ሰበር ዜና –የካንጋሮው ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ 3 ዓመት

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቱን ተጠቅሞ የፍትህ ጋዜጣና መጽሄትን ሲያዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ካንጋሮው ፍርድ ቤት 3 ዓመት የእስር ቅጣት ማስተላለፉ ተመለከተ::
የፍርድ ትዕዛዝ እስኪተላለፍበት ለ2 ሳምንታት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የቆየው ጋዜጠኛው በ እዚያው እስር ቤት ውስጥ አንገቱ ላይ የሚያስራትን እስካርቭ እንዲያወልቅ በፖሊሶች ት እዛዝ ቢሰጠውም ጋዜጠኛው አላወልቅም በማለቱ ሰው እንዳይጠይቀውና ብቻውን እንዲታሰር መደረጉን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል::
(ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)
No comments:
Post a Comment