም የሚታየው ሰቆቃ በጨቋኝና በተጨቋኝ “ዝሆኖች ” መካከል የሚደረገው ፍትጊያ ውጤት እልቂት ለመሆኑ ምስክሮች ሆንን ። ምክንያት እየተፈለገ የሚያልቁት የሚፈላለጉት ባላንጣዎች አለመሆናቸው ዛሬም ያሳዝናል …
” ዝሆኖች” በተራገጡ ቁጥር እንደ ሳሩ የሚደቁ ፣ የሚደቆሱ ንጹሃኑ ናቸው:( ይህም የሁለት ኩታ ገጠም እህታማች ሃገራት ንጹሃንን ውሎ አዳር አክፍቶታል። ከራማላህ እስከ ከቴልአቢብ ፣ ከእየሩሳሌም ጋዛና ራማላህ ያልታጠቁ ንጹሃን በስጋት ሽብር ሰለባ ሆነዋል። የአንባጓሮው ውጤት የሰው ልጅ መከራ እንዲገፍት ከማድረግ ባለፈ መገዳደሉ ባተረፈው ጥላቻ እና ቂም ጎረቤቶች በጉርብትና ሊያኖራቸው የሚችለውን ሰላማዊ ቀጣይ ህይወት እየበጠበጠው ይገኛል …
የጋዛ ፍልስጥኤናውያንን አስለቅሶ እያደማቸው ያለውን የእስራኤል ጦር እየተፈታተኑ ያሉት የሃማስ የጦር ክንፍ አባላት በእስራኤል ሰማይና ምደር እያሳዩት ያለው የመከላከል የማይጨበጥ ስልት እና ቆራጥነት እና ብርታት ለደጋፊዎቻቸው የባለድልነት ስሜት ማጫሩ ባይከፋም እየተከፈለ ያለው መስዋዕትነት ንጹሃን በዚህ ደረጃ ያልተገበረበት ቢሆን መልካም ነበር ! ለአንድ ወር እስራኤሎች በከፈቱት መጠነ ሰፊ ጥቃት ግፍ ፈጻሚው ወታደር አፈሙዙን ድረስ ግንባራቸውን እየሰጡ “ግደሉን አንፈራም !” የሚሉ ፍልሰጥኤማውያንን ታዳጊዎች ፍርሃት ሳያበራግራቸው እያሳዩት ያለ ወኔ ግፍ ያመጣው ቢሆንም ቅሉ በዚህ ደረጃ ከታዳጊዎች የሚጠበቅ አልነበረም! … ወደድንም ጠላንም ታዳጊዎች ልበ ሙሉ ሆነው ከአንጋች ጋር የመጋፈጣቸው ሚስጥሩ ፣ ግፍ በዝቶ በውስጣቸው የቋጠሩት ጥላቻ እና በቀል ለመሆኑ ጥርጣሬ የለኝም ። ምስኪን ምንዱባኑ ታዳጊዎች ሰቆቃውን አይተውት ፣ ተነግሯቸው ብሎም አስተናግደውት ሰቆቃው እልኸኛ አድርጓቸዋል ! በደሉ ሲገነፍል ደግሞ እሳት የጎረሰውን መሳሪያ የሚሸሽ ሰብዕና ያጣሉ ፣ ያመራሉ! ወንድም እህታቸውን ፣ ዘመድ አዝማድ ወገናቸውን ከጨረሰው እሳት ጎራሽ ጠመንጃ ከያዘው ወታደር ጋር ጉርቦ ለጉሩቦ ሲተናነቁ አይተናል ! በቃ ህይወት በዚያ ምድር እንዲህ ሆናለች :(
እውነቱ ይህ ሆነና ታዳጊው ተምሮ እንዳያድግ አእምሮው በሁለት ወገን ተገድቧል። በእገታ የተገደበው ዜጋ ፣ የመከራ ኑሮን በሚገፋበት ቀየ በነጻነት ታጋዮቹ በውስጥ ለውስጥ የጥላቻ አስተምሮት ተጨምሮበት ጥላቻው ጣራ ነክቷል። በዚህና በዚያ በጥላቻ አድጓልና የፍቅር ፣ የሰላምንና የአብሮነትን ተስፋው ጨልሟል ። ታዳጊው በጥላቻ ውርስ ቅብብል አድጓልና ቀጣዩ መከራ በዚህ ብቻ አያባራም። ፍልስጥኤማውያን ታዳጊዎች ከምሬት ብሶት እንባ ጋር መከራ በደሉን ሲሰሙ ያድራሉ። ከቤቱ ጥላቻ ውርስ አረፍ ሲሉ መገናኛ ብዙሃኑ ይቀበሏቸዋል።
እንደሰማን እንዳየነው መገናኛ ብዙንም ወገንተኛነት ተጠናውቷቸው በየአቅጣጫው ከእሳት ላይ የሚጨምሩት ቤንዚል ለጥላቻው መንሰራፋት ትልቁን ድርሻ መያዛቸውን መታዘብ ለቻለ አሁንም ቀጣዩን መከራ ያሳይ እንደሁ እንጃ … ለታዳጊዎች አስተማሪ ቁም ነገር የተቀላቀለበት ሳቅ ፣ ቀልድ ፣ ጫወታ ፣ ምክር አዘል ምስልና ካርቶን ያቀርቡ የነበሩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ዛሬ እያቀረቡት የምናየው መረጃ ደስ አይልም። በቅርቡ ” ጥዩር አል ጀና ” በሚል የሚታወቀው ለታዳጊዎች በአረብኛ የሚተላለፍ ዝነኛ የሆነ የልጆች ቴሌቪዥን ፕሮግራም አንድ ያልወደድኩትን ዝግጅት ተመልክቻለሁ። በዚሁ ጣቢያ ተወዳጅ የህጻናት ዘፋኝ ታዳጊ ጃንን የወታደር ልብስ ለብሳ ስለጋዛ ስትዘምር ሲታዩ የነበሩ ምስሎች ተቀነባብሮ በታዳጊዋ መቅረቡን መመልከት ህሊናን ይጎዳል ። በፕሮግራሙ መካከል ለመዝናኛ በሚመስል መንገድ የቀረበው “አብዮታዊ ” መዝሙር የጋዛን ግፍ ለህጻናት ታዳጊዎች በማይመጥን መልኩ ማሳየት ሊፈጥረው የሚችለውን ስለ ልቦናዊ ቀውስና ጥላቻ አውጥቸ አውርጀ አዝኛለሁ :( በዚህም በሉት በዚያ ግፍ እንደ ሰደድ እሳት እየለበለባቸው ያሉ ዜጎቸ መከራ ሳያንስ ለቀጣዩ ትውልድ ጥላቻና በቀል የማወራረስ ይትበሃል በመገናኛ ብዙሃነ በሰፊው ሲሰበከ መስማትና መየት ለህሊና አይመችም…
ላለፉት አስርት አመታት ብቻ ፍጥጫውን ተከትሎ በተደረጉት ሁሉ ጥቃቶች ፍልስጥኤማው

No comments:

Post a Comment