Saturday, October 18, 2014

አማረ አረጋዊ በበላበት መጮኹን ቀጥሏል!

ይሄይስ አእምሮ
Amare Aregawi“ውሻ በበላበት ይጮኻል” እንደሚባለው አማረ አረጋዊም የወያኔን የዘረኞች ሥርዓት ከውድቀቱ ለመታደግ በሚመስል ቀቢፀ ተስፋ ባለ በሌለ ኃይሉ ላንቃው እስኪበጠስ እየጮኸ ነው፡፡  የወያኔ የቁርጥ ቀን ውሾች ሁሉ ካላንዳች ይሉኝታ ጩኸታቸውን ሲያቀልጡት ማየት በተለይ የዚህ ዘረኛ የወሮበሎች ቡድን ፀሐይ መጥለቅ ከጀመረችበት ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በጣም የተለመደ ሆኗል፡፡ ለወያኔ መልካም ሽኝት፤ ለውሾችም መልካም ጩኸት እንዲሆንላቸው ከመመኘት ውጪ ምን ማድረግ ይቻላል?
ትግሬ መሆኔን ያላወቀ አንድ ጓደኛየ ዛሬ ጧት ሻይ ስንጠጣ “አንተ ይሄይስ፣ በትግርኛ መዝገበ ቃላት ‹ይሉኝታ› የሚባል ቃል የለም ሲሉ የሰማሁት እውነት ይሆን እንዴ?” አለኝ፡፡ መናደዴን እንዳያውቅብኝ ተጠንቅቄ “ውሻ፣ የውሻ ልጅ፤ አንተም እንደነሱ ልትሆን ነው?” አልኩት፡፡ “እንደነማን?” ሲለኝ ያላሰብኩበት ጥያቄ ስለነበር ወደጠየቀኝ ጥያቄ በቀጥታ አመራሁ፡፡

ለአፍታ እንደመለስ ዜናዊ ልሁን፡፡ በትግርኛ “ሀፍረት” የሚል ቃል አውቃለሁ፡፡ ይሄውም ራሱ ባማርኛ ያለው ቃል ነው – ሀፍረት፡፡ “ኻፈረ፣ ኻፊሩ፣ የኽፍር፣ ኻፍረት ዘይብሉ…” እያለ ይበዛል፡፡ “አፈርኩ፣ አፈረ፣ ያሣፍራል፣ ሀፍረት የሌለው…” እንደማለት ነው፡፡ መቼስ መረገምና የሰይጣን ነገር ሆኖ እንጂ አማርኛና ትግርኛ በቋንቋ ተለያይተው የማይለያዩ መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡ መለስ ስለ ሱዳን ሲጠየቅ ስለ ፊጂ አይደል የሚናገር ? አሁን ከመለስነቴ ልውጣና ወደተጠየቅሁት ልሂድ፡፡
ጓደኛየ በጠየቀኝ ጥያቄ ምክንያት ብዙ አላዘንኩበትም፡፡ ፍርዱን ነው፡፡ ምን ያድርግ? ዋሽንግተን ዲሲ እነዚያ ማፈሪያዎች ያን ፉስቶ (በርሜል) ሶሎሞን ተካልኝ በስማም እንደተባለበት ሰይጣን አፍዝዘውት በመሀከላቸው ገትረው በትግርኛ ዘፈን የደመቀ ፀረ-ኢትዮጵያዊ የሆነ ወያኔያዊ ድጋፋቸውን በኢትዮጵያውያኑ ተቃዋሚዎች ፊት ለፊት ሲያካሂዱ የተመለከተ ጤነኛ የመሀል አገር ሰው ይህን ጥያቄ ቢጠይቅ አልፈርድበትም፡፡ አማረ አረጋዊን ያዬ፣ የነስዬን መልፈስፈስ ያዬ፣ የነገብሩ አሥራትን መቆላጨት የታዘበ፣ የብዙኃን ተጋሩ አህዋትናን ደቂ አነስተዮን ወያኔያዊ የወቅቱን እልህ አስጨራሽ መፍጨርጨርና በኢትዮጵያዊነት ላይ ማመፅ፣ ሁሉንም ሊባል የሚችለውን የሀገራችንን ሥልጣንና የሀብት ምንጭ በአንድ ዘውግ ቁጥጥር ሥር