Sunday, August 31, 2014

መንግስት ተብዬው ምን እየሰራ ነው?

እያለማ፣በህዳሴው ግድብ፣ በባቡር መንገድ ግንባታው በኢቲቪ በሚባለውም በማይባለውም ሀገር የመገንባት ስራ ተወጥሯል የምትሉኝ ካላችሁ እሱን ተዉት!! አይደለም፡፡ህውሃት ምሽግ እየቆፈረ፣ ቦምብ እየቀበረ ነው ያለው፡፡2007 ምርጫ እየደረሰ ነው፡፡በዚህ ምርጫ ኢህአዴግ/ህውሃት እሸነፋለሁ ብሎ ባይሰጋም፣እየተደገሰልኝ ነው ብሎ እያሰበው ባለው ነገር እረፍት የተሰማው አይመስለኝም፡፡በጣም ሰግቷል፡፡ሰማያዊ ፓርቲን አይደለም የሚሰጋው፣ አንድነትም አይደለም ፣ግንቦት ሰባትን የኤርትራ መንግስትንም አይደለም፣ህዝቡ ነው፡፡እነ ሰማያዊ እነ ግንቦት 7 እነ አንድነትና ሌሎችም ጉልበት የሚኖራቸው ህዝብ ካለ ብቻ ነው፡፡ይህ ህዝብ ምቹ ቀንና አጋጣሚ ካገኘ አንዴ ከተነሳ ወደነበረበት ለመመለስ እንደማይቻል ተርድቷል፡፡ ስለዚህ ለዚህ ህዝብ ምቹ ነገር አለመፍጠር አጋጣሚ አለመስጠት አማራጭ የሌለው የመከላከያ መሳሪያ አድርጎ ነው ያለው፡፡ከነዛ መሳሪያዎች ደግሞ በአሁኑ ወቅት በልማት ስም የሚደሰኮሩ ፕሮፖጋንዳዎች፤ህዝብን ከህዝብ የመለየት ስራዎች ፣ህውሃት እራሱን አስፈሪ እሱ ከሌለ ሀገሪቷ ወደሲኦልነት እንደምትለወጥ አድርጎ የማቅረብና የመሳሰሉት ነገሮች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ከላይ ምሽግ እየቆፈረ ቦምብ እየቀበረ ነው ያልኩት ለዛ ነው፡፡እንዴት ብትሉኝ፡

