Sunday, January 11, 2015

ጣይቱ ሆቴል በእሳት አደጋ ወደመ

በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊው እና የመጀመሪያው ዘመናዊ ሆቴል – የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል መሆኑ ይታወቃል:: ሆቴሉ 109 አመታትን ያስቆጠረ ነው:: ይህ ጥንታዊ ሆቴል ዛሬ ጠዋት በተነሳ ቃጠሎ ጋይቷል:: በፒያሳ እና በአካባቢው ጥቁር ጢስ ወደ ሰማይ እየተንቧለለ አሁንም ድረስ እየታየ ሲሆን; በዚህ ጥንታዊ ቅርስ መውደም ብዙዎች ከልብ አዝነዋል:: አንዳንድ የአይን ምስክሮች እንደሚሉት ከሆነ – የ እሳት አደጋ መኪና በቅርብ ርቀት ላይ (አራዳ ጊዮርጊስ) የሚገኝ ሲሆን በቃጠሎውም ወቅት በቦታው ደርሶ ነበር:: ነገር ግን እዚያ ደርሰው በሚከፈላቸው ገንዘብ ላይ ሲደራደሩ እሳቱ እየተባባሰ መምጣቱን ገልጸዋል::



No comments:

Post a Comment