መውደቅ የተመለከተ፣ ይህን ቁጥጥር ለማቆየት እነዚሁ ወገኖች የሚያደርጉትን እጅግ አሣፋሪ ድርጊት  የታዘበ በርግጥም “ይሉኝታ” ብቻ ሣይሆን “ኢትዮጵያ” የሚል ቃል በትግርኛ ስለመኖሩ ቢጠራጠር መሠረታዊው እውነት እንደዚያ እንዳልሆነ ለማስረዳት ከመድከም በስተቀር መፍረድ ከባድ ነው፡፡ ትልቁ ችግር እንግዲህ አሁን ያለውን ክፉኛ የተመሰቃቀለ status quo ወደ status quo ante የመመለሱ ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህ ዘረኞች ያልረጩት መርዝ የለም፤ የዘሩትን መርዝ በጥበብ ለማርከስ እነሱ ከሚያራምዱት የአስተሳሰብ ዋሻ ወጥቶ እጅግ አስተዋይና ጥበበኛ መሆን ይገባል፡፡ እንደአነስታይን አባባል አንድ ችግር በተፈጠረበት አስተሳሰብ መንገድ ተጉዞ ያን ችግር ማስወገድ አይቻልም፡፡ ባጭሩ ለዘረኝነት መርዝ ማርከሻው ሌላ ዘረኝነት ሣይሆን ሰፊ የአስተሳሰብና የአመለካከት አድማስ ነው፡፡ እንደወያኔ ከተጓዝን ኢትዮጵያ ውስጥ ሊፈጠር የሚችለው ችግር – የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና – ሦርያና ሶማሌ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር የሚያስመሰግን ይሆናል፡፡ የሰዎቹ(የወያኔዎቹ) ሥራ ያን የሚጋብዝና ሀገሪቱን ከዓለም ካርታ የሚያጠፋ ነው፡፡ እርግጥ ነው – ይህ ተልእኮ የነሱ ሣይሆን የላኪዎቻቸው የኃያላኑ ኢትዮጵያን የማጥፋት ድብቅ ሤራ ተልእኮ ነው፡፡ ላኪዎቹም ተላላኪዎቹም በመጨረሻው መጨረሻ መጥፋታቸው የማይቀር ቢሆንም ለጊዜው ግን ክፉኛ እየጎዳን ነው፡፡ ይሁን፡፡ ምን ይደረጋል? ብድርን እየተከፋፈሉ መኖርን እንደባህል መሃላችን ላይ ካቆመብን እሱ ፊቱን እስኪያዞርልንና ምሕረቱን እስኪልክልን ምን አማራጭ አለን?  እንጂ እኚህ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር አንጻር እፍኝ የማይሞሉ ልጆች ይህን ሁሉ ሲዖላዊ ተዓምር ያደርጋሉ፣ ይህን ሁሉ የልዩነት ዘር ዘርተው ያፋጁናል፣ ይህን ሁሉ አጋንንታዊ ዶሴ ከፍተው እንደባቢሎን ያፍረከርኩናል… ብሎ ማን ሊያምን ይችላል? ዕዝ ነው፡፡ ፍርጃ ነው፡፡ ለዚህ መከራ የዳረገን የነሱ ብርታት አይደለም፡፡ የኛም ፍርሀት አይደለም፡፡ የነሱ ምልዓትም አይደለም፡፡ የብዙ ነገሮች ጥርቅምና የታሪካዊ ዑደት ውጤት ነው፤ እናም ያልፋል፡፡
