Friday, June 20, 2014

አህያ ለምን ኩሊ ሆነ

አንዳንድ ጥያቄዎች በጣም አስቸጋሪ ናቸው ። ለምሳሌ አህያ ለምን ኩሊ ሆነ ተብዬ ተጠይቄ አውቃለሁ ። የሚገርመው ጥያቄውን የጠየቀኝ አንድ የ ሁለታኛ ክፍል ተማሪ ነው። እውነት እኮ ነ " እንደነዚህ ልጆች/ ሕጣናቶች ካላሰባችሁ መንግስተ ሰማያት አትገቡም " የተባለው። በይበልጥ እንደዚህ ልጅ ። ግን አህያ ለምን ኩሊ ሆነ ? ሌሎች የጋማ ከብቶች እንደ አህያ ለሸክም የሚመች ጀርባ ስለሌላቸው ወይስ አህያ ሸክምን የ አርባ ቀን እድሌ ነው ብሎ ተቀብሎት ? በ እሪት ዘፍጥረት አባትችን አዳም የእንስሳ ስም ያወጣ እንደነበር ታላቁ መጽሐፍ ይናገራል ። ምናልባት ለሚስቱ ስም ያወጣ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ወንድ አዳም ይሆናል ። ( በዚህ ጉደኛ እና ሙደኛ ዓለም ላይ ስለ ብዙ ነገር እርግጠኛ መህን ባይቻልም)። ቢቻልስ ምንም የምትቀይረው ነገር የለም። ለምሳሌ የሰው ልጅ ስለ አየር ትንበያ ያለው እውቀት እየላቀ መምጣቱ አዳም ስም ሲሰይም ከነበረው የመጀመሪያ እውቀቱ ብዙ የራቀም አይደለም ።
እንደውም አዳም ምንም ቴክኖሎጂና መረጃ በሌለበት ዘመን ተፈጥሮ ነው አህያን " አህያ!" ብሎ ተገቢና አሸካሚ ስም የሰጠልን፣ እንደውም አዳም ባይኖር ኖሮ ፣ ዜመዶቼ የአደአ ጤፍን በምን ይጭኑት እንደነበር ሳስብ ለነሱ እኔ አማሪካ ሆኘ ይደክመኛል ። ግን እድሜ ለ አህያ ፣ ስሙንም ጀርባውን አሰማምሮ ተፈጠረ ። አህያ ባይኖር ኖሮ " አንተ አህያ!" ብለህ የምትሰድበውም ሰው አይኖርህም ነበር ። እድሜ ለ አህያ ስለዚህ " ብዙ አህዮች አሉ " " እነዚህ አህዮች " " አህያ መሰልኩት " " እንደ አህያ " " በአህያ ቆዳ የተሰራ ቤት ሲፈርስ ያድራል ጅብ የጮከ ለት " " እንደ አህያ አታናፋ " " ምነው እንደ አህያ አፍንጫህን ትነፋለህ " ደሞ በትግረኛ " ወዲ ሀድጊ ( የአማራ ልጅ ለማለት የሰሜን አዳሞች የሚጠቀሙበት ትግርኛ ነው ) በይበልጥ በትግሉ ጊዜ ። እንደውም አህይቱዋን መሳሪያ እየጫኑ ምስጢር ሲያወሩ " ደሞ ወሬያችንን ይዘሽ ለዘመዶችሽ እንዳትነግሪ " ይሉ ነበር አሉ ። አህያ የትም ቦታ ክብር የለውም ፣ ማንልባት ኩባ እሱም የኩባው አዳም ከሌሎቹ አዳም ዘገምተኛ ካልነበረ በስተቀር ይሄን የመሰለ ጀርባውን እያያ እንዴት ለወጥነት የሚሆን ስም እንደሰጠው እንጃ !
ግን አህያ ለምን ኩሊ ሆነ ? ወደ ጎን መውደቅ እንደሚቻል ስለማያውቅ ወይስ መሸከም እና ደውል ማንጠልጠል ስራው እንደሆነ አምኖ ስለተቀበለ ? በእውነቱ ከሆነ አህያ በጣም የሚያሳዝን እንስሳ ነው። ደክሞት እስኪሞት ድረስ የሚሸከም እንስሳ አህያ ነው። በጠፍር የተላጠ አካሉ ሳይጠግ ደግሞ ደፍጋግሞ የሚጫን እንስሳ አህያ ነው። እኔ በልጅነቴ ከማውቀው አንድ የተረት አህያ በቀር ( እሱም ሰርዶ ሆዱን ነፍቶት ሲያናፋ የዛኑ ሌሊት በጅብ ተበላ ) ሌላ የአህያ እምቢ ባይ አላውቅም ። ክርስቶስ እንኩዋ ከሞላ ከተረፈ እንሰሳ የመረጠው በ አህያ ውርንጭላ መምጣትን ነው ። ታዲያ ጀርባው ቢመች አይደለምን ። በቅሎ እንኩዋ ከአህያ ተወልዳ ዝም ብላ አትጫንልህም ( የ እንቱዋ ልጅ !)። እውነትም " አንተ አህያ !" " አህያ መሰልኩት እንዴ ? " " ሂድ ከዚህ የማነው ነው አህያ !" "አህያ የማይችለው ዝናብ " ወዘተ እና ወዘተርፈ ።

ይቀጥላል
ሄኖክ የሺጥላ

No comments:

Post a Comment