Saturday, October 18, 2014

ፓትርያርክ ብፁዕ አባ ማትያስና ተግዳሮቶቻቸው

በተክሉ አባተ
አቡነ ማቲያስ
አቡነ ማቲያስ
ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከተሾሙ እነሆ ሁለት ዓመት ሊሞላቸው አራት ወራት ገደማ ይቀራቸዋል:: ቅድመና ድኅረ ሹመታቸውን ተከትሎ የውይይትና የክርክር መድረኮች በኢትዮጵያም በውጭውም ዓለም ተከፍተው ነበር:: የአምስተኛው ፓትርያርክ የብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ድንገተኛ ሞት አንዳች ለውጥ ለቤተ ክርስቲያኗ ያመጣ ይሆናል ብለው የገመቱና የተመኙ ብዙዎች ነበሩ::
ሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ ሊያወርዱ እንደሚችሉ ተተነተነ:: ዳሩ ግን የእርቁ ሂደት ሳያልቅ ምርጫ ተደረገና ብፁዕ አቡነ ማትያስ በወሳኝ ድምጽ እንዳሸነፉ ተነገረ:: መንግስት ከነበሩበት አስመጥቶ እንዳሾማቸው:: እርሳቸውም ነጭ ልብስ እንደማይለብሱና የቅንጦት ኑሮ እንደሚጸየፉ: ቤተ ክርስቲያን ያጣችውን ክብርና ተሰሚነት እንደሚመልሱ ተናገሩ:: «ይህን ማን አየው» በሚል ተስፋ አዲሱ ፓትርያርክ የለውጥ ሐዋርያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ቅር እያላቸውም ቢሆን የገመቱ ነበሩ: -- [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

No comments:

Post a Comment