የዚያችን ነገረኛ ቃል ሁኔታ ለማወቅ አእምሮየን ለአፍታ ፈተሽኩ፡፡ አወጣሁ – አወረድኩ፡፡ አምላኬንም “ኧረ እባክህን አታሣፍረኝ!” ብዬ ለመንኩ፡፡ ግን አልሆነልኝም –  “ይሉኝታ” የምትለዋን የአማርኛ ቃል በትግርኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ(vocabulary/dictionary) ላገኛት አልቻልኩም – አላውቅም የአቅም ውሱንነት ሊኖርብኝ ይችል ይሆናል፤ የምትችሉ ታዲያ አግዙኝና በአስተያየት ዓምድ ጠቁሙኝ፡፡ ይህን እንደቁም ነገር አዘል ቀልድ ውሰዱልኝና ቃሉ በትግርኛ ኖረም አልኖረም በተግባር ግን የሀገረሰቡ የትግራይ ሕዝብ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው፣ በእንግዳ ተቀባይነቱ ወደር የማይገኝለትና ከራሱ ይልቅ ለሌሎች በቀናነት የሚያስብ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ታዲያ እነዚህን ወያኔ ልጆቹን እንደዚህ ጨካኝና ይሉኝታቢስ ያደረጋቸው ምን ይሆን? ከወጡበት ማኅበረሰብ ፍጹም ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ እንዲህ ዐይን አውጣና ሀፍረተቢስ ያደረጋቸው በርግጥ ጥላቻና ቂም በቀል ነው ወይንስ በዘረመላዊ(ጄኔቲክ) ለውጥ ምክንያት ከሰውነት ተራ ወጡ ብሎ መጠየቅ መጠራጠርም ተገቢ ነው፡፡ ሰው በጤናው መቼም እንዲህ እነሱ እየሆኑትና እያደረጉት እንዳሉት አይሆንም፤ አያደርግምም፡፡ እነዚህን ሰዎች ሳስብ የናይጄሪያው ቦኮሃራም፣ የቲምቡክቱን የቀደመ ሥልጣኔ የደመሰሱት የማሊዎቹ ቱዋሬጎች፣ የሶማሊያው አልሻባብ፣ የሜክሲኮዎቹ የዕፅ አዘዋዋሪ ነጋዴዎች፣ የጣሊያን ማፊያዎች፣ የዐረቡ ዓለም አልቃኢዳዎች፣ የቅርብ ጊዜ ክስተቶቹ የመካከለኛው ምሥራቅ ኢስላሚክ ካሊፌት ተብዬዎቹና የበላይ አለቃቸው ሣጥናኤል በተጓዳኝ ትዝ ይሉኛል፡፡ የቴዲ አፍሮን የሰሞኑን መከሰስ፣ የማኅበረ ቅዱሣንን በአሸባሪነት መፈረጅ፣ የሙስሊሞቹን በሀሰት ክስ መታሰር፣ ስንቱ ተዘርዝሮ … ይህን ሁሉ የፈጣጣ ሥራ መፈብረክ ምን ያሳያል?
አብዛኛው የትግራይ ኤሊት – እኔን ሳይጨምር – ይሉኝታን አያውቅም፤ እውነቴን ነው ይሉኝታቢስ ብሆን ኖሮ ቢያንስ በአንድ እስር ቤት ጥሩ ገራፊ ሆኜ ይሄኔ አንዳርጋቸው ጽጌን ባልተወለደ አንጀት እያንገበገብኩ ካርማየን ባቆሸሽኩና በውጤቱ ደግሞ በስባሽ ሥጋየን ባወፈርኩ ነበር – እንደሰሜነኛነቴ ቢሆን፡፡ እንደውነቱ ይሉኝታቢስነት ሰብኣዊ እንጂ ባሕርያዊ ሊሆን እንደማይችል ግልጽ ነው፡፡ እንደዚያ ቢሆን ለምሳሌ ወያኔዎች ሁሉ ይሉኝታቢስ ሆነው በሚታዩበት በአሁኑ ሁኔታ ገነት ዘውዴና አባዱላ ገመዳ ባለይሉኝታዎች ሊሆኑ በተገባቸው ነበር፡፡ ባንዳነትና ይሉኝታቢስነት በዘርና በዘውግ የማይሄድ ለመሆኑ ብዙ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ማቅረብ በተቻለ፡፡ “ካለበት የተጋባበት” እንዲሉ ከጳጳሱ በላይ ካቶሊክ መሆን የሚቃጣቸው ብዙ የተጋቦት ወያኔዎችን ስናይ ይህ መጥፎና ተለዋዋጭ ጠባይ የማያበላሸው የሰው ዘር እንደሌለ እንረዳለን፡፡ ይሉኝታቢስነት ፈውስ የሌለው በጣም አደገኛ በሽታ ነው፡፡ ከዚህ በሽታ ናጻ ለመሆን የፈጣሪን ቸርነት ይጠይቃል፡፡ ለከት የማይበጅለት ሆድ እያለ ደግሞ ዓለማችን ከዚህ በሽታ ትገላገላለች ማለት ዘበት ነው፡፡ ሆዱንና ግላዊ የሥጋ ፍላጎቱን መቆጣጠርና ማሸነፍ የማይችል ሰው ደግሞ እናቱና ልጁን እስከመሸጥ ይደርሳል፡፡ ራስ ወዳድነት ትልቁ የይሉኝታቢስነት በሽታ መንስኤ ነው፡፡ ከዚህ በሽታ ራሳቸውን ነጻ የሚያወጡ – ከዬዘውጉ – በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ እንደ አስገደ ገ/ሥላሤና  አብርሃ ደስታ፣ ገ/መድኅን አርዓያና የኢትዮሰማይ ድረገፅ አዘጋጅ ጌታቸው ረዳ፣ (ፕሮፌሰር መስፍን እኚህን መሰል ደጋግ ትግሬዎችን ሲጠቅሱ ‹ዐሥር ቢሞሉልኝ ደስ ባለኝ› ብለው ነበር ልበል?) … አዎ… ዘመኑ የፈተና ነው፡፡ መጽሐፉ “ተዓቀብ ዘንተ በዐቢይ ትጋህ” እንዲል ቆመን ያለን የሚመስለን በተለይ ለዚህች ለቀረች ትንሽ ጊዜ ላለመውደቅ እንበርታ፡፡ ጊዜ መጥፎ ነው – ለነገሩ መጥፎው ሰውና አስተሳሰቡ እንጂ ጊዜማ ከመምሸትና ከመንጋት ውጪ ምን አደረገ?…
ይሉኝታን ለማወቅ በመጀመሪያ ሰው ሆኖ መፈጠርን ይጠይቃል፡፡ ሰው ሆኖ ለመፈጠርና እንደሰውም ለመቆጠር የመጀመሪያው መለኪያ ከዘረኝነት አረንቋ መላቀቅ ነው፡፡ ሌላው ከጥላቻ ተላቅቆ የፍቅር ሰው መሆንን ይጠይቃል፡፡ ዘረኝነትና ጥላቻ( ጥላቻው መሠረት ይኑረውም አይኑረውም) ሰውን ከሰው ብቻ ሣይሆን ከቀሪው የእንስሳት ዓለምም በእጅጉ ያወርዳሉ፡፡ ውሾች ከውሾች ጋር፣ ጅቦች ከጅቦች ጋር፣ ዓሣሞችም ከዓሣሞች ጋር እንጂ ከሌሎች ጋር አይተባበሩም፤ በመንጋም አይሄዱም፡፡ ሰው ደግሞ ከእንስሳት የበለጠ ውድና ለፈጣሪ የቀረበ በአምሳሉም የተፈጠረ የምድር ገዢ ፍጡር ነው፡፡ የ40 ዓመታት የ“አማራ” ጓደኛህ ጋር ባቡር መንገድ ላይ እየሄድክ ሳለ አንድ ትግሬ ስታይ ቋንቋህን ስለተናገረ ብቻ የዘመናት ጓደኛህን ትተህና ከነመፈጠሩም ረስተህ ከዚያ “መሰልህ” ጋር ብትከንፍ ሰው አለመሆንህን ተረዳ፡፡ አዎ፣ ዕቅጩን ልንገርህ ሰው አይደለህም፡፡ ሰው በሰውነቱ እንጂ በቋንቋውና በዘውጉ ልታቀርበው ወይም ልታርቀው አይገባህምና ይህ እንስሳዊ ጠባይ ነው፤ እንዳንተ ዓይነቱ “ሰው” ትልቅ ሥልጣን ይዞ “ሀገር ሲያስተዳድር” እንግዲህ ይታይህ፡፡ እንዲህ ዓይነት ኅሊናው በዘረኝነት ደዌ የታወረ ሰው በዚያ ላይ ተጨባጭ መሠረት በሌለው ጥላቻ ተኮትኩቶ ያደገና በሕጻንነቱ ለትግል ወደበረሃ የወረደ ሰው በሚጠላው ወገን ላይ ምን ዓይነት ዘመቻ ሊከፍት እንደሚችል አስበው፡፡ በቅድስቲቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 40 እና 23 ዓመታት እየሆነ ያለው ይሄው ነው፡፡ ይህም ጠባይ ተማረ ሠለጠነ በሚባለው “ኤሊት” ተብዬው የማኅበረሰብ ክፍል እንጂ ባላገሩማ ሲያልፍም አይነካው፤ ከንጹሕ ተፈጥሮው ጋር ይኖራል – በሚያገኙት አጋጣሚ “ኤሊቶች” ካልበረዙት፡፡ በኔ የመረረ ስሜታዊ አገላለጽ ኤሊት ማለት ውሻ ነው፡፡ “ሁሉም አይደለም” ብዬ ማስተዛዘኛ ቢጤ ብናገር ከፍርሀትና ከይሉኝታ ሣይሆን ከንፍሮ ጥሬ እንደሚወጣ ሁሉ ከኤሊቶች መካከልም  ከሥልጣንና ከሀብት አራራ ርቀው ለሀገርና ለወገን የሚያስቡ፣ በታሪክ መጥፋትና መደለዝም የሚጨነቁ ቅን አሳቢዎች መኖራቸውን የመጠቆም ግዴታ ስላለብኝ ነው፡፡ አብዛኛው ከየዘውጉ የምታዘበው ኤሊት ተብዬ ግን የሀገርና የሕዝብ ፀር የሆነ ከውሻም ውሻ ነው፡፡ እንዲያውም ውሻ በአንድ በኩል ከሰው የሚበልጥበት ጠባይ አለው፤ ከታመነ ታመነ ነው፡፡ ለምን ይሆን ግን ውሻን በስድብነት የምንጠቀምበት? ምናልባት በልክስክስነቱ ይሆን? ብቻ ለምዶብን “ውሻ” እያልን የሚያናድደንን እንሳደባለን፡፡ እኔማ ፈርዶብኝ የሚያናድደኝ መብዛቱ፤ ታዲያ ስንቱን ከሃዲና ይሉኝታቢስ “ውሻ” ብዬ እዘልቀዋለሁ፡፡ እነኃይሌ አባሃና፣ እነሠራዊት ፍቅሬ፣ እነሣምሶን ቀፎ፣ እነንዋይ ደበበ፣ እነውብሸት ‹አርዓያሰብ›፣ እነሙሉጌታ አሥራበ ካሣ፣ እነሰሎሞን ተካልኝ፣እነክህደቱ አያሌው፣ … ይህን ሁሉ የወያኔ አዘጥዛጭና የባንዳዎች ባንዳ ሁሉ ተሳድቦ መጨረስ እንዴት ይቻላል?
ማፈሪያው አማረ አረጋዊ ያን ሁሉ የተማረውን የጋዜጠኝነት ትምህርት አዲዮስ ብሎ እንደውሻ ወደዘር ኩይሣው ውስጥ በመግባት “ጽንፈኞች ኢትዮጵያን አታዋርዱ” በሚል ርዕስ በቅርቡ የጻፈውን የሪፖርተር ጋዜጣ ርዕሰ አንቀጽ አንብቡለት፤ በዘረኝነት ልክፍት እንዴት እንደሚቅበዘበዝና በወያኔ ፍቅር እንዴት እንደሚቅመደመድ ታያላችሁ፤ ለይቶለት እንዳበደም ትረዳላችሁ – ታዝኑለትም ዘንድ ኅሊናችሁ ግድ ሳይላችሁ አትቀሩም፤ ክረስሮስ “የሚያደርጉትን አያውቁም ይቅር በላቸው” ያለው ወዶ አይደለም፡፡ በ“የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ” የውሾች ፈሊጥ የፈጠጠውን እውነት ላለማየት የብየዳ ጉግልስ የሚመስል የዘር መነጽሩን ዐይኑ ላይ ሰግጦ የጻፈውን ርዕሰ አንቀጽ ስታነቡለት አማረ ምን ያህል የተጎዳ ሥነ ልቦና ባለቤት መሆኑን በቀላሉ ትገነዘባላችሁ – ውሻነት ደግሞ ከዚህ በላይ የለም፡፡ ሰው ጠቁሞኝ ይህን ግማቱ ከሩቅ የሚያቅለሽልሽ ርዕሰ አንቀጽ በጥሞናና በከፍተኛ ጉጉት አነበብኩት፡፡ የመስከረም ወር መጨረሻ እሁድ ቀን ዕትሙ ይመስለኛልና ልታነቡለት የሚገባ የሰውዬውንም ብልሹ ባሕርይ ቁልጭ አድርጎ የሚያሣይ ግሩም ርዕሰ አንቀጽ ነው፡፡ ከበሸቀጡና ከገሙ አይቀር እንደዚህ ነው፤ ቪቫ አማረ! ግን ቀንህ ደርሷልና ቶሎ ቶሎ ጩኽ፡፡ የማትጮኸበት ጊዜ መምጣቱ ስለማይቀር በወያኔ ባጀት በሚደገፍ ሚዲያህ አሁንና ዛሬ በደንብ አቅራራ – “ጀምበር ሳለ ሩጥ አባት ሳለ አጊጥ” ነውና በማስታወቂያና በልዩ ድጋፍ ስም በምታጋብሰው የሀገር ሀብት እየተምነሸነሽክ የሀብቱ ጌታ የሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አዋርደው፤ ምን ትሆናለህ? ምንም፡፡ የኑሮ ችግሩን እንደሆነ ለእኛ ተወው፤ ስደቱን ለኛ ተወው፤ እንግልቱን ለኛ ተወው፤ እስራቱንና ወፌላላውን ለኛ ተወው፤ በዘር ምክንያት ከምድረ ገጽ መጥፋቱን ለሌሎች ተወው፤ የአገዛዙን ጭራቃዊ ቀምበር ለኛ ተወው፤ አንተ ያለብህ ይህን የከረፋ የዘረኞች ሥርዓት ቅባት እየቀባባህ ዕድሜውን ማራዘምና ከመክፈልቷደግሞ የድርሻህን ያህል መቦጨቅ ነው፡፡ በወደቀ የኢትዮጵያዊነት ግንድ ላይም ያሉህን ምሣሮች ሁሉ አንድም ሣታስቀር ቀርቅብ፡፡ ይሉኝታቢስነት ባንተ አልተጀመረምና በዚህ አሣፋሪ ጠባይህ ግፋበት፡፡ መጥፎ ምግባር ካላስቀበረ ስለማይቀር ይብላኝ ለነገው ታሪክህ፡፡ታሪክህ እንደሌሎች መሰሎችህ ሁሉ “ሆዳምነትና ዘረኝነት እስከመቃብር” በሚል መድብል ወደፊት ለንባብ የሚበቃ ይሆናል፡፡ ዛሬ ግን ኅሊናህ የታወረ፣ ጭንቅላትህ የደነበሸ፣ ጆሮህ የደነቆረ፣ ሁለመናህ በጥቅምና በደም ትስስር የተበከለ፣… በዚያም ሳቢያ እውነቱን ላለማየት የተሣነህ ድውይ ነህና የሚታዘንልህ ምሥኪን ዜጋ ነህ፡፡
ይህ ርዕሰ አንቀጽ ዘጠኝ አንቀጾች ያሉት ሲሆን ሁሉም አንቀጾች የተቃውሞውን ጎራ የሚያበሻቅጡ ናቸው፡፡ መነሻው የዋሽንግተኑ የተቃዋሚዎች የወያኔን ኤምባሲ ለተወሰነ ጊዜ መቆጣጠርና እውነተኛዋን ሰንደቅ ዓላማ ለደቂቃዎችም ቢሆን ማውለብለብ ነው፡፡ ውሻው አማረ የሚጮኸው “ … በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓት አለ፡፡ በዚህ ሥርዓት መሠረትም አገር የሚመራ መንግሥት አለ፡፡…”እያለ ነው፡፡(የ7ኛው አንቀጽ መነሻ ዐረፍተ ነገሮች) ድንቄም ህገ መንግሥት፣ ድንቄም አገር የሚመራ መንግሥት፡፡ ለነገሩ እነዚህን