Monday, February 17, 2014

አቡጊዳ – የዶር ያእቆብ «አሰብ የማን ናት?» መጽሃፍ ሰባት ጊዜ እንደታተመ ተገለጸ

ዶር ያእቆብ ኃይለማሪያም፣ የአሰብ ወደብን በተመለከተ የጻፉት መጽሃፍ ሰባት ጊዜ እንደታተመ ከሲ.ቢ.ኤስ ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገለጹ። «ይህ የሚያመለክተዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ያህል የአሰብ ጉዳይ እንደሚያንገበግበው ነዉ» ያሉት ዶር ያእቆብ፣ በአሰብ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች በስላም መፍታት እንደሚቻልም ለማሳየት ሞክረዋል።
የኤርትራ ሕዝብና የኢትዮጵያ ሕዝብ ወንድማማች ህዝብ እንደሆኑ የተናገሩት ዶር ያእቆብ፣ ጠቡና መለያየቱ የመጣዉ በመሪዎች ችግር ብቻ እንደሆነ ይገልጻሉ። «ተለያየትን አንቀርም። አንድ ቀን ተመልሰን አንድ መሆናችህ አይቀርም» ያሉት ዶር ያእቆብ ፣ የአሰብ ጉዳይ በሰላም የሚፈታበትንም አራት አማራጮችን አቅርበዋል።

ኤርትራና ኢትዮጵያ፣ እንደገና በፌዴረሽን ይሁን በኮንፌዴሬሽን ከተዋሃዱ በቀዳሚነት የሚፈለገዉና የሚመረጠው አማራጭ እንደሆነ ያስቀመጡ ሲሆን፣ አሰብ ወደ ኢትዮጵያ እንድትሆን የሚያደርግ፣ ኤርትራን በሌላ መልኩ የሚጠቅም የመሬት ማሸጋሸግ ሥራዎችን መስራቱን እንደ ሁለተኛ አማራጭ ያቀርባሉ።
ካስፈለገም ደግሞ በሶስተኛ አማራጭነት፣ አሰብ እራሷን በራሷ እንድታስደዳር ተደርጎ፣ ሁለቱም አገሮች ባለቤት የሚሁኑበትን ፎርሙላ ማመቻቸት እንደሚቻልም የሕግ ባለሞያዉ ይናገራሉ።
ሶስቱ የተዘረዘሩ አማራጮች ካልሰሩ፣ የአለም አቀፍ ሕግና ታሪክ ኢትዮጵያን ስለሚደግፍ ፣ ጉዳይ ወደ ተባበሩት መንግስታት ይዞ መሄድ እንደሚቻል፣ ያስረዱት ዶር ያእቆብ፣ የአልጀርስ ስምምነትን «የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅምን የማያስጠብቅ» ሲሉ ተቀበይነት እንደሌለዉና አሳሪ እንዳለሆነም አረጋግጠዋል።
በቅርቡ አምባሳደር ሺን እና ሄርማ ኮን፣ ኢትዮጵያ አሰብን እንድተከራይ በሚል ያቀረቡትን ሃሳብ ዶር ያእቆብ «ኢትዮጵያን መናቅ ነዉ» ሲሉ አጣጥለዉታል።

No comments:

Post a Comment