Wednesday, January 30, 2013

የኛ ራእይ ሁላችንም ያለ አድልኦ የምንኖርባትን አገር መገንባት ነው ። በሙት መንፈስ መመራት አይደለም !


የኢትዮጵያ ህዝብ ራእይ በአንባገነኖች እንደትንኝ እየተጨፈለቀ መኖር አይደልም። የኛ ራእይ ህወሃቶችን እየፈራንና እየተንቀተቀጥን፣ እየገደሉ፣ እየቆረጡ፣ እያሰቃዩ ኢትዮጵያን ምድራዊ ሲኦል ሲያደርጉ ተለጉመን መኖር አይደለም።
የኛ ራእይ ሁላችንም ያለ አድልኦ በዘራችን ሳይሆን በዜግነታችን ተከብረን በነጻነት፣ በሰላምና በእኩልነት ተከባብረን የምንኖርባትን ሰላምና የህግ ልእልና የሰፈነባትን አዲሲቷን ኢትዮጵያ እውን ማድረግ ነው። ይህን ጣፋጭ ህልማችንን ለማጨንገፍ የሚጥሩ ሁሉ ከውጭ ወራሪ እኩል የሚታዩ እንደ ሕወሃት እና አሻንጉሊቶቹ ያሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች ናቸው።
      ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
            ከዘካሪያስ አሳዬ

No comments:

Post a Comment