ይኸውላችሁ፡ዛሬ ቆመው የምታዩዋቸው ፎቆች የተዘረጉ መንገዶች የሚወሩ የሚለፈፉ ነገሮች ህውሃት ምሽጎች ናቸው ፡፡ህዝቡ በዚህ እየተጃጃለ፣ህውሃት100 እና ከመቶ አመት በላይ በስልጣን ለመኖር የሚያስፈልጉትን ስንቆችና ትጥቆች አዘጋጅቶና አከማችቶ እስኪጨርስ ድረስ ጊዜ መግዛዎች ናቸው፡፡ጸጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል እንደሚባለው የኢትዮጵያ ህዝብም ፎቅ መጣ፣ መንገድ ገባ፣ ባቡር ሄደ፣ግድቡም ደረሰ እያለ እየኖረ መስሎት አለመኖሩን ሳያውቅ እንዲሞት ነው እየተደረገ ያለው፡፡አንድ ፊልም ላይ እንዲህ የሚል ስንኝ ሰሜቼ ነበር፡
When we are saying,
let’s defend the cities,
It isn’t about the stones
It is about the people in the walls.
የኢትዮጵያ ህዘብ ሳርና ጭቃ የለበሰ ቤት ለምዶ አሁን የቆርቆሮና የድጋይ ቤት ሲቆምለት ፣ ሰው ሆኖ የጨረሰ መስሎት ይኸው ህውሃት ጢባጢቤ እየተጫወተበት በማይረባ ነገር እጠተንጠባጠበ ነው ያለው፡፡ፎቅ ቢሰራ መንገድ ቢሰራ ሰው ያሁሉ ስራ ሰው የማይሰራበት፣ አላማው ሰው ለማፍረስ ከሆነ ምን ጥቅም አለው?እገሌ የተባለ የህውሃት ባለስልጣን 100 ፎቆች ቢሰራ የሱን ቦርጭ ከማኮፈስ ቀንበር ከማብዛትና ባንዳ ከማብዛት በቀር ምን ጥቅም አለው?የአንድ አሙስ እድሜ የሌላቸው ፎቆች ቆሙ አልቆሙ ካድሬና ባንዳ ለማሰፈር ካላገለገሉ በስተቀር ዋጋ የላቸውም፡፡ዝምብሎ አንዳንድ ምስኪኖች እየቆጠሩ የድሆች ጎጆ ነው ማለት ሞኝነት ነው፡፡ለማነኛውም ህውሃት ውስጥ ለውስጥ ሰው እያፈረሰ ፊት ለፊት ድንጋይ ስላቆና ስላነጠፈ ሀገር እያለማነው ማለት መሸወድ ይመስለኛል፡፡ህውሃት የአዲስ አበባ መንገድ ላይ ወርቅ እንኳን ቢያነጥፍ እንኳን ልክ አሸዋ ላይ ተሸላልም የቆመች ግን ቀላል ነፋስ እንኳን ቢመጣ የሚገለብጣ አይነት ቤት ናት፡፡የኢህአዴግ መሸሸጊያና መባለጊያ ከመሆን ውጪ ጥቅም የላትም፡፡
አዲስ አባባ ዋና ከተማ ናት ግን ህዝቡ በፎቅ በግድብ በምናምን ወሬ ልቡ ተደፍኖ አንድ ወር ሁሉ ውሀ ፍለጋ ጀረኪና ይዞ ይዞራል፤ ጋግሮ ከላ ይጠግባል ይነሳል ተብሎ በኢቲቪ ወሬ እየተቀለበ ያለ መብራት ስንት ሳምንት በጨለማ ይዳክራል፣ታክሲ ፍለጋ ሰልፍ፣ ውሃ ፍለጋ ሰልፍ ፣ መንገድ ለመሻገር ሰልፍ ብቻ የባርነት ሰልፍ፣ የመደፈር ሰልፍ ለምዶ የነጻነት ሰሰልፍ፣ የእኩልነት፣ ፍትህ ሰልፍ እንዲረሳ ሌት ተቀን እየደነዘዘ፣ እየፈዘዘ እንዲሄድ ይፈልጋል፡፡ለዋና ከተማ የማይመጥን ህዝብ ሆኖ እየተበየደ ነው ያለው፡፡ሁሉ ረሀቡን፣ ጥማቱን እያሰበ ቁራሽ ዳቡና ጭላጭ ውሃ ብቻ እንዳባረረ በተሸወደ ተስፋ ተኝቶ እንዲኖር ነው የሚፈለገው፡፡ህዝቡ ሲተኛ ኢህአዴግ ምን መስረቅ እንዳለበት ያውቃልና!!
እስቲ ህውሃት በሀይማኖትና በብሄር ስም እየቀበራቸው ያሉ ቦምቦችን ልብ ብላችሁ አስተውሉ፡፡ ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ በሚቀጥለው ምርጫ መጠቀሚየ ሊያደርገው ይፈልጋል፡፡በአሁኑ ወቅት ህውሀት በኮንትራትም ቢሆን ከኦፒዲኦ ጋር ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ አክራሪ ብሄርተኞች ነን ከሚሉት የጋብቻ ቀለበት ለማድረግ ይፈልጋል፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ በሚቀጥለው አመት ሁሉም ብሄር በራሱ ቋንቋ ይማር እንደተባለው የራሱን ታሪክ ብቻ እንዲማር ይፈለጋል፡፡ለምሳሌ ለኦሮሚያ ክልል የሚዘጋጀው የታሪክ መጽሀፍ በሚኒሊክ ዙሪያ ከሚያስተምረው ትምህርት አንዱ ምን እንደሚሆን አስቡት ጡትና አንገትን ቆረጠ፣ ይህንን ቆመጠ ያንን ፈለጠ እየጠባለ እንደሚሰጥ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ህውሃቶች አኖሌ ብለው ያቆሙት የትላቻ ምልክት ለምን አይነሳም ሲባሉ የሰጡት መልስ ታሪክ ስለሆነ ችግር የለውም ታሪክ ታሪክ ነውና ማለታቸው ይታወሳል፡፡በሌላ አባባል ሁሉም ክልል የኢትዮጵያ ታሪክ የሚባል ሳይሆን የእገሌ ክል /ብሄር ታሪክ ብሎ የሚማር ከሆነ ትልቁ የገጽ ሽፋን ከሚያገኙት ውስጥ የጥላቻ ምልክት የሆነው የአኖሌ ምስል አንዱ እንደሚሆን አያጠራጥርም፡፡እና በ2007 ህውሃትዬ ታሪክ አክባሪ መስሎ የኦሮሞን ህዝብ በተረት ተረት ሊሸውድ እየተዘጋጀ ነው፡፡በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል የተዘጋውም ለዚህ አዲስ እየተቀረጸ ላለው ተረት ቤት ለማሰናዳት ፣የታሪክን ቤት በተረት ጣራና ግድዳ ለመቀየር ብሎ ነው፡፡
