Wednesday, January 9, 2013

የጋዜጠኛ ርዕዮተ አለሙ የሰበር ይግባኝ ውድቅ ተደረገ


የፌዴራሉ አቃቤ ህግ የአገሪቱ አንድነት እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ተንቀሳቅሳለች ሲል ውጪ ሀገር ለሚገኙና ለአንደኛው ተከሳሽ ኤሊያስ ክፍሌ አማካኝነት መረጃዎችን አቀብላለች ሲል በአንደኛ ክስ እንዲሁም፤ በሽብርተኛ ቡድን ውስጥ በህቡዕ በመሳተፍ አባል በመሆንና አባል በመመልመል ጭምር ተሳትፋለች እና ከኤርትራ መንግስት እና ከግንቦት ሰባት ጋር ምስጢራዊ ግንኙነትን በመጠቀም ከሽብር ቡድኑ የሚገኝን ገንዘብ ተቀብላ ጥቅም ላይ አውላለች የሚሉ ሦስት ክሶችን ያቀረበባት ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ፤ በይግባኝ ሰሚ ሰበር ችሎት ያቀረበችው አቤቱታ ትናንት ውድቅ ሆነ። 

በውጪ ሀገር ለሚገኙ የሽብር ቡድኖች መረጃን ታቀብል ነበር የሚለውን አንደኛ የአቃቤ ህግ ክስ እንዲሁም ከኤርትራና ከግንቦት ሰባት ቡድኖች ጋር በመገናኘት ህጋዊ ያልሆነን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ በመጠቀም የሚለውን ሦስተኛ ክስ ውድቅ ለማድረግ፤ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሀምሌ 27 ቀን 2005 ዓ.ም የ14 አመቱ እስር ወደ አምስት አመት ያወረደው ሲሆን፤ በ2ኛውም ክስ ቢሆን ልጠየቅ አይገባም ስትል የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን የቅጣት ውሳኔ እንዲያሻሽልላት ለፌዴራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ክፍተት አለበት ስትል ያቀረበች ቢሆንም፤ የጋዜጠኛዋን ጉዳዩን ሲመረመር የቆየው ሰበር ሰሚው ችሎት አቤቱታው ምንም አይነት የህግ ስህተት እንዳለ አያሳይም ሲል ውድቅ አድርጐታል።
ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የተለያዩ የአለም አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘች ሲሆን፤ እጇ ተይዞ ወደ እስር ቤት የገባችው ሰኔ 14 ቀን 2003 ዓ.ም እንደሆነ ይታወሳል።
             ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment