Tuesday, June 30, 2015

“መንግስታዊ ቅሌት !”

“መንግስታዊ ቅሌት !”
ህውሓት/ኢህአዴግ በአገራችን ኢትዮጵያ ዜጎች በአደባባይ ወጥተው መንግስትን የመቃወም እና የመተቸት አለም አቀፍ እንዲሁም ህገ-መንግስታዊ መብት ጨፍልቆ፣የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ማሰር፣መግደል እና ከአገር እንዲሰደዱ ማድረግ ዋና ዋና የመንግስት ስራ ከሆነ ዓመታት ተቆጥሯአል፡፡
በኢትዮጵያ የሚኖሩ “ኤርትራዊያን” የአገራቸውን መንግስት እንዲቃወሙ የአደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ በመፍቀድ ፣ ሃሳብ ማመንጨት እና ማስተባበር እንዲሁም ቦታን መፍቀደ የህውሓት/ኢህአዴግ ጭንቀት ከሆነ ቆየ !

በእርግጥ ይህ ዓይነት መንግስታዊ ውንብድና ሲፈፀም የመጀመሪያ አይደለም ፣ ከዚህ ቀደም ግንቦት ወር ቀኑን ለጊዜው ባላስታውሰውም 2005 ዓ.ም ተመሳሳይ መንግስታዊ ቅሌት ተፈፅሟል፡፡

No comments:

Post a Comment