Friday, June 27, 2014

ውስጣዊ ጥራታችን በማጠናከር ጠንክረን እንውጣ !!

ከአስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል
መቐለ 

 በአንድ “ዲሞክራሲያዊ ነኝ” የሚል ፖለቲካዊ ፓርቲ ውስጣዊ የአንድነትና የትግል 
ህይወት ከሌለው ውጤቱ ውድቀት ነው። 
 በ60ዎቹ ዓ.ም በሃገራችን ፀረ የተበላሸ ዘውዳዊ ስርአትና ፋሽሽታዊ ደርግን በመቃወም ይታገሉ የነበሩ ወገኖች አወዳደቅ 
ስንመለከት ፤መጀመርያ መደራጀቱ ሲጀምሩት የሃገራችን ሙሁራን፤ተማሪዎች ፤ወዛደሮች ጨቋኝ ስርአቶችን አስወግደው 
ዲሞክራሲያዊና ህዝባዊ መንግስት ለመመስረት የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ፤ወዛደሮች፤ተማሪዎችና ሌሎች ማ/ሰብ 
በመንቀሳቀስና በመደራጀት መልካም የሚባል የኢትዮጵያ አንድነት የሚያንፀባርቅ እንቅስቃሴ አድርጓል፡፡ 
 የኋላኋላ ግን ደርግ ሁሉም ነገር የዲሞክራሲያዊ ጥያቄ በመዝጋቱ በአንድነት ይንቀሳቀሱ የነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፡ 
ሙሁራኖች መሰረታዊ ባልሆነ ልዩነት፡አንዳንዶቹ “የብሄር ጭቆና ጥያቄ መመለስ አለበት” ፡አንዳንዶች ደግሞ “የመደብ ገዢዎች ከተገረሰሱ ሁሉም ነገር አልጋ 
በአልጋ በሆነ መንገድ ይፈታል”፡በማለት ሌሎች ደግሞ “ለደርግ መታገል አያስፈልግም በውስጡ ሁነን ማስተካከል ይቻላል”፡በማለት ከደርግ ታረቁ፡፡
በሌላ 
በኩል የመገንጠል ጥያቄ የሚያነሱ እንደነ የኦሮሞ ፓርቲዎች፤የህወሓት መሪዎችና የኤርትራ ድርጅቶችን ነበሩ፡፡እነዚህ ሁሉ ይዘውት የነበረ አስተሳሰብ ታሪካዊ 
አመጣጥና መነሻ ያልነበረው በየአከባቢያቸው ፤ብሄራቸው ሄደው የንጉስነት ዘውድ አክሊል ሊሰቅሉ ካልሆነ በስተቀር በዚህ ምክንያት የተማሪዎችን ጥያቄ 
ለሉአላዊነት፤ለአንድነትና እኩልነት የነበረው በጥቂት “እኛ እናውቃለን” የሚሉ የግል ፍላጎታቸው ለመርካት በየአከባቢውና ክልል “ፀረ ደርግ” በሚል ስም ብዙ 
የታጠቁ ተቃዋሚ ሀይሎች ተፈጠሩ፡፡ 
 እነዚህ ተቃዋሚ ሀይሎች ነፍጥ አንስተው የደርግ ስርአትን ለመጣል ልዩነታቸውን በማጥበብ ተባብረው የህብረት ጠላታቸውን እንደመጣል ፤ጠባብ 
የስልጣን ፍላጎታቸው ለማሟላት ሲሉ እርስበርሳቸው በጦርነት ተፋጁ፡፡ህዝብም በየግል ፍላጎታቸው በጎናቸው በማሰለፍ አስጨረሱት፡፡ 
 ይህ አልበቃም ብሏቸው ለሚፈፅሙት ድርጊት በመቃወም የውስጥ ትግል በማንሳት “ፓርቲ ከፓርቲ አንጋጭ ፤ዲሞክራሲያዊ የግጭት አፈታት አቅጣጫ 
እንከተል፤ውስጠ-ዲሞክራሲ ይስፈን ፤ሉአላዊ ሃገርና አንድነት ይኑር” ብለው ጥያቄ ላነሱ ሙሁራን በበረሀና በዱር በገደሉ ደብዛቸው አጠፏቸው፡፡በተለይ 
በኢ.ህ.አ.ፓና በህ.ወ.ሓት “የውስጠ- ፓርቲ ጥራት ይኑር ጠባብ የአከባቢ፤ ብሄርተኝነትና ትምክህተኝነት ይጥፋ ፤በዘመድ አዝማድ መሰባሰብ ይወገድ ፤
