ዳኛቸው ቢያድግልኝ
በቅርቡ የሴቶችን ቀን አስመልክቶ በተደረገ የሩጫ ዝግጅት ወቅት የሚኒሊክና የጣይቱ ልጆችነ ነን ያሉ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች “አትለያዩን! አትከፋፍሉን! ነፃነት እንሻለን! ለድሃው ይታሰብለት! ኑሮ ከበደን! ውሃ ጠማን! መብራት ናፈቀን!” በማለት በጣም ሰብዓዊና እናታዊ ጥሪ ጮክ ብለው አሰምተው ነበር። ይህም መልካም ድርጊታቸው ለፍትህና ለአንድነት የሚደረግ ህዝባዊ ጥሪ በሚያስበርግጋቸው የወያኔ ባለስልጣናት ሁከት ፈጠራ ተብሎ ተወነጀሉ። ፕሮፌሰር አልማርያም በተቆጣው ብዕራቸው
… ያገሬ ወይዛዝርቶች በምህረት አልባ ጨካኞች ሲንገላቱና ሲወገሩ ከዳር ቆሜ ማየትን ህሊናዬ ፈጽሞ አይፈቅድልኝም። ይልቁንም የእንግልታቸው ምክንያት ሰብዓዊ በሆነው መብታቸው ድምፃቸውን ስላሰሙ በመሆኑ የነሱና የመሰሎቻቸውን ጥሪ በዚህም ሳቢያ የሚደርስባቸውን አበሳ ሁሉ ለአለም አሳውቅ ዘንድ ድምጼን ከፍ አድርጌ እጮሃለሁ… ብለው ነበር።