Tuesday, June 30, 2015

ፖሊስና አቃቤ ህግ በኢህአዴግ ላይ ሰልፍ መውጣታቸውን ቀጥለዋል!

አይ ኤስን ለመቃወም ከተጠራው ሰልፍ በኋላ ፖሊስና አቃቤ ህግ በየ ችሎቱ ኢህአዴግ ላይ ሰልፍ በመጥራት ስድብ እያዘነቡበት ነው፡፡ በሚያዝያ 14ቱ ሰልፍ ላይ በቦታው ያልነበሩት የሰማያዊ፣ የቀድሞው አንድነትና የቀድሞው መኢአድ አባላትና አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ወጣቶችን ያስሩና እነዚህ ወጣቶች ያላሉትን ክስ ብለው ያቀርባሉ፡፡ ይህ ክስ ደግሞ ለእነሱ የሰልፍ መፈክር መሆኑ ነው፡፡ የስድብ ውርጅብኝ፡፡ በቃ ችሎት የቁጭት መውጫቸው ሆኗል ማለት ይቻላል!
ፖሊስና አቃቤ ህግ በየ ችሎቱ (ሰልፍ እንበለው) ከሚያሰሟቸው መፈክሮች መካከል፡-
• ኢህአዴግ ሌባ ነው!
• ጠንካራ እንጅ ጠንጋራ መሪ አንፈልግም
• ቴዎድሮስ ለህዝብ ሞተ፣ መለስ ደንግጦ ሞተ፣ ሀይለማሪያም በቁሙ ሞተ!
• እያዋረደን ያለው ወያኔ ነው!
• ወያኔ አሳረደን!
• ኢህአዴግ ቡሽቲ መንግስት ነው! (አሁን ይህም ክስ ላይ ይቀርባል! ዳንኤል ብርሃኔን መሰሉኝኮ)
• የወያኔ 24 አመት አገዛዝ ይበቃናል!
• የሀገር አበሳ የውጭ ሬሳ
• ኢህአዴግ….
• ኢህአዴግ….እና የመሳሰሉት ስድቦች (ማለቴ መፈክሮች) ይገኙበታል!

አንድ ጓደኛዬ በተደጋጋሚ ችሎት ላይ ተገኝቶ አቃቤ ህግና ፖሊስ ‹‹ጠንካራ እንጅ ጠንጋራ መሪ አንፈልግም!›› ብለዋል እያሉ መፈክር ሲያሰሙ ያዳምጥና ‹‹በዚህ መፈክር የተከሰስኩት እኔ ብሆን መከላከያ ምስክር የማደርጋቸው ጠንካራ መሪ አይደሉም የሚባሉትን ሰው ነበር፡፡ ችሎት ላይ አቅርቤ እሺ ጠንካራ ናቸው ወይንስ…. እላቸው ነበር›› ብሏል፡፡
ዛሬ እነ ቴዎድሮስ አስፋው ላይ ደግሞ ‹‹ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው፣ መለስ ደንግጦ ነው የሞተው፣ ኃይለማሪያም በቁሙ ነው የሞተው›› ብላችኋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ መርዶ እኮነው ስንሰማው የዋልነው፡፡ ለፖሊስና ለአቃቤ ህግ ደግሞ የብሶት መፈክር መሆኑ ነው! ሌላው ቀርቶ ‹‹ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው!›› የሚለውም የክስ መዝገብ ላይ መስፈሩ ያሳፍራል፡፡ ለማንኛውም በዚህ ክስ ላይም ያ ጓደኛዬ መቃወሚያ ቢጤ አቅርቧል፡፡
‹‹መለስ ደንግጦ አልሞተም ስትሉ፣ ኃይለማሪያም በቁሙ አልሞተም ስትሉ የሀኪም ማስረጃ አምጡ!›› እላቸው ነበር ብሏል! ያው የመለስን ገዳይ በቅርብ አላገኘውም ብሎ ይሆናል!
ጌታቸው ሺፈራው

No comments:

Post a Comment