Sunday, June 7, 2015

አምባገነኑ የህወሓት አገዛዝ ለስልጣኑ መጠበቂያ ያቋቋመው መከላከያ ሠራዊት እየፈረሰ የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ላይ ነው፡፡

የህዝብ ጠላት የሆነው ህወሓት ከህዝብ አብራክ የተከፈለውን መከላከያ ሠራዊት በፀረ-ህዝብነት ሙሉ ለሙሉ የማሰለፉ ዓላማው ሲከሽፍ በዓይኖቹ በብረቱ በመመልከት ላይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰሞኑን በርካታ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው በመኮብለል አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቅለዋል፡፡ ህዝብን ለማጥፋት የቆመውን ህወሓትን ከድተው ለህዝብ ከቆመው አርበኞች ግንቦትት 7 ጎን ከተሰለፉት ከእነዚህ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የአግአዚ ኮማንዶ ክፍለ ጦር አባላት ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡

ከሁሉም የታጠቁ ኃይሎች ለስርዓቱ የበለጠ ቅርብና ታማኝ ነው የሚባለው እንዲሁም ምርጫ በመጣ ቁጥር በከተሞች እየተሰማራ ህዝብ እየጨፈጨፈ አመፅ የሚያከሽፈው አግአዚ ኮማንዶ ጦር እየከዳ የነፃነት ትግሉን መቀላቀል መጀመር የህወሓት አገዛዝ ልጡ የተራሰና መቃብሩ የተማሰ ያበቃለት መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ህወሃት በሚያራምደው በጎሰኝነት የተቃኘ ቅጥ ያጣ የምጣኔ ሀብት ስርዓት ምክንያትና በአገዛዙ በሚደርስባቸው ጫና እንደመከላከያ ሠራዊቱ ሁሉ እየኮበለሉ በረሃ በመግባት ላይ ናቸው፡፡ በመሆኑም በርካታ ባለሀብቶች አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment