Wednesday, December 18, 2013

ሰላማዊ ትግል፣ ምርጫ እና መፈንቅለ-መንግስት

 በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርት (አንድነት) በሰላማዊ ትግልና ባህሪያቱ ክፍል አራት በአቶ ግርማ ሞገስ በስካይፕ የሚሰጠው ስልጠና ተጠናቋል። ዝርዝሩ ዝቅ ብሎ ቀርቧል። ስልጠና ክፍል አራት፥ ሰላማዊ ትግል፣ ምርጫ እና መፈንቅለ-መንግስት ቅዳሜ ታህሳስ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. [December 14, 2013] የስልጠና ክፍል አራት ግብ የሚከተሉትን ማጥናት ነው፥ (1ኛ) ስለ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምንነት እና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለውጥ የሚያመጣባቸው 3 መንገዶች፣ (2ኛ) በዴሞክራሲ አገሮች የሚደረጉ ምርጫዎች ግባቸው እና ፎርሙላቸው ምን እንደሆነ፣ (3ኛ) አምባገነን መንግስቶች የሚያደርጉዋቸው ምርጫዎች ግባቸው እና ፎርሙላቸው ምን እንደሆነ፣ (4ኛ) አምባገነን መንግስቶች በሚጠራቸው ምርጫዎች ተቃዋሚ የምርጫ ፓርቲዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና በመጨረሻ (5ኛ) በህዝብ የተመረጠን መንግስት ከስልጣን ለማውረድ የሚፈጸምን መፈንቅለ-መንግስት እንዴት በሰላማዊ ትግል መከላከል እና ማስወገድ እንደሚቻል ማጥናት። ሰላማዊ ትግል እና ባህሪያቱ ethioforum

No comments:

Post a Comment