በውስጣችን ዲሞክራሲያዊ ህይወት ያልፈጠርን ለህዝብ ዲሞክራሲያዊ ህይወት ልናመጣ አንችልም፤ስለሆነ ለየግላችሁ እርካታ ስትሉ አታፋጁን” ላሉ ወገኖች 
ልክ እንደ ደርግ እምቢ ላለ ጥይት አጉርሰው በማለት ብዙ ስህተት ፈፀሙ፡፡ 
 አብዛኞቹ የደርግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በውስጣቸው በስብሰውና አንባገነን ሆነው ሳለ ለውስጠ ጥራትና ትግል ወደ ጎን በማድረጋቸው ለውጫዊ ጠላቶቻቸው 
መከላከልና መቋቋም ተስኗቸው ተፈረካክሰው ግማሾቹ ወደሚጠሉት ደርግ እጃቸው ሲሰጡ ሌሎቹም በበርሃ ሙተው ሲቀሩ ጥቂቶቹ ደግሞ ወደ ስደት 
ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ 
 አሁን በሃገራችን ያለው “አውራ ፓርቲ” እያለ የሚኮፈስብን የህወሓት ቡድንም ከጥንቱ ከጥዋቱ ጀምሮ “ውስጠ- ዲሞክራሲ ይኑር፤ቡድናዊነት፡
አከባቢያዊነት(አውራጃውነት) ፤የዘመድ አዝማድ አሰራር ይወገድ ፤ለሃገር ሉአላዊነት እንታገል፤ጠባብነት ይወገድ ፤የመገንጠል ጥያቄ ከየት የመጣ ነው? 
የኤርትራ የመገንጠል ጥያቄ የህወሃት መሪዎች ብቻ የሚመልሱት አይደለም ፤በኢትዮጵያ ህዝብና በሚቋቋመው መንግስት ስልጣን ነው፤ፀረ-ደርግ ከሆኑ 
ፓርቲዎች በነፍጥ መምታቱ ይቁም፤አመራራችን በዲሞክራሲያዊ መንገድ በጉባኤ ይመረጥ፤ልዩነታችን በሂደት እያጠበብን ከሁሉም የአንድነት ሃይሎችና ፀረ-
ደርግ ሀይሎች እንተባበር ”ያሉ ብዙ ወገኖች ጠፍቷል፡ተሰድደዋል፡ደብዘቸው ጠፍቷል፡፡ 
 ህወሓቶች ያ የነበረው ተፈጥሮአዊ ባህርያቸው ደርግ ከተወገደ በኋላ እስከ አሁንም እየቀጠሉበት ይገኛሉ፡፡በውስጡ ውስጠ-ዲሞካራሲ የሚባል የለም፡፡
አመራሩ ከቁንጮ እስከ ቀበሌ በዘመድ አዝማድ ጓደኝነት የተሳሰረ አመራር ይከተላል ፤ለህወሃት መሪዎች የሚቃወሙ በዚህ መሬት አይኖራትም፤ተበታትነዋል 
ደብዛቸው ጠፍተዋል፡፡ 
 ተቃዋሚ ፓርቲዎችም በህዝብ ተቀባይነት አግኝተው ለስልጣኑ አስጊ ከሆኑ፤ ህዝብ ፡ተማሪዎች፡ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ባነሱበት ልክ እንደ ደርግና ራሱ 
እንደለመደው እምቢ ላለው ጥይት አጉርሰው እያለ ይገኛል፡፡ 
አንጋፋው ታጋይ 
አስገደ ገ/ስላሴ  እስከአሁንም “ካለ እኔ ሌላ አውራ ፓርቲ የለም” በማለት በውስጡም፤በሃገራችን ለነበሩና ላሉ ፓርቲዎች ስጋት በመፍጠር በነፍጥም እየጠራረገ በውስጡም
የሚቃወሙት አባላቱ እያባረረ የሀገራችን አንጡራ ሀብት አሟጥጦ ለዘርመንዝሩ በማሸከም ውስጡ በስብሶ ከመዋቅሩ ተነጥሎ ከጥቂት ባለስልጣናት ብቻ በአየር
ተንጠልጥሎ ይገኛል፡፡መጨረሻውም እንደ ነመንግስቱ መጥፎ አወዳደቅ ያጋጥመዋል፡፡ 
 በሃገራችን ያሉ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ቢፈተሹስ? 