ዐ. ነገሮች ስንመረምራቸው ራሱ አማረም ቢሆን አንደበቱን ያዝ እያደረገውና በ”መንግሥቱ” እያፈረበት በፈራ ተባ የጻፈው መሆኑን መረዳት ይቻላል፤ ባያፍርበት ኖሮማ “በኢትዮጵያችን በሕዝበ ውሳኔ በሙሉ ድምፅ የጸደቀ ሕገ መንግሥት አለን፡፡ ይህን ሕገ መንግሥት ሙሉ በሙሉ አክብሮ የሚንቀሳቀስና በሕዝብ ያልተሸራረፈ ዴሞክራሲያዊ መብት የተመረጠ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት አለን፡፡ በሀገራችን ቦምብና ጥይት ሣይሆን ማርና ወተት እያዘነበ ያለ ኅብረ ብሔራዊ መንግሥትና ኅብረ ብሔራዊ መከላከያ አለን፡፡…” በማለት ይበልጥ በሣቅ ባፈነዳን ነበር፡፡ ወይ ሆድ! ሆድና ዘረኝነት ለካንስ እንደዚህ ያደድባል? ጣሊያኖች ሲናደዱ “ፊሌ ዲ ካኔ!” የሚሉት ወደው አይደለም – “የውሻ ልጅ!” ለማለት፡፡  እነሱ ምን የሌላቸው ስድብ አለ – “ቴስታ ዲ ጋሊና”ም ይላሉ – እንዳማረ አረጋዊና መሰል የዘረኝነት ልምሻ የሚያጥመለምላቸውን ድኩማን ዜጎች “ዶሮ ራስ” ብለው መሳደብ ሲያምራቸው፡፡ አማረ ግን አይገርምም ትላላችሁ? ውይ ረስቼው – ይሄው ጭንጋፍ ሰውዬ ያኔ በ97 “ ኢሕአዴግ ቢሸነፍ ኖሮ ‹ትምክህተኛና ነፍጣም› ዳግም ከሚገዛኝ ጠበንጃ ይዤ በረሃ እገባ ነበር” ብሎ ነበር አሉ፡፡ ጨካ የሚወርደው የተበደለ፣ የተጨቆነ፣ ፍትህን የተራበ፣ የተጎሳቆለ… ነው እንጂ እንደነአማረና እንደነበረከት፣ እንደነሣሞራና እንደነሰዓረ፣ እንደነአርከበና እንደነሥዩም፣ እንደነስብሃትና እንደነአባይ ያለ የጠገበ ትኋን አይደለም፤ እንደነዚህ ያለ የጠገበ መዥገር ከእንግዲህ በረሃ ወርዶ — ዛር ወርዶ ተንቀጥቅጦ— ዘምቦ ተባርቆ — የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ትግል አከሽፋለሁ ማለት የፍትህ አምላክ የሆነውን እግዚአብሔርን ጭምር የመታገል ያህል ነው፡፡ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ትኋኖችና መዥገሮች በራሳቸው ጊዜ ሣይቀር ማንም ሳይነካቸው ይፈርጣሉ፤ ያቺን መከረኛ ቃል ከትግርኛ መዝገበ ቃላት ያወጡ የአስተሳሰብ ድውያን ዘረኞችም ታሪካዊና የማይቀር ዋጋቸውን ይከፈላሉ፡፡ ከፋይ ማን ነው? ማን ሊሆን ይችላል – በሠፈሩት ቁና መሥፈርን የፍትህ ሚዛኑ ዓርማ ያደረገው እግዚአብሔር ነዋ! ምን ጥርጥር አለው፡፡ ነፍስ ይማር ጋሽ አማረ! ይህችን ጽሑፍ ያዛት፡፡ ዕድሜ ዘልዛላ ነው፡፡ እንገናኝ ይሆናል – ከይንራኸብ’ውን አይንተርፍን ኢና ወዲ ዓደይ – ክሳብ ሽዑ ግና ንኣሃን ከምዕውን ንኸብዶም ኢሎምስ ምስወያነ ተሰሊፎም ዓድናን እንዳቀተሉ ንዘለው ተጋሩ አኅዋተይን እግዚእብሔር ልባማት ምእንቲ ክገብሮም፣ ሀዱሽ ታሪኽ ምዕንቲ ክሠርኹ ክክአሎም ውሽጢ ዐይኒታቶምን ከብርሆሎም ይምነ፡፡ ዘይሃልፍ የለን፤ ሰማይን ምድሪን ወሲኹ ሁሉ ነገር የሀልፍ፡፡ ዘየሃልፍ ግና እዙይ ንስኻን ምስካልኦት ቆልኡት ዓድናን እንዳገበርኩም ዘለሁም ታሪኽ ዘይረስዖ ፀላም ግብሪ ኢዩ፡፡
