ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማክሰኞ ጥቅምት ፬ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፪

ሌሎችን መረጃዎች እንኳ ብንተዋቸው፣ በራሳቸው ፓርላማ ተብዬ እንደገለፁልን፣ በ፲(አሥር) ዓመታት ጊዜ ውስጥ 2.5 ሚሊዮን (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ) ዐማሮች ሥልታዊ በሆነ መንገድ እንዲጠፉ ማድረጋቸውን ራሳቸው አምነው ነግረውናል። ለዘር ማጥፋት ዘመቻቸው የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች፦ ተፈጥሮአዊ የመዋለድ መብቱን በማሳጣት ዐማራውን ተተኪ ትውልድ-አልባ ማድረግ፣ የኤች.አይ.ቪ./ኤድስ በሽታን በሰው-ሠራሽ መንገድ በመርፌ በማሰራጨት ዐማራውን ሟች እና ታማሚ ማድረግ፣ ወባ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን በዐማራው ላይ ማስፋፋት ይገኙበታል። በዐማራው ላይ በመፈፀም ላይ ላለው የዘር ማጥፋት ድርጊት ሌላው ማሣያ፣ ከጭፍጨፈው በገፍ በመሸሽ በስደት ከሚኖሩት ኢትዮጵያውያን መካከል በቁጥር ዐማራው ከፍተኛውን መጠን የያዘ መሆኑ ይታወቃል። በአሜሪካን አገር ያለው የትግሬ-ወያኔ ኤምባሲ ባደረገው ጥናት መሠረት በዩ.ኤስ. አሜሪካ በስደት ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ውስጥ ስድሣ ከመቶው ዐማራ ነው። ይህም ዐማራው በአገሩ በሰላም ሠርቶ የመኖር መብቱን በይፋ የተከለከለ መሆኑን በግልፅ ያሣያል።
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ ዐማራው በዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ ለከፍተኛ እና አሠቃቂ እልቂት ተጋላጭ የሆነው፣ እርሱን ሆኖ ለመቆም ባለመቻሉ ብቻ ሳይሆን፣ ጥቃቱን ለመቋቋም ባለመደራጀቱ እንደሆነ ያምናል። በዚህም ምክንያት ባለፉት ሁለት ዓመታት ይህን ጉልህ ክፍተት ለመሙላት ዐማራውን ለማደራጀት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል። ይህ የዐማራው መደራጀት እና ራሱን ሆኖ የመቆም አዝማሚያ ሥጋት የለቀቀባቸው ወያኔ እና መሰል የዐማራው ነገድ ጠላቶች፣ «ሳይቃጠል በቅጠል» እንዲሉ፣ ዐማራውን በቡድን የመጨረስ ዓላማቸውን በስፋት ተያይዘውታል። ለዚህም ሠሞኑን በጋምቤላ ክልል በሜጢ ወረዳ፣ እንዲሁም በደቡብ ክልል በማጂ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ ይኖሩ በነበሩ ዐማሮች ላይ የሚፈፅሙት የማባረር እና ንብረት የመዝረፍ ብቻ ሳይሆን፣ በታጣቂ አስከብቦ መተናፈሻ በማሳጣት በጅምላ የመግደል ስልት የማያወላውል ማስተማመኛ ነው። በዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ፣ ግን በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ዐማሮች የተገደሉ መሆኑ ታውቋል።
የሠሞኑ የትግሬ-ወያኔ የዘር ማጥፋት ሠለባ ኢትዮጵያዊ ጨቅላ
ይህ ላለፉት ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት የትግሬ-ወያኔ በዐማራው ነገድ ላይ በማድረስ ላይ ያለው የዘር ማፅዳት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ፣ ድርጅታችን የተቋቋመበት መሠረታዊ ዓላማ መሬት የያዘ ሐቅ መሆኑን በተጨባጭ ያሣያል። በተጨማሪም በሌለ የይስሙላ የኢትዮጵያዊነት ካባ ተጠፍሮ፣ የወገኑን ሞት፣ ስደት፣ ስቃይ፣ መከራ እና ርሃብ በትዝብት ቆሞ ለሚመለከተው፣ እንዲሁም ለሞረሽ-ወገኔ ጥሪ «ጆሮ ዳባ ልበስ» ላለው ዐማራ የማንቂያ ደወል እንደሆነ ይቆጥረዋል። ከዐማራው ቀንደኛ ጠላቶች ጎን ቆሞ ለወገኖቹ መጥፊያ እጀታ ለሆነው «ሆዳም ዐማራ» ደግሞ ራሱን ቆም ብሎ እንዲመረምር የሚያደርግ የማንነት ጥያቄ የሚደቅን እና ለማንነት ለመቆም የሚያስገድድ ፈታኝ ሁኔታ እንደሆነ ይረዳል። በሌላ በኩል ድርጊቱ ለሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በርቶት መታገል ተጨማሪ የቁጭት እና የመጠቃት ስንቅ እያስቋጠረ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። «ደባ ራሱን፣ ስለት ድጉሱን» ነውና፣ ይህ የትግሬ-ወያኔ ድርጊት የማይቀርለትን ታሪካዊ ውድቀቱን የሚያፋጥን ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ እንደሆነ ያስገነዝበናል።
ሠሞኑን ወያኔ እና አጋሮቹ በእርዳ-ተራዳ ዐማራውን እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞችን በአንድነት ጨፍልቀው ለማጥፋት የከፈቱት ዘመቻ ሁለቱንም ወገኖች ወደ አንድነት እና የተቀነባበረ ትግል እንዲገቡ ደወል የሚያሰማ ነው። የሁለቱ አንድነት ወያኔን ከሥልጣኑ የሚፈነግል እና የኢትዮጵያን ትንሣኤ የሚያበስር ሁኔታ ሊፈጥር ወደሚችል አቅጣጫ እንሚወስድ ሊታወቅ ይገባል። ስለዚህ የጥቃቱ ሰለባ የሆናችሁ፣ የዐማራው ነገድ አባሎች ዘራችሁ ፈጽሞ ሳይጠፋ፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮችም የሆናችሁ ማተባችሁ ሳይቆረጥ፣ በአንድነት በመቆም በማንነታችን እና በሃይማኖታችን ላይ የጥፋት ክንዱን ባነሣው ወያኔ እና መሰሎቹ ለመዝመት እንዘጋጅ! የማይቀረውን ሞት ቆመን በፍርሃት ተውጠን ከመሞት፣ ገዳዮቻችን በቆራጥነት ታግለን ለመጣል እንነሣ! የአባቶቻችን ይትባሃል «ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ» ነውና ዛሬውኑ ይህንኑ ዕውን እናድርግ! ለዚህም ከሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ጎን በመቆም የወገኖቻች ደም እንፈስ! የአገራችንን ትንሣዔ እናብስር! ግፉ እና በደሉ በዚህ ይብቃ! ግፉ በዚህ እንዲያቆም ፍላጎቱ ያለን፣ የግፉ ማስቆሚያ መንገድ ተደራጅቶ ከጠላት ፊት መቆም ነው። ለዚህም የሞረሽ-ወገኔን ዓርማ በማንሳት በተቀነባበረ ትግል አጥፊያችን ፈጽሞ ሳያጠፋን የእርሱን እስትንፋስ እናስቁም!
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!
No comments:
Post a Comment