 በአሁኑ ሰአት ያሉ ተቃዋሚዎች ከነህወሃት፤ኢህአፓ፤ኢድዩ፤ኦነግ፤ሌሎችም እርስ በርሳቸው በፈጠሩት ግጭት እንደወደቁ ፤ተሞክሮ ቀስመው በተጨማሪ 
ለውስጠ-ዲሞክራሲ ሂወትና ጥራት ቦታ ሰጥተው የአንድነትና የትግል ጉዞ አቅጣጫ ተከትለው አለመጓዛቸው የወደቁ መሆናቸው ተረድተውና ተምረው 
ያሉዋቸው መሰረታዊ ያልሆኑ ልዩነቶች በማጥበብ ለአንድነትና ለውሁዷ ኢትዮጵያ እንደመታገል ፈንታ የህወሃት ኢህአደግ መሪዎች ሌጋሲ ተከትለው እየተጓዙ 
ይገኛሉ፡፡ 
 ይኸውም ህወሃት ለውስጠ-ብስባሴው ደብቆ የውጭ ሁኔታ እንደሽፋን ተጠቅሞ ታጋዩና ህዝብ ለውስጠ-ትግል ቦታ እንዳይሰጡት በማጭበርበር ይጓዝ 
እንደነበረ ሁሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ነባር ይሁኑ አዲሶቹ ፓርቲዎች በውስጣቸው በስብሰው እያሉ በራሳቸው “በጥሩ ሁኔታ አለን” የሚሉ ግን 
ደግሞ ውስጣቸው ጥሩ ያልሆነ ሳሉ ፤በውስጣቸው ለሚነሱ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎች “የጥያቄዎች መንስኤ ምንድናቸው ?፤በየትኛው አቅጣጫ ነው የተነሱ?፤
ውስጣችን እስቲ ንፈትሽ፤?”ብለው ለራሳቸው ቅድሚያ ፤ኋላም ለአባሎቻቸውና ለደጋፊዎቻቸው ሰፊ መድረክ ከፍተው እንደመገማገም ፈንታ ፤በአንፃሩ ጥያቄ 
ላነሱ አባሎቻቸው ስማቸው በማጥፋት “የህወሃት ኢህአደግ ቅጥረኞች፡የተገዙ፡ከጂዎች”፡እያሉ በአሽሙር በሚድያ(ፌስ ቡክ) እየተሳደቡ ይገኛሉ፡ 
 የፓርቲ መሪዎች ፈላጭ ቆራጭነት ስልጣናቸው እንዳይነጠቁ ልክ እንደ ህወሃት ያደርገው እንደነበረ (ራሱ የኢትዮጵያ አውራ ፓርቲ ለመሆንና ለጊዜው 
እንደተሳካለት) ፤እነዚህም ራሳቸው የኢትዮጵያ አውራ ፓርቲና አምባገነኖች ለመሆን የህወሃት ሌጋሲን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ይህ ደግሞ የማይሆንና የ21ኛው 
ክ/ዘመን ጭንቅላት የማይቀበለው አስተሳሰብ ነው፡፡ስለሆነ በተለይ አንዳንድ ወገኖች ፈፅሞ የተማረ ሰው የማይሰራው በጨቅላ አስተሳሰብና በግብታውነት ላይና 
ታች የሚሉ ቢቆጠቡ መልካም ነው፡፡ ይህ አመለካከት በኦሮሞ ፓርቲዎች፤በአንድነት፤በዓረና ትግራይ፤በመኢአድ ፤በደቡብ ህብረት፤በሰማያዊ ፓርቲና ሌሎች 
በተጨባጭ የሚታይ ያለውና ፀረ-ውህዷ አንድነቷና ሉአላዊነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያን እንዳትኖር የህወሃት ኢህአደግ ፍላጎት ለማሟላት የሚደረግ ድርጊት 
ነው፡፡ 
 ይህ የህዝባችን የለውጥ ፍላጎት የሚያጨልመው ተግባር ነው፡፡ስለሆነም ሁላችሁ ተቃዋሚ ፓርቲዎች“ ህዝብ ምን ይለናል” ፤ብላችሁ አዳምጡ፡ብቻችሁ 
አትሩጡ፡፡ 
 እነዚህ ፓርቲዎች በውስጣቸው የአባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ዲሞክራሲያዊ መድረክ በመፍጠር ፤ውስጣቸው ከአምባገነንነት ፤አባታውነት ፤ቡድናውነት፤