ሌላው ቦምብ ደግሞ በዚህ በሚዘጋጀው የታሪክ ትምህርት ክልሎች የራሳቸው መንገድ የሚከተሉ ከሆነ ለግራኝ መሀመድ ስራዎች የክብር ዘውድ እንዲደፋለት በማድረግ እስካሁን ልቡን እያራዱት ያሉ አንዳንድ ሙስሊሞችን ለማስደሰት ይፈልጋል፡፡የኢትዮጵያ ታሪክ ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሄድ እግሩን ከቆረጡት በኋላ ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ተያያዥነት አላቸው የሚሏቸው ተቃማት አንገት መቁረጥ ነው፡፡ይህ ለማድረግ መጽኀፍቱ እስኪታተሙና በየትምህርት ቤቱ እስኪሰራጩ የሚጠብቅ አይመስለኝም፡፡ከእነዚህ ተቃማት አንዱ የኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያንን አንገት መቁረጥ ነው፡፡ ጉምድ ማድረግ፡፡ በዚህች ቤተክርስቲያን ደግሞ ነገሮች አጥብቆ እየሰራ የቤተክርስቲያኒቷን አስራር ለማዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ ምንጣፍ ለይ እየጠራመዱ ያሉ ስብስቦች አሉ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን፡፡ ማጥፋት ፡፡ ምክንያቱም በኢትዮጵያዊነትና በኢትዮጵያ ታሪክ ስለሚያምን ለክፉ ቀን አይሆንም ተብሎ ይታሰባልና፡፡ከዛም በምርጫው ሰበብ የሚነሱ ማናቸውም ነገሮች አቅም ማሳጣት፣ የአራት ኪሎን ቤተመንግስት ከስጋት ነጻማድረግ፡፡ ነጻ የሚሆነው ከማነው ይባል ይሆናል፡፡ ከጎን ሆነው ይህን ህዝብ ብሶትና አንድነት ተጠቅመው ከመቶ አመት ጉዞው ሊያደናቅፉት የሚፈልጉት ሀይሎች፡፡
ያ ህዝቡ ሀይል ባይኖራቸውም ከህህቡ ጋር ሀይል ፈጥረው ችግር ሊፈጥሩ ከሚችሉት ውስጥ ግንቦት 7 የኤርትራ መንግስት የሀገር ውስጥ አንዳንድ ፓርቲዎች እንዲሁም ግለሰቦችና ተቋማት ይጠቀሳሉ፡፡በተለይ የየግንቦት 7 አመራር የመግደል ሙከራ ከከሸፈ በኋላ፣ የህውሃት በእነ አሜሪካ በኩል ከኤርትራ ጋር አስታርቁኝ በኢሳያስ እምቢተኝነት ከተቋጨ በኋላ የህውሃት ያገኘውን ሁሉ ከመቧጠጥና ከመቧጨር ወደ ኋላ እንደማይመለስ አረጋግጧል፡፡ምንአልባት የቅርብ ስጋቱ የሚሆነው ግብጽ በደቡብ ሱዳን በኩል የኢህአዴግ አፍንጫ ላይ ለመቀመጥ መንደርደሯን ነው፡፡ እላይ በተባሉትም ሆነ በሌሎች ባልጠተቀሱ ምክያቶች ህውሃት ለ2007 ምርጫ ምሽግ እየቆፈረና ቦምብ እየቀበረ ነው፡፡ ተሳክቶለት 2007ን ካለፈ ሶስት አማራጮች አሉት፡፡ አንዱ በሁሉም ነገር የትግራይ የበላይኔ የሰፈነባትና የነገሰባት ኢትዮጵያን መፍጠር፣ኢሳያስን ከስልጣን አውርዶ የትግራይና የኤርትራ ባንዲራን ለማጋባት መሞከር፡፡ከዛም ኢትዮጵያን በሁሉም ነገር በበላይነት የመግዛት፣የመጠቀም እድል ካልተገኘ ልክ ልክ ራሺያ ክርሚያ የተባለችው ግዛት በጠቀለለችው አኳን ኤርትራን ትግራይ ተጠቃለው አንድ ሀገር ሆነው ሌሎቹ የኢትዮጵያ ክልሎች በብሄር በሀይማኖት ተከፋፍለው እርስ በእርስ ሲናጩ ማየት፡፡ የምሽጉም የሆነ የቦምቦ የመጨረሻ ግብ ከሁለቱ አላማ አንዱን ለማሳካት ነው፡፡
ከሁለቱ አንዱ የሆነ እለት ሀይለማሪያም ደሳለኝ የአንዷ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር ሆነው ነገሩን እያስታወሱ ሺህ ጊዜ ንስሀ ቢገቡ እግዜር የሚሰማቸው አይመስለኝም፡፡እግዜር ደግሞ ቀላል አይደለም! መጨፈራቸውን ብቻ ሳይሆን ለዚህ አላማ ሌሎች እንደጨፍሩ ማነሳሳታቸው ሳይቀር መስመር በመስመር እንደሚጠይቃቸው እርግጠኛ ነኝ፡፡ ያኔ አዳም እንዳለው ሜስቴ አስታኝ ነው አይሰራም ፣ እግዜር አይሰማም፣ ወ/ ሮ ሮማን ተስፋዬ እንዲህ እንደ ሄዋን የማይሆን ነገር እየመከሩ ሰው የሚያስቱ ከሆነ ቢያስቡበት መልካም ነው፡፡እግዜር ከእንግዲህ በኋላ ሰ ቆዳ ሰፍቶ የሰዎችን ሞራል የሚጠብቅበት እድል ያለ አይመስለኝም ፤ቆዳ ነው እንጂ የሚያደርገው!!ቶሎ የለሁበትም ይህ ህዝብ ንጹህ ነው ብሎ እንደ ጲላጦስ እጅ መታጠብ ይሻላል!! ይታሰብበት!! አለቀ!!!

No comments:

Post a Comment