Tuesday, June 30, 2015

ሃይ ባይ ያጣው የአለም ህዝቦች ስጋት!

አለም ዝም ያለው, ታላላቅ ሀያላን ሀገራት ሁሉ ፀጥ ብለው ተመልካች የሁኑበት አረመኔያዊው እውነተኛው ትርኢት በጭራሽ አላባራም. እንዲያውም ብሶበታል. ሶሪያ ደበነች, ኢራቅን ፈጁት, ሊቢያ ን አናወዟት, ግብፆችን አረዱ, ኢትዮጵያዊንኑ ወንድሞቻችን ደገሙ. ኮሪያ, አሜሪካ, ኤርትራ ብቻ ያልነካኩት የለም ግን ዝም ተብለዋል. ሀይ ባይ አልተገኘም.
አንድ ቡድን አለምን ሲያስጨነቅ አለም መሪዎች ያጣች ይመስላል. ነገሩ ግራ የገባ ነው. ልምምዳቸው በሜዳ ነው.ይባስ ብለው ለዚሁ ሽብር ተግባር የሚጠቅሙ ህፃናት እያሳደጉ ነው. አልተሸሸጉም. ሆኖም ዝም ተብሏል.

ይሄው እያደገ የሚሄደው አረመኔያዊ አገዳደል መልኩን ከእርድ ቀይሯል. በደማሚት, በእሳት, በውሃ መድፈቅ ጀምሯል.ደአሽ ሰውን ሲገድል ብዙ ልቦችን እንደሚገድል ያውቃል. ከሚሞተው ሰው በላይ ቀሪውን የአለም ህዝብ ለማቃጠል, ሁሌ እያሰብን እየዘገነን እንድንኖር እያደረገ ነው. ሀይ ባይ እስከሌለ ድረስ ገና ይቀጥላል. ፈጣሪ የበላዩ ጌታ ሀይ ይበልልን እንጂ.
ይሄው የትናንቱ ደግሞ ከመቸውም ጊዜ የከፋ ነው. 16 ኢራቃዊያንን በሶስት በተለያየ አይነት መንገድ የገደሏቸው አገዳደል. ምክኒያታቸው የኢራቅ መንግስት ሰላይ ናችው የሚል ሰበብ ነው ያቀረቡት. ባይሆኑስ ይተዋቸው ነበር?
* የመጀመሪያ አራቱን ሰዎች እጅና እግራቸውን አስረው በአንድ መኪና ውስጥ አስገብተው ቆልፈው መኪናውን በመሳሪያ አጋዩት, እየተቀጣጠሉ ጩኸታቸው እየተሰማ ደበኑ.
* ሁለተኛዎችን በብረት የተሰራ አጥር መሳይ አራት መአዘን ቤት ውስጥ እንደ ውሻ እያሰሩ ካስገቧቸው በሗላ በሚዘገንን ሁኔታ በውሃ ውስጥ ለቀቁዋቸው.
* ሶስተኛውና በጣም ዘግናኙ ደግሞ ሁሉንም በተቀጣጣይ የደማሚት ሽቦ አንገታቸውን አስረው ጠላልፈው ለኮሱ, በጫጨቋቸው. እንደው በእነዚህ ሰዎች ላይ ሁሉም አለም ተቆጥቶ እንዲነሳ ምን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ግራ ይገባል. ምንም አላስቀሩ ሁሉንም ወንጀል ደስ እያላቸው ፈፅመውታል. ይህ ሁሉ ሆኖ አሁንም አልተዘመተባቸውም.የኢራቅን የሳዳምን ሀያል ጦር የፈረካከሰው, የጋዳፊን ግዛት በአንዴ ያሽመደመደው የአለም የተባበሩቱ ጦር እንዴት ደአሽ አቃተው? ISIS ምነው ከበደው? ሁሌም ጥያቄ ይጭራል.
ሰላሙን ያብዛልን

No comments:

Post a Comment