Sunday, October 19, 2014

ተወዳጁ ድምፃዊ ናትናኤል አያሌው (NHATI MAN ) ከአገር ተሰደደ


 ማነው የሚለየው ይህ ትውልድ ፍም እሳት ነው በሚለው ስሜት ቀስቃሽ ዘፈኑ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አድናቆትና ዝናን ያተረፈው ድምፃዊ ናቲ ማን በወያኔ ዘንድ ፍም የሆነችውን ዘፈኑን ለአድማጭ ካደረሰ ጀምሮ ወያኔ ድምፃዊውን መላወሻ አሳጥቶት እንደነበርና የሚያደርሱበትን ችግር መቋቋም ስላቃተው ወደ አውስትራሊያ መሰደዱን ምንጮቻችን ገልፀዋል ።ይህ ድምፃዊ በአገር ቤትና በውጪ አገራት  በሚያቀርባቸው ስራዎቹ ላይ ፍም እሳ የሚለው ዘፈኑን በሚጫወትበት ግዜ ህዝብ ለማነሳሳት ሞክረሃል፣አላማህ ሌላ ነው፣ከጀርባህ ሌሎች ሰዎች አሉ በማለት የተለያዩ ዛቻና ማሰፈራሪያዎች ሲደርሱበት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
ወያኔዎች ንፁሃን ዜጎችን፣ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ከማሳደድ አልፎ ወደ ድምፃዊያን ዘመቻቸውን አድርገውታል። ማነው ባለ ሳምንት ?????? በነገራችን ላይ ይህ ህዝብ ፍም እሳት ነው የሚለው ዘፈን ኢትዮጵያዊን በሚሰባሰቡበት ስፍራና በአዲስ አበባ ስታዲዮምም ሳይቀር ተወዳጅ ዘፈን እየሆነ መቷል።   


ማን ነው የሚለየው? የሚደፍረው?
ይህም ትውልድ ፍም እሳት ነው።
የታለ አንድነቱ…. የፍቅር ተምሳሌቱ?
አረ ጎበዝ…..
እምቢ በል!
እምቢ…. እምቢእምቢ…..

No comments:

Post a Comment