Wednesday, December 4, 2013

በመርካቶ ከፍተኛ ቃጠሎ ተከሰተ

በአዲስ አበባ መርካቶ የተነሳው የ እሳት ቃጠሎን ይህ ዜና ለዘ-ሐበሻ እከደረሰበት ሰዓት ድረስ የከተማዋ የ እሳት አደጋ ሊቆጣጠረው አለመቻሉን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ አስታወቁ። ዘጋቢዎቻችን እንዳሉት መሃል መርካቶ ከከምዕራብ ሆቴል ወደ በርበሬ በረንዳ በሚወስደው መንገድ ወይም በተለምዶው ቦምብ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በተነሳ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ከፍተኛ ንብረት እየወደመ ነው። በዛው አካባቢ በሚገኙት ሜትሮ ሆቴል. ሐረር ዳቦ ቤት፣ ዓለም ሽንሽንና ጌጣጌጥ መሸጫ መደብሮች በዚህ ቃጠሎ የተጠቁ ሲሆን ከአንድ ሰዓት በላይ በፈጀው የእሳት ማጥፋት ሥራ ቃጠሎውን ሊቆጣጠሩት አለመቻላቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ትናንት ማክሰኞ በትራንስፎርመር መቃጠል ምክንያት 70 ዎርክሾፖች በ06 ቀበሌ (ኢንዱስትሪ ዞን) በእሳት ቃጠሎ መውደማቸውን አብረሃ ደስታ ከመቀሌ መዘገቡን ዘ-ሐበሻ ላይ አስነብበን ነበር። ዛሬም አብርሃ ከመቀሌ እንደጻፈው “ዛሬ ሮብ ሌሊት ደግሞ በዓዲ ሐቂ ገበያ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደርሶ ብዙ ንግድ ቤቶች ወድመዋል። በተመሳሳይ አጋጣሚ ዛሬ ሮብ ጠዋት በዓዲሹምድሑን ሰፈር በእሳት ቃጠሎ አደጋ ንብረት ወድመዋል።” ብሏል።
አብርሃ ‘መቐሌ በሁለት ቀናት ዉስጥ በሦስት አቅጣጫዎች (ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ) የእሳት አደጋ ሰለባ ሆናለች። የማክሰኞው አደጋ በትራንስፎርመር መቃጠል ምክንያት ሲሆን የዛሬው የዓዲ ሐቂና የዓዲሹምድሑን ቃጠሎ መንስ ኤ ግን እስካሁን በትክክል አልታወቀም።” የደረሰበትን መረጃ በፌስቡክ ገጹ አካፍሏል።
አብርሃ የመቀሌውን ዜና ከዘገበ በኋላ በአንዳንድ ሰዎች የተሰጠውን አስተያየት ሲተች “መቐለ በ18 ሰዓታት ዉስጥ ሦስት የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች አስተናግዳለች (06፣ ዓዲሐቂና ዓዲሹምድሑን)። ህዝብ ተጨንቀዋል፣ አዝነዋል፣ ተገርመዋል። ባለስልጣናቱ ግን ምንም ዓይነት ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ እንኳን ዝግጁ አይመስሉም። ካድሬዎቹም አደጋው ከመከላከል ይልቅ ‘ንብረት ወደመ’ ስንል ‘ቃላት ተሳሳቱ’ እያሉ ያሸፉብናል። በመቐለ ከተማ በወደመው ንብረት ለማዘን ስለ እሳት አደጋው መስማት በቂ ነው። ስለ ቃላት አመራረጥ ማተኮር ግን ጥሩ አይመስለኝም። ምክንያቱም ጥረታችን ፅሑፍ መፃፍ ሳይሆን ስለ ደረሰው አደጋ መረጃ መስጠት ነው።” ብሏል።
(ዘ-ሐበሻ) 

No comments:

Post a Comment