Thursday, January 3, 2013

‹‹ሹመት ካልሠሩበት ምን ይፈይዳል?››

ሙስና እንደ ሸረሪት ድር በየቦታው አድርቷል፡፡ መልካም አስተዳደር ጠፍቷል፡፡ የሕግ የበላይነት አለ በሚባልበት አገር ፍትሕ ርቋል፡፡ በሕገ መንግሥት የተረጋገጡ መብቶች ተጨፍልቀዋል፡፡ ሥርዓቱን ሙስና እንደነቀዝ እየበላው ስለሆነ የመፍትሔ ያለህ እየተባለ ነው፡፡ እኔ የምለው ተሿሚዎቹ ይህንን ችግር ለማስወገድ ካልሠሩ ሹመታቸው ምንም አይረባንም እላለሁ፡፡ ይህንን ሐሳቤን ለጓደኛዬ ብነግረው በመገረም እያየኝ፣ ‹‹አስተያየትህን በአስቸኳይ ለኢቲቪ ለምን አትልክም?›› አለኝ፡፡ እኔስ ምኔ ሞኝ ነው? ‹‹ኢቲቪ ሐሳቤን ቆራርጦ በ‹‹አበረታች›› ሊተካው ስለሚችል ፌስቡክ ላይ ለጥፈዋለሁ፤›› ስለው አንገቱን እየወዘወዘ ሳቀብኝ፡፡ ወደ ስራችን ስናመራ፣ ‹‹ሹመት ካልሠሩበት ምን ይፈይዳል?›› ስለው፣ ‹‹ምንም! ነገር ግን ያስተዛዝባል፤›› አለኝ፡፡ ሹመት ችግር ካልፈታ ፋይዳቢስነቱ ገዝፎ ታየኝ፡፡ 
                                                  ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment