Sunday, October 5, 2014

ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ የ17 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚያሰቅቅ ሁኔታ እየደረሰ ያለው የመኪና አደጋና በዚሁ ጉዳትም የሚያልቀው ሕዝብ ብዛት እጅጉን አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው። ዛሬም ወደ አዲስ አበባ 65 መንገደኞችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ 17 ሰዎች ወዲያውኑ መሞታቸው ታውቋል።
Car accident
በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንኳ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ ከዘገብናቸው ዘግናኝ የመኪና አደጋዎች ውስጥ፦
ከሞያሌ ወደ ሻሸመኔ የሚጓዝ አገር አቋራጭ አውቶቡስ ተገልብጦ 17 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ፤
ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር የሚጓዝ አውቶቡስ ተገልብጦ 41 ሰዎች ማለቃቸው፤
በአዲስ አበባ ከካራ ወደ መርካቶ የሚጓዝ አውቶቡስ 15 ሜትር ጥልቀት ካለው ገደል ገብቶ የሰዎች ሕይወት ማለፉ፤
ወደ ደብረማርቆስ የሚጓዝ አውቶቡስ ተገልብጦ የ13 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱና ሌሎችም ይገኙበታል።

ዛሬ ከሃገር ቤት የተሰማው ዜና እንደሚያስረዳው ከደባርቅ ወደ አዲስ አበባ 65 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተገልብጦ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። አደጋው የደረሰው ዛሬ ከቀኑ 6:30 ላይ አውቶብሱ በአማራ ክልል፣ ደጀን ወረዳ፣ ባልበሌ ቀበሌ አካባቢ በሚገኝና 50 ሜትር ጥልቀት ባለው ገደል ገብቶ ነው።
መንግስታዊ ሚድያዎች እንደዘገቡት በዚህ አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ 37 ሰዎችም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

No comments:

Post a Comment