Thursday, October 30, 2014

‪#‎Ethiopia‬ በገዥው የወያኔ መንግሰት ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻች መቼም ቢሆን አንረሳቸሁም፡፡

መቼም አንረሳችሁም !
ምርጫ 97 ተከትሎ ጥቅምት 22/1998 ዓ.ም በግፍ የተገደሉ፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና ከአገር የተሰደዱ ጀግኖቻችንን መቼም ቢሆን በታሪክ ይዘከራሉ፡፡በመሆኑም ከጥቅመት 20 እስከ 23 የሚቆይ የማህበራዊ ድረገፅ ንቅናቂ በሰፊው ይካሄዳል፡፡ የዚህ ንቅናቂ ዋናው ዓላማ በግፍ ግድያ ሕይወታቸውን ያጡ በክብር በማሰታወስ ፣ገዥውን የወያኔ መንግሰት ለመለወጥ ጊዜው አሁን መሆኑን ለማመላከት ነው፡፡

በዚህም መሠረት ከላይ የተገለፀውን ዓላማ ተቀዳሚ ያደረግ በሥነ-ፁሑፍ፣ በፎቶ ግራፍ እና በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ ጀግኖች ሰማዕታትን የሚያስታውስ እና የተጀመረው ትግል ውጤታማነትን የሚያበረታታ ሰፊ ቅስቀሳ ይደረጋል፡፡ አንተም አንቺም የዚህ ንቅናቂ ተሣታፊ ለመሆን ፣መስፈርቱ የገዥውን የአምባገነን የወያኔ ስርዓት መቃወም ብቻ ነው፡፡
በመሆኑም በዚህ ንቅናቂ የሚስማማ ሁሉ ካዘሬ ጀምሮ ከላይ በተገለፁት ዘዴዎች ከጥቅምት 20 እስከ 23 በሚደረገው የማህበራዊ ድረገፅ ንቅናቂ ተሳታፊ እንዲሆን ሕይወታቸውን ባጡ በጀግኖች ስም ጥያቄው ቀርቧአል፡፡የማህበራዊ ድረገፅ ፕሮፋይል መለያ ፎቶ ከዚህ ፁሑፍ ጋር ተያዟል፡፡
ይህ መረጃ ለሁሉም አንዲዳረስ የሁላችንም ግዴታ ነው!
ኢትዮጵያን ፈጣሪ ይባርካት፣አሜን !!!

No comments:

Post a Comment