ከባብያውነት፤ወደ ዘረኝነት የሚወስድ ተፈጥሮአዊ ባህሪ አስወግደው ለውስጠ-ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ህይወትና ጥራት ልክ እንደ ውጫዊ ትግል እኩል ቦታ 
በመስጠት የማጥራት ስራ እየሰሩ ፤ለውጫዊ አንባገነን አውራ ፓርቲ እንደ መምታት ፈንታ በውስጣቸው ስሟቸው እየተጠፋፉ ይገኛሉ፡፡ 
 እነዚህ ፓርቲዎች ፤እንደ ህወሃት ትጥቅ ፤ የሚሸፍናቸው ጫካ ስለሌላቸው እንጂ እያሳዩት ያሉት ባህርያትና ተግባር ልክ እንደ የሀገራችን አውራፓርቲና ገዢ 
ህወሃት ኢህአደግ ብዙ ዜጎች እምቢ ላለው ጥይት አጉርሰው እንዳለው ብዙ ወገኖች ይበሉ(ይጨርሱት) ነበር፡፡ 
 እነዚህ ፓርቲዎች ይህ ሁሉ ከማድረግ ፤በውስጣቸው ዲሞክራሲያዊ ህይወት አስፍነው ጠንካራ የውስጥ ትግል በመጠናከር ልዩነታቸው አስወግደው አገራችን 
ከአንባገነኑ አውራ ፓርቲ ህወሃት ነፃ ቢያወጡት እጅግ ጠቃሚ ነበር፡፡ 
 ነግር ግን እነዚህ ወገኖች ምንም ልዩነት የሌላቸው የየክልላቸውና ብሄራቸው ንጉሶች ሁነው ከላይ እንደ ጠቀስኩት በኪሳቸው የዘውድ አክሊል ይዘው 
ንጉሳን ለመሆንና ዘውዱን ለመስቀል(ለመግዛት) ለውስጠ-ዲሞክራሲ እንቅፋት እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ 
 በአሁኑ ጊዜ ፓርቲዎች የሚያሳዩዋቸው ያሉ ተግባራት በውስጣቸው ነፃነት ፈጥረው ለሚነሱ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎች ሰክነው አዳምጠው ለጥያቄዎችና 
ግርጭቶች ዲሞክራሲያዊ መልስ እንደ መስጠት በአየር ላይ ተንሳፍፈው ብቻቸው ቢሮጡ፤በኢንተርኔት፤ ፌስቡክና ጋዜጦች መግለጫ ቢሰጡ፤ ዜናዎች ቢዘግቡ፤
መሰረታዊ መፍትሄ ሊያመጡ አይችሉም፡፡ዋናው ጠንቅ ደግሞ አሽሙርና ሀሜት በአንድ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ መኖር የሌለበትና እጅጉን አፍራሽ ነው፡፡ 
 በመግለጫዎችና በሚድያ ልክ እንደ ህወሃት መሪዎች ከአፋቸው ወደ ጆሯቸው ፤ከጆሯቸው ወደ አፋቸው እያዳመጡና እየተኮፈሱ ከመርካት ለውስጣዊ 
ትግልና ጥራት ቅድሚያ ቦታ ሰጥተው በመታገል የውጭ ትግልን መጠናከር ሲገባቸው አንዳንድ ግለሰዎችና ቡድኖች በፓርቲዎች ለሚነሱ ዲሞክራሲያዊ 
ጥያቄዎች ሰክነውና ተረጋግተው የተነሱ ጥያቄዎች ከምንጫቸው መርምረው ፍትህ እንደ መስጠት ፋንታ ልክ እንደ የህወሃት መሪዎች ያደርጉት እንደ ነበረ ፤
ጥያቄ ላነሱ ፤ሃሳብ ላመነጩ፤ተቃውሞ ያሳዩ፤ያለ አንዳች መሸማቀቅ ትናንት ሲያወዱሷቸውና ሲያደንቋቸው እንዳልነበረ ፤ዛሬ ስማቸው በማጥፋት “ከጂዎች፡
ተገዢዎች፡አንጃ(ሓንፈሽቲ)፡ ሰላዮች ወዘተ” እያሉ ስማቸው እያጠፏቸው ይገኛሉ፡፡  እንደዚህ አይነት ስም ማጥፋት የህወሃት ሌጋሲ በመከተል በውስጣቸው ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ እንዳይነሳ መዝጋትና አምባገነንትን ማስፈን ነው፡፡ ይህ ስራ