አማረ አናጋው በሪፖርተሩ እንዲህ ይለናል፤
ይህ ዘመን ወደድንም ጠላንም በሕጋዊ መንገድ የመንግሥት ሥልጣን የሚያዝበት ነው፡፡ ይህ መንግሥታዊ ሥልጣን ደግሞ የሚገኘው በሕዝብ ድምፅ ብቻ ነው፡፡ የሕዝብ ድምፅ ወሳኝ የሚሆነው ዲሞክራሲ በተሟላ ሁኔታ ሲሰፍን ነው፡፡ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ዋነኛ ፀር አምባገነንነትና ጽንፈኝነት ናቸው፡፡ እነዚህን አሉታዊ ተግባሮች የሚያራምዱ ወገኖች ጠባቸው ከማንም ጋር ሳይሆን ከባለድምፁ ሕዝብ ጋር ነው፡፡ በዚህ ዘመን የሕዝብን ወሳኝነት አለማመንና ጭልጥ ብሎ ወደሕገወጥነት መንጎድ የትም አያደርስም፡፡ ማንም የፈለገውን የመደገፍ ወይም የመቃወም፣ የመምረጥ ወይም ያለመምረጥ መብት አለው፡፡ ይህ መብት ደግሞ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ በሕግም ዋስትና ያገኘ ነው፡፡ ነግ ግን ይህ መብት ተግባራዊ የሚሆነው በሕጋዊ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ሕጋዊውን መንገድ ትቶ አገርን የሚያፈራርስ ተግባር መፈጸም በሕግ ያስጠይቃል፡፡ መብቴ ተጓድሏል የሚል ሕግና ሥርዓትን ተከትሎ እስከመጨረሻው ደድረስ በመጓዝ መብቱን የማስከበር ኋላፊነት የራሱ ብቻ ነው፡፡ ተጠያቂውም ተጨንቆና ተጠቦ ምላሽ መስጠት ይኖርበታል፡፡ ሕገወጥነት አገሪቱን እንዳያዋርድ መጠንቀቅ ይገባል፡፡
ይህ አንቀጽ ቢተነተን አንድ ትልቅ መጽሐፍ ይወጣዋል፡፡ አንባቢ እየደጋገምክ በማንበብ ተንትነው፡፡ ለአማረ ግን የምለው የመጨረሻ ቃል እንዲህ ነው፡፡ “ቋንቋ የተፈጠረው እውነትን አናት አናቷን ቀጥቅጦ ለመግደል ነው፡፡” አዎ፣ የአማረ አረጋዊ ጥረት ኢትዮጵያዊትን እውነት በአማርኛ ቋንቋ መዶሻነት ቀጥቅጦ ድራሹዋን ለማጥፋት ነው፤ ግን እውነት ትቀጥናለች እንጂ አትበጠስምና ይህ ውሽከታህ ውኃ የማያነሣና ፍጹም ሀሰት መሆኑን ዓለም የሚመሰክርበት ጊዜ እየቀረበ ነው – እመነኝ፡፡ ከሰው ሣይሆን አንተንና መሰል መዥገሮችን በኢትዮጵያና ሕዝቧ ጫንቃ ላይ ለቅጣት የጣለውን የአምላከ ኢትዮጵያን ፍርድ በቅርብ ታያለህ፡፡ ይቅናችሁ – አሪቬዴርቺ አማረ፡፡

No comments:

Post a Comment