Saturday, January 12, 2013

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት በአበበ ገላዉ ላይ በወያኔ ስርአት የተቃጣዉን የግድያ ሴራ አስመልክቶ መግለጫ አወጣ


ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት በጀግናዉ አበበ ገላዉ ላይ በወያኔ ስርአት የተቃጣዉን የግድያ ሴራ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
ENTC
ጥር 10/2013 ዓ/ም (እኤአ)በቅርቡ ጀግናዉ አበበ ገላዉን ለመግደል በህወሀት/ኢህአዴግ የተጠነሰሰ ሴራ በአሜሪካ በFBI መጋለጡንና ተጠርጣሪዎቹም መያዛቸዉንና ምርመራ ላይ መሆናቸዉ ተገልጿል። ይህን እጅግ አሳፋሪ ተግባር የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት አጥብቆ ያወግዛል። የፋሽሽቱና ዘረኛዉ ህወሀት/ኢህአዴግ ስርአት ምርጫ 97ትን ተከትሎ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተረቆ በአዉሮፓ አሜሪካና በሌሎች ሃገሮች ለሚገኙ የኢትዮጽያ ኤምባሲዎች በሚስጢር የተሰራጨው ባለ 52 ገጽ በአለም ዙሪያ የሚገኙ ተቃዎሚዎችን ለመምታትና ለማዳከም ያወጣዉን እቅድና ዝርዝረ ጉዳዮችን የያዘ የስርአቱ ሰላዮች ሰነድ ሾልኮ በመውጣቱ ለኢትዮጵያኖችና ለአለም አቀፍ ህብረተሰቡ ይፋ መሆኑ የታወሳል።
ስርአቱ በሀገር ውስጥ የሚያደርገውን የሽብርተኝነት ተግባራት በጎረቤት ሀገሮች በማስፋፋት በኬንያ፤ በሱዳን፤ በጅቡቲና ዩጋንዳ በሚገኙ ኢትዮጽያዉያን ስደተኞችና ተቃዋሚዎች ላይ የሚሰራቸዉ ያሸባሪነት፤ የገዳይነትና፤ ከስደተኞች ካምፖችና ከያሉበት አፍኖ በመዉሰድ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች እንዲሞቱ የማድረግ ተግባራቶች ያለምንም ተጠያቂነት እየቀጠለ እያለ፤ በታላቋ አሜሪካን ሀገር እጅግ አሳፋሪና ፍፁም የአሸባሪነትና የእብሪት ተግባር ለመፈጸም ሙከራ አድርጓል። ይህም ተግባሩ የስርአቱን ማንነት በገሀድ ያጋለጠ ብቻ ሳይሆን አለም አቀፍ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል ሽፋን በቢሊዮኖች የሚቆጠር የግብር ከፋዮች ገንዘብ ለሚያፈስለት የአሜሪካን ሀገር መንግስት ያለዉን ንቀት በተግባሩ ያረጋገጠ ነው። ለነገሩ ወያኔ/ህወሃት በግድያና፤ የዘር ማጥፋት ፤ እኩይ ተግባሩ በአሜሪካን መንግስት እኤአ ከ 1975 እስከ 1991 ዓ/ም ድረስ በአለም አቀፍ የሽብርተኛ ድርጅትነት መመዝገቡን ለምናስታዉስ ይህ አጸያፊ ተግባሩ ሊገርመን አይገባም።
ስለነጻነት የጻፉ ጋዜጠኞችን ሽብርተኛ ናቸዉ በማለት ለረዥም አመታት ያሰረ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ለመብታቸዉ የሚታገሉትን የሙሰሊም ወገኖቻችንን በሽብርተኝነት ከፈረጀ፤ በደቡብ፤ በአኝዋክ፤ በኦሮሞና በአማራ ህዝብ ላይ የእልቂት ተግባሮችን እራሱ ፈጽሞ የገደላቸዉና ደማቸዉን ያፈሰሰዉ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ኢትዮጵያዉያንን ሽብርተኞች እያለ ከሚፈርጅና ህጻን ልጆችን ከሚገድል ስርአት ምን የተሻለ ተግባር ይጠበቃል? ዋናዉ ቁም ነገር ይህ በአሜሪካን ሀገር የተቃጣዉ የንቀት እኩይ የግድያ ሙከራ የአሜሪካን መንግስትን ሰለወያኔ ስርአት ያለዉን አመለካከትና ፖሊሲውን እንደገና በጥሞና እንዲያጤን ማስገደድ አለበት በማለት ባፅንኦት እንለምናለን። ሁላችንም ተቃዋሚ ሀይሎችና በዉጭ ሀገር የምንገኝ ሀገርና ወገን ወዳድ ዜጎችም ይህንን አለም አቀፋዊ የሽብርተኝነት ተግባር የአሜሪካን መንግስት ከስር መሰረቱ በማጣራት አስፈላጊዉን እርምጃ እንዲወስድ ያላሰለሰ ግፊትና ጫና እንድናደርግና የስርቱን ሰላዮች በማጋለጥ መረጃዎችን ለሚመለከተው ከፍል እንድናስተላልፍ እንጠይቃለን። በዚህ አጋጣሚ ከጀግናዉ አበበ ገላዉ ጋር የምንቆምና ለእሱ ያለንን ክብር በድጋሚ በማረጋገጥ ለወያኔ ስርአት የምናስተላልፈዉ ግልጽ መልእክት በአበበ ላይ የተቃጣዉ የፈሪዎች እኩይ ተግባር ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ጀግና አበበዎችን በቅርቡ በመፍጠር ይህንን ጨካኝ ስርአት ጠራርጎ ከሀገራችን ለማስወገድ በቆራጥነት እንደምንታገል እናረጋግጣለን።
በጋራ ትግላችን ገዳዩንና ዘረኛዉን ስርአት እንስወግዳለን።
ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት አመራር
 ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
              ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment