Monday, January 28, 2013

የፍርሃት እስረኛ መሆን የለብንም !!!


እንኳን ሰው ፈረስ እንኳን አልለጎምም ካለ ማንም እንደፈለገው አይጋልበውም። ሲያስፈራሩን ካልፈራናቸው፣ አትናገርሩ ሲሉ ከተናገርን፣ አትጻፉ ሲሉ ከጻፍን፣አትንቁ ሲሉ ከነቃን፣ ተከፋፈሉ ሲሉ ከአበርን፣ ፍሩን ሲሉ ከደፈርናቸው፣ ተንበርከኩ ሲሉ ከቆምን፣ አወድሱን ሲሉ ካወገዝናቸው...እንደ ጥንት አባቶቻችን እንቢ አሻፈረኝ ብለን በጋራ ከአመጽንባቸው እነርሱ ጥቂቶቹ አኛን ብዙሃኑን ፈጽሞ ሊረግጡን አይቻላቸውም። አንድ ህዝብ በጨቋኞች ጫማ ስር ወድቆ የሚረገጠው ጨቋኞቹ ስለበረቱ ሳይሆን የፍርሃት እስረኛ ከሆነ ብቻ ነው።
ነጻነትን የሚናፍቅ ኢትዮጵያዊ ሁሉ መጀመሪያ ሊያሸንፍ የሚገባው በልቡ የነገሰውን ፍርሃት ነው። እውነቱን ለመናገር ሰው በታች ሆኖ እየተረገጡ ከሞኖር ለነጻነት፣ ለክብር፣ ለፍትህና ለእኩልነት ሲፋለሙ በክብር መሞትን ያህል ታላቅ ነገር የለም። 
ወደፊት አገራችንንም የሚመሩ ሰዎችም ክፉ ጌታ የሚሆኑብን ሳይሆኑ ህዝቡን በትህትና ያለ አድልኦ እንደባሪያ የሚያገለግሉ መሆን ይገባቸዋል። 
የነጻነታችን ቁልፍ አንድነታችን መሆኑን ተገንዝበን ኢትዮጵያን በነጻነትና በእኩልነት እነደ ዜጋ ተከብረን የበላይና የበታች ሳይኖር የሁላችንም አገር ለማድረግ በጋራ እንነሳ። በህወሃቶች ተንኮል ብቻ ሳይሆን በእራሳችንም በጎ ፈቃድ ተከፋፍለን መረገጥ ይብቃን።
አንባገነኖች የሚሸነፉት የሚረግጡት ህዝብ የፍርሃትን ሰንሰለትን አሽቀንጠሮ ጥሎ ሲያምጽ ብቻ ነው። እኛም በያለንበት ለአመጻ የስነ-ልቦና ዝግጅት ማድረግ ይገባናል። ይ አፋኝና ዘረኛ ስርአት ፈጽሞ ሊቀጥል አይገባውም!
    ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

No comments:

Post a Comment