ለህወሓት ቡድን እድሜ ማራዘምያ መድሀኒት (ድጋፍን መስጠት) ያመለክታል፡፡እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ በሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቋርጦ ፤ውስጣዊ
ጥራታችን በማጠናከር በውስጣችን ያለው አንባገነንነትና አባታውነት አስወግደን ኢህአደግን አሸንፈን ስልጣኑ ለህዝብ እናስረክበው ፡፡ 
 አንዳንድ ወገኖች በግብታውነት ወደ የፓርቲዎች ከፍተኛ የአመራር እርከን ወጥተው በተሰጣቸው ሃላፊነት የብዙሃኑን ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ በአግባቡ መልስ 
ሰጥተው ብቁ አመራር እንደ መስጠት ፈንታ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ አንስተው በፓርቲዎች የሚከሰቱ ስህተቶች ለማስተካከል ሞክረው ስላልተሳካላቸው ከትግሉ 
ራሳቸው ሲያገሉ፤ወደ ነበሩበት አላማ እንዲመለሱ ማበረታታት ሲገባ እንደገና ሰብአዊ መብታቸው መንካት ተገቢ አይደለም፡፡ ማንም ዜጋ ወዳመነበት ፓርቲ 
ሲሰለፍ በእምነቱ ነበር፤ከፓርቲው ለመልቀቅ ከፈለገም መብቱ ነው፡፡ለዚህ ሰው ምንም በቄ መረጃ የሌላቸው “የገዢ ፓርቲ ቅጥረኛ ሆነዋል፤በገንዘብ 
ተደልለዋል” እያሉ ለዜጎች ስም ሚያጠፉ ያልበሰሉ፤ በፀረ-ዲሞክራሲና ቂም በቀል የተጠመቁ፤ ራሳቸው ከፀረ-ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ያልወጡና ነፃ ያልሆኑ 
ናቸው፡፡ 
 ለዚህ ጉዳይ የሚያባብሱ ወገኖች ለተሰለፉበት ፓርቲ ደንግጠው ሳይሆን ለራሳቸው ርካሽ ታዋቂነት ሲሉ የሚናገሩትና የሚፅፉት የምያስንቃቸው፤ክብራቸውና 
ዝናቸው ያወርደዋል፡፡ስለሆነም ለሰዎች በቀጥታ ይሁን በአሽሙር(ተዘዋዋሪ) ስም ማጥፋት ለራሳቸው ሲሉ ቢያቁሙ ይመረጣል፡፡ያልበሰለ ሀሳብ ይዛችሁ 
ወጣወጣ ማለት ያስገመግሟችኋል፡፡ 

 የፓርቲ መሪዎች ሁነው በእንካሰላንትያ መስመር መሳታቸው ያሳዝነኛል፡፡ይህ ደግሞ “የግለሰው መብት መከበር አለበት” የሚል መርህም መጋፋታቸውን 
ያመለክታል፡፡ 
 በተጨማሪ በከፍተኛ የፓርቲ አመራር ላይ ተቀምጠው ሰክነውና ቆም ብለው አስበው ግጭቱን እንደ መፍታት ደጋፊ እንደማሰለፍ በአሽሙር በፌስ ቡክ 
ማጭበርበርና ስም ማጥፋት ትክክል አይደለም፡፡ 
 ሌላ በሃገራችን ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተናጠል “እኔ ነኝ አውራ ፓርቲ ”እያሉ ከመበጣበጥ ይታቀቡ፡፡ይህም የህወሃት መሪዎች ሌጋሲነት ነው፡፡ዘመኑ 21 
ክ/ዘመን ስለሆነ አምባገነኖችና አባታውያን ቦታ የላቸውም፡፡ ጠንክረን ውስጣዊ ጥራታችን በመጠበቅ ለውጫዊ አውራ ፓርቲ እንታገል፡፡ 
 ከአስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል 

No comments:

Post a Comment